GRACE TUBE


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


" ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር #ጸጋ ተገልጦአልና፤"
(ወደ ቲቶ 2:11)
@Sabbath_School
Share your favorite quotes and stories for us to learn @Selah_Weekly

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


📚የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ

____________________________________________________________________________


ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ። ቲቶ 2፡11-15

ፀጋ ምንድነው ብለን ብንጠይቅ አብዛኛው ሰው ነፃ ስጦታ ነው ብሎ እንደሚመልስ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ዛሬ ግን የተለየ ትርጉሙን እንመለከታለን፡፡

ፀጋን የሚያስችል ሃይል ፣ ለሰው በነፃ የተሰጠ የእግዚአብሄር ችሎታ እና የእግዚአብሄር ብቃት በማለት መተርጎም እንችላለን፡፡

ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ያለፈውን ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና በሃጢያታችን እንድንቀጥል አይደለም፡፡

ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ሃጢያታችንን ይቅር ሊለን ከአሁን በኋላ በእግዚአብሄር ፀጋ በሃጢያት ላይ የበላይ ሆነን እንድንኖር በሃይል ሊያስታጥቀን ነው፡፡ ፀጋ በህይወታችን ያስፈገበት ምክኒያት ከሃጢያት የበላይ ሆንን እንድንኖር ሊያበረታን ነው፡፡

· ፀጋ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን እንድንኖር ያበረታናል፡፡

ሃጢያትን መካድ ቀላል አይደለም፡፡ ከዓለማዊ ምኞት የበላይ ሆኖ ጌታን ማክበር በእኛ የእግዚአብሄር ችሎታ መገለጥን ይጠይቃል፡፡ የፀጋም አላማ እኛን በማበርታት ኃጢአተኝነትና አለማዊ ምኞት በእኛ ላይ ጉልበት እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

· ፀጋ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ጉልበት ይሆነናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ስለመዳንም ሆነ ስለመቀደስ ሲያስቡ ሰማይ እስከሚሄዱ የማይሆንና በምድር ላይ የማይሳካ አድርገው ያስባሉ፡፡ መጽፅሃፍ ቅዱስ ግን በዚህ ዘመን ኢየሱስ ሳይመጣ የኢየሱስን መምጣት እየተጠባበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንድንኖር ፀጋው እንደሚያችለን ያስተምራል፡፡

ምክኒያቱን ሲናገር ኢየሱስ ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን እንደሰጠ ይነግረናል፡፡ የኢየሱስ ሞት አላማው እኛን በፀጋው ሃይል በማስቻል ከአመፃ የነፃን እግዚአብሄርን ለማገልገል የሚቀናን ህዝብ ማፍራት ነው፡፡

ይህ ጸጋ ተገልጦአል፡፡ ማንም ላለመዳን ፣ ራሱን ላለመግዛት ፣ በፅድቅ ላለመኖርና እግዚአብሄርን ላለመምሰል ሰበብ የለውም፡፡

@Grace_Tube
@Grace_Tube




ሁለቱ ሹፈሮች

በሹፍርና ህይወት ያሳለፈ አንድ ጎልማሳ ሰውዬ በመንገድ መኪና እያሽከረከረ እያለ አንድ ወጣት በህግ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ እያሽከረከረ እያለ ጎልማሳው ሹፈር መኪናውን ከፍትለፍት በማቆም ወጣቱ መክናውን እንዲያቆም ይነግረዋል።

ወጣቱም መኪናውን በማቆም በጎልማሳው ሹፈር በጣም ይናደድበታል ይጮህበታል ጎልማሳው ሹፈር ወጣቱ ሹፈር ተናግሮና ተበሳጭቶበት እስከምጨርስ ድረስ በትዕግሥት ጠበቀው ። ወጣቱ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ጎልማሳው ሹፈር ልጄ አሁን ያንተን ጨርሰሃል አሁን እኔን ስማኝ አለው ።

በማስቀጠልም ጎልማሳው ሹፈር " ልጄ እኔ በህይወት ዘመኔ በሹፍርና ብዙ ነገር አይቻለሁ ክፉውንም መልካሙንም አይቻለሁ ከመልካሙ ይልቅ ክፉ ነገር ስለሚበዛበት ልጄ ያስቆምኩህ ለህይወትህ ጥንቃቄ እንድትወስድ ብዬ ነው ያስቆምኩህ " አለው ።

ወጣቱ በጣም በመናደድ የራስህ ጉዳይ እኔ አንተን አይደለሁም አያገባህም ብሎት ተበሳጭቶበት ሄደ ። ብዙም ከጎልማሳው ሹፈር ሳይርግ ትልቅ መኪና ውስጥ ገብቶ ህይወቱን አጣ ።

እግዚአብሔር ስለእኛ ከእኛ በላይ ያስባል ። እግዚአብሔርን ስለእኔ አያገባህም ብሎ የሄዴ መጨረሻው ይህ ነው ።

" እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:7)

@YekalSink






✍ ክርስትያኖች ሆይ ..


፦ እምነት ብቻ አይበቃም
ምሠሉ....
፦ መምሠል ብቻ አይበቃም
ኑሩበት .....
፦ መኖር ብቻ አይበቃም
መስክሩ.....
፦ መመስከር ብቻ አይበቃም
አጠንክሩ .....
፦ ማጠንከር ብቻ አይበቃም
ብቁ አድርጉ.....
፦ ብቁ ማድረግ ብቻ አይበቃም
ወንጌልን አስፋፉ
፦ ማስፋፋት ብቻ አይበቃም
ምርኮን ሠብስቡ ።



፦ ይህን ስለምታደርጉ ፡ እያደረጋችሁም ስላለ ፡በጌታ ክርስቶስ ኢየሡስ ተባረኩልኝ ።

መልካም ሰንበት
¥
Happy Sabbath

@Yekalsink


ፍርሃት አብሮ የተፈጠረ ነገር አይደለም ። ድፍረትም ከሰው ልጅ ጋር በውልደቱ ግዜ አብሮት አልነበረም ። የሰው ልጅ ራሱን ያሳመነበት ነገር ነው ። ነገሮችን ሞክሮ ሳያውቅ እፈራለሁ ይላል ። ለመሆኑ የፈራሄው ነገር ምን እንደሆነ አይተሃልን ?

ምንነቱንና ማንነቱን ሳያውቅ ራሱን እፈራለሁ ብሎ ያሳምናል ።
አንድ ወጣት ወደ ቤቱ ስመጣ አምሽቾ መምጣት ጀመረ ። እሱ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ውሻ እንዳያልፍ ያደርገዋል ሁሌ አምሽቶ ስለምመጣ በጣም ያስቸግረው ነበር ። ወጣቱ በመናደድ አንድ ቀን እንደሁልጊዜው አምሾቶ እየመጣ ስያስቸግረው ለማባረር ብሎ ያለ የሌለ ሀይሉን ሰብስቦ በንዴት ልመታውና ልያባርረው ስጠጋ ውሻው ያረጀና ጥርስ የሌለው ሆኖ ያገኘዋል ። ወጣቱ ከዚህ በፍት በፍርሃት ያሳለፋቸው ግዜያት በጣም ቆጩት ።

እኛም እንደወጣቱ ማንነቱንና ምንነቱን ሳናውቅና ሳንረዳ ከሩቅ አይተን እንፈራለን ተጠግተን ካየነው ግን በጣም ቀላልና ቀላል ሆኖ እናገኘዋለን ።

" በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን? "
(መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1:9)

@SelahWeekly


Channel update

New weekly package is NOW ADDED to the channel.

An upgrade to the outreach with a weekly story Saturday : sharing with you an inspiring story to help us get more closer to God.

@SelahWeekly

Share your story with us @Selah_Weekly

God bless you all.


አቅም ያለን ይመስል ያሉብንን ችግሮች በራሳችን አቅምና ማስተዋል ለማሸነፍ ጥረት እናደርጋለን ። ድክመታችንን ባለመረዳት ለማሸነፍ የተለያዩ ነገሮችን እንሞክራለን ። ነገሮች ሁሉ እኛ ባሰብነውና ባቀድነው ይመስለናል ።

እስከዛሬ ድረስ በእውቀቱና በጥበቡ ችግሩንና ሸክሙን ያሸነፈ የለም ። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ሸክም አለበት ያለበትን ሸክም ለእግዚአብሔር አሳልፎ ብሰጥ ኖሮ ነገሮች ሁሉ ቀላልና የወረደ ዋጋ በኖራቸው ነበር ። እግዚአብሔር በልጁ አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሸክማችንን ሊያራግፍልን ይፈልጋል ። መድሃኒታችንም ይህንን ሸክማችንን ለማራገፍ ከሰማይ ወደ እኛ በማይገባ ሁናቴ ወረዳ ። ይህንን አስተውለን " ጌታ ሆይ እኔ ተሰባር ደካማ ፍጡር ነኝ ፤ ስለኔ አንተ አብስተህ ትጨነቃለህና ያለብኝንን ሸክም ሁሉ እንደጠየከን መሰረት ይሄው ላንተ አሳልፈን እንሰጣለን " የሚል ማን አለ ?

" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 11:28)

@SelahWeekly


ባለንበት ዘመን ክርስትና ዋጋ ባጣበትና እምነት በቃላት ጥበብ ሆኗል ። በየእምነት ቤቱ ከተካሄደ ቦታ የምሰጠው ሰዎችን በተረት ተረት ለሚያዝናና እንጅ የእግዚአብሔርን ቃል ገልጦ ለሚናገር አይደለም ።

ዘመኑ በተቀየረ ቁጥር እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ቃል የሚለወጥ ይመስል ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በራሱ ለራሱ ለመተርጎም ጥረት ያደርጋል ። ህይወት ሰጭ የሆነው የዘላለሙ የእግዚአብሔር ቃል ተዓምራትን እየሰራ የነበረ ወደፊትም የሚሰራ ድንቅ የሆነ የማይለወጥ ነው ።

" እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:4-5)

@SelahWeekly


መፅሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ለማጥናት የሚያስችል በየሶስት ወሩ እየተዘጋጀ የሚቀርብ የመጽሐፍ ቅዱስ መምሪያ ነው:: አያሌ ጥያቄዎች የሚጠየቁበትና መልሶች የሚሰጡበት ክፍት የውይይት መድረክ በመሆኑ አብረውን የሰንበት ትምህርት በመወያየት የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትዎን ያዳብሩ ።

አጋር ቻናል ፦ @SelahSoft

ለማንኛውም ጥያቄ ፦ @Selah_Soft

t.me/Sabbath_school


#የማለዳ_ስንቅ

#መንፈሳዊ_ቤት



ቤት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሰው የሚያርፍበትና የሚያድርበት ቤት ከሌለው አያርፍም፡፡ ሰው ቤት ካለው ደግሞ ነፃነቱ ይበዛል፡፡

እንዲሁም እግዚአብሄር የሚንቀሳቀስበት ፣ የሚናገርበት ፣ የሚገኝበት ፣ የሚያርፍበትና በጎነቱን የሚያስተላልፍበት ቤት ይፈልጋል፡፡ ቤት ሰፋ ባለ ቁጥር ፣ ቤት ንፁህ በሆነ መጠንና ቤት ጠንካራ በሆነ መጠን ለመኖርም ፣ እንግዳን ለመቀበልም ፣ ለማረፍም እንዲሁም ለማደር ያበረታታል፡፡ ቤት ግን በደንብ ካልተሰራ ፣ ንፅህናው በደንብ ካልተጠበቀ ፣ ጠንካራ መሰረት ላይ ካልተመሰረተ ፣ ውበት ከሌለው ለመኖር ፣ ለማረፍና እንግዳ ለመቀበል አይመችም፡፡

እኛም ንፁህ ሰፊ ጠንካራ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ራሳችንን ሰጠንና በተሰራን መጠን እግዚአብሄር በቀላሉ ፣ በደስታና በእረፍት በእኛ ይኖራል በእኛ ይታያል ፣ በእኛ ይናገራል ፣ በእኛ ይወቅሳል ፣ በእኛ ሌሎችን ይደርሳል ፣ በእኛ ያርፋል ፡፡

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡5

ቤት ማረፊያና መደሰቻ እንደመሆኑ መጠን የእግዚአብሄር ማረፊያና መደሰቻ ለመሆን እለት በእለት በእግዚአብሄር ቃል መሰራት ይኖርብናል፡፡ ሰው ሌላ ቦታ ቢያዝን ቤቱ ግን ማዘን የለበትም፡፡ ሰው ሌላ ቦታ ቢታመፅበት በቤቱ የሚነገረው ነገር ሁሉ እርሱን የሚያከብርና እርሱን የሚያስደስተው ብቻ መሆን አለበት፡፡

. . . ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ኤፌሶን 4፡29-30

ቤት መገኛ አድራሻ እንደመሆኑ መጠን የእግዚአብሄር በጎነት የሚገኝበት ፣ የእግዚአብሄር ምህረት የማይታጣበት ፣ የእግዚአብሄር ይቅርታ በልግስና የሚከፋፈልበት ፣ የእግዚአብሄር ፍቅር የማይጠፋበት መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። ኤፌሶን 4፡32

ቤት ንፁህ ነገር ብቻ የሚገኝበት እንደመሆኑ መጠን የእግዚአብሄር ነገር ብቻ የሚገኝበት ከሰይጣን ሃሳብና ከሃጢያት ምኞት የፀዳ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17

ቤት ከምንም አስቀድሞ አስተማማኝ በሆነ አለት መሰረት ላይ እንደሚገነባ ሁሉ በቃሉ መሰረት የእግዚአብሄር ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ማቴዎስ 7፡24

ሰው ከምንም በላይ ቤቱን በከበረ ነገር እንደሚያስውበው መጠን በየዋህነትና በዝግተኝነት የተዋበ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4

ቤት የሚስብ ትህትና የሚታይበት ቦታ እንደመሆኑ መጠን በትህትናና በተሰበረ ልብ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ቤት ለመሆን ተሰሩ፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2

" ኢየሱስም መለሰ አለውም። የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።"
(የዮሐንስ ወንጌል 14:23)

@SelahWeekly
@SelahWeekly






4, ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር የታገለበት ቦታ ምን ይባላል ? A ራማ B ጵንኤል C ኡር D ምድያም
So‘rovnoma
  •   A ኡር
  •   B ራማ
  •   C ጵኒኤል
  •   D ምድያም
10 ta ovoz


#የማለዳ_ስንቅ

#ወላጆች_እንደ_ሌላቸው_ልጆች



ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሃንስ 14፡15-18

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ያስተምራቸውና ይመራቸው ነበር፡፡ ጥያቄ ሲኖርባቸው ጥያቄያውን በትክክል ይመልስላቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እንደአባት ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸው ነበር፡፡

ኢየሱስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ በሚወሰድበት ጊዜ ግን ደቀመዛሙርቱ የኢየሱስን የአባትነት መሪነት ያጡታል፡፡ ኢየሱስ ወደሰማይ ሲወሰድ በግል እያንዳንዳቸውን አግኝቶ ሊመክራቸ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራቸው አይችልም ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስ ከምድር ከመሄዱ በፊት አባት እንደሌላቸው ልጆች ካለ ምሪትና ካለ ማፅናናት እንደማይተዋቸው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተመልሶ እንደሚመጣ ለደቀመዛሙርቱ የሚነግራቸው፡፡

አሁን መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ አለ፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በሚከተሉ ሰዎች ውስጥ ያድራል፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ያደርገው የነበረውን ማፅናትና ምሪት ሁሉ ይሰጣል፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ሊያፅናና ፣ ሊመክር ፣ ሊያስተምርና ወደ እውነት ሁሉ ሊመራ የሚችለው ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምደር ሲኖር በስጋ የተወሰነ ስለነበር የምድር ህዝብን ሁሉ በግል ሊያፅናናና ሊመራ አይችልም ነበር፡፡

አሁን መንፈስ ቅዱስ ግን በስጋ ስለማይኖርና በስጋ ስለማይወሰን ኢየሱስን የተቀበሉት ሰዎች ሁሉ ውስጥ ይኖራል፡፡ ኢየሱስን በሚከተሉት ሰዎች ሁሉ ውስጥ በመኖር ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸዋል፡፡

እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሃንስ 14፡15-18


@SelahWeekly
@SelahWeekly


#የማለዳ_ስንቅ

#እግዚአብሔርን_አመስግኑ

________________________
________________________



እግዚአብሄርን ለማመስገን ብዙ ምክኒያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን የሁሉም ሰው የጋራ ምክኒያት የሆነው አንድ ምክኒያት ነው፡፡ ሰው ሌላ ምክኒያት ቢያጣ እንኳን በዚህ ምክኒያት እግዚአብሄርን ሊያመሰግን ይገባዋል፡፡ ሰው ምክኒያት ቢያጣ እንኳን ይህ ምክኒያት እግዚአብሄርን ለማመስገን በቂ ነው፡፡

መፅሃፍም ቅዱስም ይህን ምክኒያት እግዚአብሄርን ለማመስገን ምክኒያት አድርጎ ደጋግሞ ፅፎታል፡፡

እግዚአብሄር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁለንተናው መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄር አይለወጥም ሁልጊዜም መልካም ነው፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡16-17

የመልካምነት ትርጉሙ ቢያከራክር እንኳን ለመልስ እግዚአብሄርን ማየት በቂ ነው፡፡ እግዚአብሄር የመልካምነት ማጣቀሻ (Refrence) ነው፡፡ ሰው በሚያነበው መፅሃፍ ላይ ያለን ቃል ትርጉም ባይረዳ ማጣቀሻን ይፈልግና የቃሉን ትርጉም ያያል፡፡ እንደዚሁ የመልካምነት ትርጉሙ ቢያጠራጥር እግዚአብሄር ጋር መልሱ አይታጣም፡፡

እግዚአብሄር መልካም ብቻ ሳይሆን የመልካምነትም ደረጃ መዳቢ ነው፡፡ እሱ መልካም ያለው መልካም ነው እርሱ መልካም አይደለም ያለው መልካም አይደለም፡፡ ስለ መልካምነት የመጨረሻው ወሳኝ አካል እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያርመው የለም፡፡ እግዚአብሄርም ማንንም አያማክርም፡፡

እግዚአብሄርን መልካም ስለሆነና ምንም የማይወጣለት ፍፁም መልካም ስለሆነ እግዚአብሄርን ማመስገን መልካም ነው፡፡ ሰው በምንም ነገር ቢሳሳት እግዚአብሄርን ስለማመስገኑ በጭራሽ አይሳሳትም፡፡ እግዚአብሄርን ማመስገን ምንም የሚወጣለት ነገር የለም፡፡

እግዚአብሄር መልካም ስለሆነ ምስጋና ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄርን ማመስገን ይገባል፡፡ እግዚአብሄርን ማመስገን ውበት አለው፡፡ እግዚአብሄርን ማመስገን ያማረ ነው፡፡

እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው። መዝሙር 147፡1

ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፤ መዝሙር 135፡1፣3

እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። መዝሙር 92፡1-3

ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ መዝሙር 107፡1

ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና። መዝሙር 118፡ 1



@SelahWeekly
@SelahWeekly


#የማለዳ_ስንቅ

#የመጨረሻው_ዕድል


እግዚአብሄር ሰውን ፈጥሮአል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ሃጢያትና ድካም ይረዳል፡፡

እግዚአብሄር ግን የማይቀበለውና ምንም ሰበብ የማይቀበልበት አንድ ሃጢያት አለ፡፡ ሰው ምንም ያህል ምክኒያት ቢያቀርብ ተቀባይነት የማይኖረው አንድ አመፃ አለ፡፡ ይህ ሃጢያት በእግዚአብሄር ፊት ምንም ሰበብ ተቀባይነት የማይኖረው ነው፡፡

በሃጢያት ምክኒያት ሰውና እግዚአብሄር ተጣልተው ነበር፡፡ በሰው አመፅ ምክኒያት ሰውና እግዚአብሄር ጠላቶች ነበሩ፡፡ የሰው ልጅ ከሚጠፋ የመታረቂያውን መንገድ እራሱ እግዚአብሄር አዘጋጀ፡፡ ሰው ሁሉ ወደ መዳን አንዲደርስ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 1፡16

ስለሰዎች ሃጢያት እንዲሞት እግዚአብሄር አንድያ ልጁን ኢየሱስን ወደ አለም ልኮታል፡፡ ኢየሱስ በእኛ ምትክ ሆኖ እኛ መሰቃየት የነበረብንን ስቃይ ተሰቃይቷል፡፡ እኛ መሞት የነበረብንን ሞት በመሞት ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ከፍሎልናል፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

ስለሰው ሃጢያት እግዚአብሄር ይህን ሁሉ አዘጋጅቶ ሰውን ይቅር ለማለት እየጠበቀ ሰው ግን ይህንን ባይቀበል ከዚህ በላይ መስዋእት ሊደረግለት አይቻልም፡፡ ሰው እንዳይጠፋ ያዘጋጀለትን የደህንንት መንገድ ካልተቀበለ እግዚአብሄር ካለፈቃዱ በግድ ሊያድነው አይችልም፡፡

ሰው ኢየሱስን በመቀበል ከእግዚአብሄር ጋር ታርቆ የእግዚአብሄር ልጅ መሆን ካልፈለገ እግዚአብሄር ምንም ሊያደርግለት አይችልም፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡3

ይህን ኢየሱስን መቀበል የሚፈልግ ማንም ሰው ይህን ፀሎት አብሮኝ መፀለይ ይችላል፡፡

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ ስላዘጋጀህልኝ የመዳኛ መንገድ ልጅህን ኢየሱስን ስለላክልኝና አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ የሃጢያቴን እዳ ለመክፈል እንደሞተና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን የህይወቴ አዳኝና ጌታ አድርጌ በህይወቴ ላይ እሾመዋለሁ፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን



@SelahSoft
@SelahSoft


#የማለዳ_ስንቅ


#ልባችሁን_አጥሩ

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡8

እግዚአብሄር ሲጠራንና የተስፋ ቃል ሲገባልን ሁለት ሃሳቦች በልባችን ይነሳሉ፡፡

አንደኛው እግዚአብሄርን ለማገልገል እድሉን አገኘሁ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ የሚል ሃሳብ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ህዝብ ለማገልገል እግዚአብሄር ታማኝ አደርጎ ስለቆጠረን ደስ ይለናል፡፡ ያለንን ለእግዚአብሄር ህዝብ ማካፈል እንደ እድል እንቆጥረዋለን፡፡ የእግዚአብሄር መጠቀሚያ መሆንንና እግዚአብሄርን ማገልገልን እንደ ትልቅ መብት እናየዋለን፡፡ ሰማይና ምድር የሰራው እግዚአብሄር ሊጠቀምብን

ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ስለወደደ ልባችን በደስታ ይሞቃል፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡12

እግዚአብሄር ሲጠራን በልባችን የሚነሳው ሌላኛው ሃሳብ ደግሞ በቃ አሁን እጠቀማለሁ የሚል ነው፡፡ በጥሪያችን ስም ዝነኛ መሆን ፣ በጥሪያችን ተጠቅመን እግዚአብሄ የሰጠንን ሃይልን ለፈለግነው ነገር ማዋል ፣ ተሰሚነታችንን ተጠቅመን የግል ጥቅማችንን ማሳደድ ፣ እግዚአብሄር ለአገልግሎት የሰጠንን ተቀባይነት ለራሳችን ጥቅም ማዋል ፣ ባለን ጥሪ ተጠቅመን ሀብታም መሆንና  የአግልግሎታችንን ክብር ወደ እኛ ማዞር ሃሳብ ይነሳል፡፡

እግዚአብሄር ታዲያ እንዲህ ይላል ሁለት ሃሳብ ያለችሁ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ጠራን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የሚለቀን ልባችንን ስናጠራ ብቻ ነው፡፡

ልባችን ሲጠራ እግዚአብሄርን የምናገለግለው እግዚአብሄር ብቻ ስለሆነ ብቻ ስለሆነ ይሆናል፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመጥቀም ብቻ ሲይሆናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቤት የምንሰራው ለራሳችን ቤትን ለመስራት አይሆንም፡፡ የእግዚአብሄን ህዝብ የምናገለግለው እግዚአብሄር ወደአየላቸው ተራ እንዲደርሱ በቅንነት ለመርዳት እንጂ ኑሮዋችንን ለመስራት አይሆንም፡፡ ልባችንን ስናጠራ እግዚአብሄር ወዳየልን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንለቀቃለን፡፡

ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡8


@SelahSoft
@SelahSoft


📚 #የቀን_ስንቅ

#ማለዳ_ማለዳ_አዲስ_ነው



የቆምነው ከእግዚአብሄር ምህረት የተነሳ ነው፡፡

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆቃው ኤርምያስ 3፡22-23

እግዚአብሄር ይቅር ባይ ነው ለዘላለም አይቆጣም

እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም። መዝሙር 103፡8-9

የእግዚአብሄር ምህረት ለልጅ ልጅ ነው፡፡

እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና። መዝሙር 100፡5

የእግዚአብሄር ምህረት ለዘላለም ነው፡፡

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መዝሙር 136፡1

እግዚአብሄር ስለምህረቱ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ መዝሙር 107፡1

@SelahSoft
@SelahSoft

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

269

obunachilar
Kanal statistikasi