Ethiopian Artificial Intelligence Institute


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute. The institute is established under the regulation No. 463/2020 with defined powers and responsibilities.

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በምድራችን የውሃ አካላት ውስጥ አራት ሺህ የሚደርሱ ሮቦቶች እንደሚንቀሳቀሱ ያውቁ ኖሯል?

በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት ውስጥ የምድር የውሃ አካላት ቁልፍ ስፍራ አላቸው፡፡ ሙቀት እና ካርቦን ዳይኦክሳይድን አምቆ በመያዝ ረገድም ሚናቸው አይናቅም፡፡

ሆኖም የመሬት ገፅን ሰባ አንድ በመቶ ከሚሸፍኑት የውሃ አካላት ለአየር ሁኔታ ትንበያ እና መሰል አገልግሎቶች የሚውል ትክክለኛ እንዲሁም በቂ መረጃ መሰብሰብ እጅግ አዳጋች ሆኖ ቆይቷል፡፡

ይህን የተረዳው አርጎ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ዓለም አቀፍ ጥምረት አራት ሺህ የሚደርሱ #ሮቦቶችን በምድር ዙሪያ ባሉ የውሃ አካላት በማሰማራት ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና በቂ መረጃ እየሰበሰበ እንደሚገኝ IEEE Spectrum የተባለው ድረ-ገጽ አስነብቧል፡፡

ይህ ከዓለም ዙሪያ በተውጣጡ ሰላሳ ሀገራት ጥምረት ትግበራ ላይ የሚገኝ እንቅስቃሴ #ፍሎትስ የሚል መጠሪያ በተሰጣቸው አነስተኛ ሮቦቶች አማካኝነት መረጃዎችን እየሰበሰበ ይገኛል፡፡

ሮቦቶቹ ሁሉንም ጊዜያቸውን ከውሃ አካላቱ ገፅ በሺህ ሜትሮች ዝቅ ብለው በመንቀሳቀስ የውሃውን ሙቀት እና ጨዋማነት እየለኩ ይቆያሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሮቦቶች የውሃ አካላቱን ሥነ-ሕይወት እና የንጥረ ነገር ውቅር (ኬሚስትሪ) የተመለከቱ መረጃዎች ጭምር ይሰበስባሉ፡፡

የሰበሰቡትን መረጃ ፈረንሳይ እና ካሊፎርኒያ ወደሚገኙ የዳታ ማዕከላት በሳተላይት አማካኝነት ለማስተላለፍ በየአስር ቀኑ ወደ ውሃ አካላቱ ገጽ ብቅ ብለው ይንሳፈፋሉ፡፡

መረጃውን በዚህ መልክ ለመሰብሰብ ያስፈለገበት ዓብይ ምክንያትም በመሬት የአየር ንብረት ውስጥ የውሃ አካላቱ ያላቸውን ሚና በመረዳት ወደፊት የተሻሉ ትንበያዎችን ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል፡፡








አትላንቲክ ውቅያኖስን ያቋረጠችው ሰው ዓልባ ጀልባ

ሜይፍላወር የተባለችው ሮቦት ጀልባ ከእንግሊዝ ፕሊመዝ ከተማ በመነሳት አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጣ በምሥራቅ ካናዳ የወደብ ከተማ ወደሆነው ሀሊፋክስ መድረሷ ተዘግቧል፡፡

በአይ.ቢ.ኤም ኩባንያ የበለፀገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥርዓት በጀልባዋ ላይ የተገጠሙ ስድስት ካሜራዎች እና ሃምሣ አነፍናፊዎችን (ሴንሰር) በመጠቀም ቀዘፋውን እንደሚከውን ተገልጿል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የምትመራው ሜይፍላወር አራት ሺህ አራት መቶ ኪሎሜትሮችን በጉዞዋ መሸፈኗን ቢ.ቢ.ሲ ዘግቧል፡፡

ጀልባዋ ምንም እንኳን ቀዳሚ የጉዞ መዳረሻዋ ሀገረ አሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት ቢሆንም በጉዞዋ በገጠማት ዕክል ምክንያት መዳረሻዋን ለመቀየር ተገዳለች፡፡

ይህች አስራ አምስት ሜትሮች ርዝመት ያላት እና በፀሐይ ኃይል የምትንቀሳቀስ ጀልባ ሃያ ኪሎሜትር በሰዓት የመቅዘፍ አቅም እንዳላት ተመላክቷል፡፡






አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ኢትዮኔስት ቴክኖሎጂ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የምርምር እና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ታዬ ግርማ እንዲሁም የኢትዮኔስት ቴክኖሎጂ ማናጀር አቶ ዘላለም መሰለ ተፈራርመዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ታዬ ግርማ የሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት መስማማታቸው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮኔስት በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያቋቋሙት የቴክኖሎጂ ተቋም በመሆኑ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሙያ እና መሰል ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮኔስት ቴክኖሎጂ ማናጀር አቶ ዘላለም መሰለ በበኩላቸው በውጭ ሀገር ያካበትነውን አቅም ለኢትዮጵያ አስተዋጽዎ እንዲያበረክት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የስራ ሀላፊዎች በተለያዩ ፕሮጀክቶች በሚደረግ መደጋገፍ በጋራ ፍሬያማ ስራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡










Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሳተላይቶች ወደ ህዋ ሲመጥቁ ዋንኛ ተግባራቸው የምድር ሁኔታ የሚያሳዩ እጅግ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን በማንሳት መላክ ነው፡፡ የዛሬው ጥንቅር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግኝት ሳተለያቶች እንዲያስቡ ያደረገ በፈጣን መንገድም የመረጃ መላላኩን በቅጽበት እንዲካሄድ ያደረገ ነው፡፡












አዲስ ገጽታን ተላብሶ የመጣ ብስክሌት ነው፡፡የሚሰራው በኤሌክትሪክ ነው፡፡ የተለያዩ የብስክሌቱን ወቅታዊ ሁኔታ መከታተል የሚያስችል ማሳያ ስክሪን አለው፡፡ሙሉ መረጃውን ከዝግጅቱ፡፡ https://youtu.be/8--bx8b2ET8


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በኢንስቲትዩቱ የሚገኘው ዳታ ማዕከል እና የሀገራችንን የተለያዩ ተቋማት የአገልግሎት ጥራት እና ፍጥነት ለማዘምን እየተሰሩ የሚገኙ የምርምር ሥራዎች የተዳሰሱበትን ጥንቅር ተጋበዙልን፡፡

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 331

obunachilar
Kanal statistikasi