FDRE Education and Training Authority


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/
9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri










ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጥ የነበረው አዲስ ፈቃድ፤ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ተደረገ
-- ---------------------------------------------------------------------
በአማኑኤል ይልቃል
የፌደራል የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን፤ ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆመ። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፈቃድ መስጠት ያቆመው፤ ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያዘጋጀ ያለውን “አዲስ የመመዘኛ መስፈርት” የማውጣት ስራን እስኪያጠናቀቅ መሆኑን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የትምህርት እና ስልጠና ጥራትን የማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለበት ይህ የፌደራል ተቋም፤ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ማንኛውም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ የመስጠት ስልጣን በማቋቋሚያ ደንቡ ተሰጥቶታል። ተቋሙ ፈቃድ በሚሰጣቸው የትምህርት ተቋማት ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ ሲሆን፤ ባገኘው ውጤት መሰረትም ዕውቅና የመስጠት፣ የማደስ እና የመሰረዝ ስልጣን አለው።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በመላው ሀገሪቱ ፈቃድ ከሰጣቸው 360 ገደማ የሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ፤ 60 በመቶ ያህሉ የተከፈቱት “በቅርብ ዓመታት” ውስጥ መሆኑን በተቋሙ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በብዛት እየተከፈቱ መሆናቸው ዘርፉ ባለሀብቶችን እየሳበ ስለመሆኑ ማሳያ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ውብሸት፤ ሆኖም በሚሰጧቸው ትምህርቶች ጥራት ረገድ ከፍተኛ ችግር እንደሚስተዋል አስረድተዋል።
በተጨማሪም የተቋማቱ መብዛት እና የሚቀበሏቸው ተማሪዎች ቁጥር ከተፈቀደላቸው “በብዙ እጥፍ” የበለጠ መሆኑ፤ ተቋሙ የሚያከናውነውን የቁጥጥር ስራ “አዳጋች” እንዳደረገው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። “ይህንን መግታት እና ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻለው፤ የተቋማቱ ቁጥር ሲቀንስ ወይም ባለበት ሲገታ ነው” የሚሉት አቶ ውብሸት፤ በዚህም ምክንያት አዲስ ለሚከፈቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት በማቆም፤ ያሉትን የማጥራት ስራዎች ላይ ትኩረት መደረጉን አስታውቀዋል።
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን “ክትትል ያላደረገባቸው፣ ፍቃዳቸው ያልታደሰ እና ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚሰሩ ተቋማት” እንዳሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት ብቻ፤ “የመመሪያ ጥሰት ፈጽመዋል” ባላቸው ከ350 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቆ ነበር። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ፈጽመዋቸዋል ከተባሉ ጥሰቶች ውስጥ፤ ፈቃድ ባልተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች፣ ካምፓሶች እና የትምህርት አሰጣጥ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይገኙባቸዋል።
ባለሥልጣኑ ካለፈው ወር ህዳር 30፤ 2015 ጀምሮ ደግሞ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በአዲስ ፈቃድ ላይ እገዳ ጥሎ በሚቆይባቸው ጊዜያት ውስጥ፤ ከዚህ ቀደም ፈቃድ ያገኙ ተቋማት ፈቃድ ያገኙበትን መንገድ፣ የተቋሞቹን ባለቤቶች ማንነት እና ያሉበትን ሁኔታ የመፈተሽ እቅድ ይዟል። የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህም ባሻገር፤ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት እና ተቋማቱን የሚከፍቱ ባለሃብቶች ምን አይነት መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው የሚደነግጉ መመሪያዎችን እየዘጋጀ ነው።
የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚያስጀምሯቸው የትምህርት ፕሮግራሞች፤ ፈቃድ ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን አዲስ የመመዘኛ መስፈርቶች (ስታንዳርዶች) የማዘጋጀት እና ያሉትን መመዘኛዎች የመከለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ወብሸት አስረድተዋል። ከእነዚህ ዝግጅቶች መጠናቀቅ በኋላ፤ ከዚህ ቀደም ፈቃድ ያላቸው የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ በመመዘኛ መስፈርቶቹ መሰረት ምዝገባ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
እንደ አዲስ ምዝገባ የሚፈጸም መሆኑ ተቋማቱን “ለማጥራት እና እርምጃ ለመውሰድ” እንደሚረዳ የገለጹት አቶ ውብሸት፤ ከዚህ ሂደት በኋላ ከተቋማቱ እና ከተማሪዎቻቸው ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች እንደሚሰጥባቸው ተናግረዋል። ውሳኔዎቹን ለመስጠት በሚያስፈልገው ጊዜ ምክንያትም፤ በተያዘው ዓመት አዲስ ፈቃድ የመስጠት ስራ ይጀምራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


#ተቋሙ_ሐሰተኛ_የትምህርት_ማስረጃን_ለማጥራት_ከባለድርሻ_አካላት_ጋር_በቅንጅት_እየሠራ_ነው
====== ====== ====
ታደሰ ብናልፈው
አዲስ አበባ፡- በፌዴራልና በክልል የመንግሥት ተቋማት በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው የሚሠሩ ግለሰቦችን ለማጥራት በትብብር እየተሠራ መሆኑን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።
የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ማርታ አድማስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት በሚሠራው መጠነ ሰፊ ሥራ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠሩ ነው።
የፌዴራልና የክልል ተቋማት አዲስ የሰው ኃይል ቅጥር ሲፈፅሙ እና የደረጃ ዕድገት ሲሠጡ የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ መሆንና አለመሆኑ እንዲጣራላቸው ወደ ተቋሙ መላካቸው አብረው የመሥራት ቁርጠኝነታቸውን ያሳያል ብለዋል።
እንደማሳያም የደበብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከክልል እስከ ወረዳ ያለው የመንግሥት መዋቅር ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማጋለጥና በማጥራት ሂደት ቀዳሚ እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ተቋማት ከትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን ጋር በቅርበት እየሠሩ መሆኑን ወይዘሪት ማርታ ተናግረዋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ማምጣታቸውንና መረጃ ተቀብሎ የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የ12ኛ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለከፍተኛ የመንግሥት ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው እንዲሠለጥኑ የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው የግል ተቋማት መግቢያ ነጥብ መኖሩን አውስተው ተማሪዎች የግል የትምህርት ተቋማትን ሲቀላቀሉ የፌደራል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን ነጥብ አሟልተው መግባታቸውን ለማጥራት የተማሪዎችን ሰነድ እየፈተሹ እንደሆነ አብራርተዋል።
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የ12ኛ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለከፍተኛ የመንግሥት ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው እንዲሠለጥኑ የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው የግል ተቋማት መግቢያ ነጥብ መኖሩን አውስተው ተማሪዎች የግል የትምህርት ተቋማትን ሲቀላቀሉ የፌደራል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን ነጥብ አሟልተው መግባታቸውን ለማጥራት የተማሪዎችን ሰነድ እየፈተሹ እንደሆነ አብራርተዋል።
አያይዘውም መስፈርቱን ሳያሟሉ በተገኙ ተማሪዎች እና ከተፈቀደላቸው የማስተማር፣ የፕሮግራም እና የቁጥር ፍቃድ ውጭ እየተቀበሉ በሚያሠለጥኑ የግል ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የግል ተቋማት በአንድ የሙያ ዘርፍ ከተፈቀደላቸው የተማሪ ቁጥር በላይ አልፈው ሲያሰለጥኑ ከተገኙ ተማሪዎች ብቻ መቀጣታቸው ቀርቶ ተቋማትንም ለመቅጣት ከፍትሕ አካላትና ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ጋር ለመሥራት መታቀዱን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ተቋሙ የማስተማር ፍቃድ እና የሚሰጣቸው የፕሮግራም ፍቃድ የማጣራት ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ለኅብረተሰቡም ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንዲኖረው ማንኛውንም የሚዲያ አውታር በመጠቀም ግንዛቤ እንዳስጨበጠና በማስጨበጥ ላይ እንደሆነ የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተናግረዋል።
ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት የፌዴራል መንግሥት በተለያየ ዘርፍ ከባለሥልጣኑ ጋር እየሠራ መሆኑን እና ወደፊትም በቁርጠኝት ለመሥራት ጥናት እየተደረገ እንደሆን ጠቁመው ትውልድ ገዳይ የሆነውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለማጥራት መንግሥት፣ ኅብረተሰቡ እና ሚዲያዎች በማጋለጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።




#ለሚመለከታቸው ሁሉ
ጉዳዩ፡- ወደ ባለሥልጣኑ ደብዳቤዎችን የሚልኩ አካላት አዲሱን ስያሜ ብቻ እንዲጠቀሙ ስለማሳሰብ
በቀድሞው ‘የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ’ ተብሎ ሲጠራ የነበረው መ/ቤታችን በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 መሰረት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተብሎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የቀድሞውን ስያሜ በመጠቀም ወደ መ/ቤታችን የሚላኩ ደብዳቤዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን እየገለጽን፤ ለቀጣይ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ወደ ባለሥልጣኑ የሚልኳቸውን ደብዳቤዎች ‘ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን’ በማለት አዲሱን ስያሜ ብቻ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡


የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መዋቅር
====== ======
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አንድ ዋና ዳይሬክተር፣ ሶስት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችና ሌሎች በርካታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ፣ ሥራ አስፈፃሚ እና ዴስክ ሃላፊ የሥራ ክፍሎች የተቋቋመ ነው፡፡ ሶስቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችም፡-
I. ፈቃድ አሰጣጥ እና ጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣
II. ኢንስፔክሽንና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና
III. የዕውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ናቸዉ፡፡
I. ፈቃድ አሰጣጥና ጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
በስሩ ሶስት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሥራ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ማለትም ፡-
I. የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ፣
II. የቴክኒክና ሙያና አጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና
III. ጥራት ኦዲት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
 የዳይሬክቶሬቱ ተግባርና ኃላፊነት፡-
ከስያሜዉ ለመረዳት እንደሚቻለዉ ዳይሬክቶሬቱ ተቋማት የፈቃድ አሰጣጥና ፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን ለመስጠት የተዋቀረ ነው፡፡
 በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
I. በመደበኛና በርቀት መርሀ ግብሮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀርቡ የፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ጥያቄዎችን መልስ ይሰጣል፣
II. ድንበር ተሻጋሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2ተኛ ዲግሪ የስልጠና መስኮች የፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ይሰጣል፣
III. ወደ ከፍትኛ ትምህርት ለሚገቡና ነባር ተቋማት የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣
IV. በፌደራል ደረጃ ለሚቋቋሙ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት እና ለአጠቃላይ ትምህርት (ዓለም አቀፍ ት/ቤት፤ በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ማህበረስብ ት/ቤት፣ በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረስብ ት/ቤት የፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ይሰጣል፣
V. የጥራት ኦዲት አገልግሎት ይሰጣል፣
VI. ፈቃድ የተሰጣቸውን ተቋማት፡ካምፓሶች ፕሮግራሞች በተመለከተ መረጃ መስጠትና ማሳወቅ፣ የሚሉት በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች ናቸው፡፡
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን
ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ


ባለሥልጣኑ_የእርምት እርምጃ የወሰደባቸውን 3 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ካምፓሶቻቸውን ይፋ_አደረገ
========== ========== ========
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው የድንገተኛ ጉብኝት ፍተሻ የስነ-ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ ሐራምቤ ዩንቨርስቲ ሲኤምሲ ካምፓስ፤ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ እና ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ ካምፓስ ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን ይፋ አደረገ ፡፡
ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ሐራምቤ ዩንቨርሲቲ በሲኤምሲ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በዲግሪ መርሀ ግብር በቢዝነስ ማኔጅመንት የትምህርት መስክ ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ፤ ፈቃድ ባላገኘባቸው ማስተርስ ኢን ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ማስተርስ ኢን አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ የትምህርት መስኮች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር አድርጎ ማስታወቁ እና የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማሩ በመረጋገጡ የቅድመ ምረቃ ቢዝነስ ማኔጅመንት የትምህርት መስክ በመዝጋት እና የመዘገባቸውን ተማሪዎች በማሰናበት ለባለስልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ለተከታታይ 3 ዓመታት በመረሀ ግብሩ ፈቃድ እንዳይጠይቅ እግድ የተጣለበት መሆኑን ገልጿል፡፡
ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአራት ኪሎ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር በማስተርስ ኦፍ ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ በመረጋገጡ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር በማስተርስ ኦፍ ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስኮች በመዝጋትና የመዘገባቸው ተማሪዎችን በማሰናበት ለባለስልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ከላይ ለተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ለተከታታይ 3 ዓመታት በመረሀ ግብሮቹ ፈቃድ እንዳይጠይቅ እግድ የተጣለበት መሆኑን መሆኑን ገልጿል፡፡
ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ካምፓሱ ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ በማስተርስ ኦፍ በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን እና ግሎባል ስተዲስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን እያስተማረ መሆኑ በባለሥልጣኑ በመረጋገጡ በመጀመሪያ ዲግሪ በግሎባል ስተዲስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን እና በመጀመሪያ ዲግሪ በግልባል ስተዲስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስኮች ከቁጥር በላይ የመዘገባቸውን ተማሪዎች ፈቃድ ወዳላቸዉ ተቋማት በማሰናበት ለባለስልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ከላይ ለተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ለተከታታይ 2 ዓመታት ተማሪ እንዳይቀበል እግድ የተጣለበት መሆኑን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም በተፈፀመው የህግ ጥሰት ግኝት የተቋሙ ባለሀብቶች እና የበላይ አመራሮች ከዚህ በተጨማሪ ወይም ተያያዥነት ባላቸው የህግ ጉዳዮች ጥሰት በፍትሀ ብሄርና በወንጀል ህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ካለ በሚመለከታቸው የፍትህ አላካት ተጠያቂ የሚያደረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ


#ማሳሰቢያ
ለሚመለከተው ሁሉ
-----------------------
ኤም. ኤስ .ኤል .ጂ (MSLG) ኮሌጅ ከትምህርት ስልጠና ባለሥልጣን በሁለተኛ ዲግሪ በድንበር ተሻጋሪ መርሃ ግብር በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን፣ በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን ኢን ግሎባል ስተዲስ፣ በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን ኢን ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት የትምህርት መስኮች እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ በአካውንቲንግና ፋይናንስ የትምህርት መስክ ፈቃድ ያገኘ ቢሆንም በተደጋጋሚ በተደረገው ክትትል ለባለሥልጣኑ ሳያሳዉቅ የመማር ማስተማር ሥራ እንዳቆመ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንኑ በመገንዘብ ከተጠቀሰዉ ተቋም ምንም ዓይነት ከትምህርትና ስልጠና ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዳይጠቀም እናሳስባለን፡፡


የስነ-ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ በ2 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ካምፓሶቻቸው ላይ የእርምት እርምጃ ተወሰደባቸው
========== ========== ===========
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው የድንገተኛ ጉብኝት ፍተሻ የስነ-ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙት ግሬት ኮሌጅ መገናኛ ፣ ቦሌ ሚካኤል እና ቡልቡላ ካምፓሶች እና ሮያል ኮሌጅ ሰሜን ካምፓስ ላይ ነው የማስተካከያ እርምጃ የተወሰደው ፡፡
ግሬት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስክ ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ መዝግቦ ማስተማሩ፤ በቦሌ ሚካኤል ካምፓስ በማስተርስና በዲግሪ መረሀ ግብር በመደበኛና በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት እና በማታ መረሀ ግብር ምዝገባ ላይ እንዳለ በማስታወቁ እና ቡልቡላ ካምፓስ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን፣በመጀመሪያ ዲግሪ መረሀ ግብር በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና በማኔጅመንት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማሩ መረጋገጡ ተገልጿል ፡፡
በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ ግሬት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስክ ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ የመዘገባቸውን ተማሪዎች እንዲያሰናብትና በትምህርት መስኩ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል እግድ የተጣለበት መሆኑ ተገልጿል ፡፡በቦሌ ሚካኤል ካምፓስ በማስተርስና በዲግሪ በመደበኛና በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት እና በማታ መረሀ ግብር የመዘገባቸውን ተማሪዎች በማሰናበት ለባለሥልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ለተከታታይ 3 ዓመታት በመረሀ ግብሮቹ ፈቃድ እንዳይጠይቅ እግድ የተጣለበት መሆኑም ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ቡልቡላ ካምፓስ ያለእውቅና ፈቃድ የከፈተውን ማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን፣በመጀመሪያ ዲግሪ መረሀ ግብር በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና በማኔጅመንት የትምህርት መስኮች በመዝጋት የመዘገባቸውን ተማሪዎች በማሰናበት ለባለሥልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ለተከታታይ 3 ዓመታት በመረሀ ግብሮቹ ፈቃድ እንዳይጠይቅ እግድ የተጣለበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሮያል ኮሌጅ አዲስ አበባ በሚገኝው ሰሜን ካምፓሱ ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ ተማሪዎችን በዲግሪ መረሀ ግብር ተቀብሎ በማስተማር ላይ በመሆኑ ያለፈቃድ የከፈተውን መረሀ ግብር በመዝጋትና የመዘገባቸውን ተማሪዎች በማሰናበት ለባለሥልጣኑ በ10 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርግና በካምፓሱ ለተከታታይ 3 ዓመታት በመረሀ ግብሮቹ ፈቃድ እንዳይጠይቅ እግድ የተጣለበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በተፈጸመው የህግ ጥሰት ግኝት የተቋሙ ባለሀብቶች እና የበላይ አመራሮች ከዚህ በተጨማሪ ወይም ተያያዥነት ባላቸው የህግ ጉዳዮች ጥሰት በፍትሀ ብሄርና በወንጀል ህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ካለ በሚመለከታቸው የፍትህ አላካት ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን
ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ


የ12 ክፍል ተፈታኞች ወደ ግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ውጤት ካመጡ ከባለስልጣኑ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ወቅታዊ ቁመና ማጣራት አለባቸው
========== ========= ==========
ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቂ ማጣራት ሳያደርጉ ከባለስልጣኑ ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ባልተፈቀደ የትምህርት ዘርፍ ተምረው ውጤት ቢያመጡም ውጤታቸው አይረጋገጥም ሲሉ ወ/ሪት ማርታ አድማሱ በኢፌድሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ለኢቲዮ .ኤፍ. ኤም ተናግረዋል ።
ለዚህም ሲባል ዝግጅት መደረጉን አንስተው በያዘ ነው ሳምንት መጨረሻ ስለ አጠቃላይ የኮሌጆች ቁመና ትክክለኛ መረጃ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ይፋ እንደሚያደርግ ለኢቲዮ. ኤፍ. ኤም ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው የአቅም ማሻሻያ ( በሪሚዲያል ፕሮግራም ) የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲቀበሉ የሚወሰንላቸው ነጥብን እየተጠባበቅን ነው የሚሉት ወ/ሪት ማርታ ውጤቱ ይፋ ሲሆን የግል ኮሌጆችን በዛ መሰረት እንዲሰሩ ቁጥጥር የምናደርግ ይሆናል ብለዋል።
ባለስልጣኑ የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸውን ፣ ፍቃድ ያላቸውን እና የሌላቸውን እየተከታተለ በተቋሙ ድረ ገፅ ላይ በቀለማት በመለየት እንደሚያጋራ እና ተማሪው ያንን ሳያጣራ ከመመዝገብ እንዲቆጠብም አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል የተለያዩ ኮሌጆች መመሪያውን ጥሰው ሲሰሩ መያዛቸውን ይፋ አድርገን ነበር የሚሉት ወ/ሪት ማርታ አሁንም ህብረተሰቡ የኛን መረጃ በመከታተል ካለአስፈላጊ ወጪ እና ከጊዜ ብክነት ራሱን ማዳን ይኖርበታል ብለዋል።
ቀደም ብሎ እንደተገለጸው በ2014 ዓ.ም በተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ እና በሌሎች የክልል ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችን እና ቅርንጫፎቻቸውን በ5 ዙር ማሳወቁ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በ1ኛው ዙር(አዲስ አበባ ከተማ) 106 ፤ እንዲሁም በክልል ከተሞች 2ኛው ዙር 95፣ በ3ኛው ዙር 104፣ በ4ኛው ዙር 27 እና በ5ኛው ዙር 25 በድምሩ 357 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶች እና ቅርንጫፎቻቸው ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱንም ገልጾ ነበር።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም


ባለሥልጣኑ ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃንን ስርዓተ ትምህርቱ በሚደነገገው የጊዜ ገደብ እንዲያስመርቁ አሳሰበ
========= ========= ========
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ዓ.ም እና በደንብ ቁጥር 515/2014 ከተሰጡት ኃለፊነት እና ተግባራት መካከል አንዱ ምሩቃን የሀገሪቱ ስርዓተ ትምህርት ላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እና አጠቃላይ ክሬዲትአወር (credit hour) በሙሉ ማጠናቃቀቸውን መቆጣጠር እና ማረጋገጥ ነው፡፡
ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ባለስልጣኑ የምሩቃንን የትምህርት ማስረጃዎች በሚያረጋግጥበት ወቅት ተቋማት ስርዓተ-ትምህርቱ ላይ ከተደነገገው የጊዜ ገደብ እና ክሬዲት አወር (credit hour) በታች እንዲሁም በላይ አስመርቀው መገኘታቸውን መረጋገጡን ገልጿል፡፡
በዚህ ደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ የምሩቃን የትምህርት ማስረጃ በስርዓተትምህርቱ ላይ ከተደነገገው የጊዜ ገደብ እና ክሬዲት አወር (credit hour) በታች ወይም በላይ ሆኖ ሲገኝ ባለስልጣኑ ተቋማት ላይ አስፈላገውን የእርምት እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አስታውቋል፡፡


#በከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት_የሚደረገው_ክትትል #Asham_Tv [የካቲት 14/2015 ዓ.ም]
በኢፌዲሪ ትምህርትና ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒዩኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ማርታ አድማሱ እና የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማህበር ስራ አስፈጻሚ አቶ ተገኝ አለሜ ከአሻም ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቆይታ።
https://youtu.be/hkW5gGNwwKo


የድህረ ምረቃ ትምህርት የሚሰጡ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቋሚ መምህራኖቻቸውን የስም ዝርዝር እንዲልኩ ተጠየቀ
========= ========= =========
ባለሥልጣኑ በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያስተማሩ ያሉ መምህራንን መረጃ በማደራጀት ለጥናትና ምርምር ግብአትነት ለመጠቀም በድህረ ምረቃ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ትምህረት እየሰጡ ያሉ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ስም ዝርዝር መሰብሰብ ማስፈለጉን አስታውቋል፡፡
የድህረ ምረቃ ትምህርት የሚሰጡ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይህ ደብዳቤ ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ ባሉት የ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ የቋሚ መምህራኖቻቸውን የስም ዝርዝር እንዲልኩ አሳስቧል፡፡









20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

3 894

obunachilar
Kanal statistikasi