"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢኽላስ)
ክፍል ስድስት (6)
ኻሊድ ድንገት ሳያስበው በሰሚር መምጣት ምክንያት ፖሊስ ብሎ ተነፈሰ። ይሄኔ ሰሚር በጣም ግራ ትጋብቶ በማለት ጥያቄ አቀረበለት።ይሄን ግዜ ኻሊድ ተደናግጦ ብሎ ነገሩን አድበሰበሰው። ይሄኔ ሰሚር ነገሮችን አላስተዋለምና ቀለል አድርጎ ብሎ ተሰናብቶት ወጣ። ኻሊድ አይተንፍሱ መተንፈስ እየተነፈሰ በዛ ልጅ አቅሙ በዛ ጨቅላነቱ በማያውቀው ጭራሽ በማያገባው ሁኔታ እናቱ መጥፋቷ ሳያንስ በነገሮች በጣም ተስቃየ። እጅጉን የተጨነቀው ኻሊድ በሩጫ ወደ እቤት ገባ።
እትዬ መርየም ብቻቸውን ተቀምጠው ሀሳብ አስምጧቸዋል። እያሰቡ ያሉት ስለ ሙና ነው። ሙና ትላንት ምሽት ሰሚር ክፍል ምን ፈልጋ መጣች? ለምን ነበር የመጣችው? ምን አልባት ከውስጥ ሆኜ ዝም ብላት ምን ትልነበር ብለው ግራ ይጋባሉ። መርየም የሙና እናት ናቸው ለሀዋ ግን የእንጀራ እናት የትዬ መርየም ያውድ ባሏ አቶ የሱፍ ዛሬ በህይወት የሉም። አቶ ዩሱፍ መርየምን ከማግባታቸው በፊት የሀዋን እናት አግብተው ነበር። ከሀዋ እናት ሀዋን እንደወለዱ እናትየው በምጥ ምክንያት በፈሰሳት ከፍተኛ ደም በዛው አረፈች። ከሆስፒታል ገና ሳትወጣ የሞተችው የሀዋ እናት እጅግ መልከ መልካም ሴት እንደነበረች አቶ ዩሱፍ ይተርካሉ። ሁሌም ቢሆን ስለሷ መልካምነት አውርተው የማይጨርሱት አቶ ዩሱፍ እትዬ መርየምን እንዳበሳጩ ነው። እትዬ መርየም እጅግ በጣም የሚከፋቸውና ሲያስታውሱት እንኳን የሚገርማቸው አቶ ዩሱፍ በሞት እና በህይወት መሀል ጣር ላይ ሆነው እንኳን ስለሀዋ እናት ማድነቃቸውና ማዳነቃቸውን አለመተዋቸው ነው።
.....እንዲህ ሲሉም ያስታውሱታል። አቶ ዩሱፍ ከፍተኛ ህመም አሟቸው የአልጋ ቁራኛ ሆነው ለሞት የዳረጋቸውን በሽታ እየተፋፈጉ በነበረበት በዚያ ግዜ ስብርብር ባለችና በምጣፍጥ አንደበታቸው እንዲህ ይሉ ነበር። > ይህ ቃል ከትዬ መርየም አእምሮ ውስጥ አንድም ቀን ወጥቶ አያውቅም ነበር። ሁሌም እትዬ መርየም ለምን ይሆን ዩሰፍ የሀዋን እናት እንዲ አብዝቶ ሚወደው? እኔ ቆይ ምን አጉድዬበት ነው? እይሉ ይጠይቃሉ። አቶ ዩሱፍ የሀውን እናት ካገቡ በኋላ ሀዋን ብቻ ወለዱ ከዛም ሀዋን በማሳደግ ላይ ሆነው ከ እትዬ መርየም ጋ ተዋወቁ። ከእሳቸው ጋርም ልክ እንደ ሀዋ እናት የወለዱት አንዲት ልጅ እሷም ሙናን ብቻ ነበር። ነገር ግን እትዬ መርየም ከዩሰፍ ጋ ከመጋባታቸው በፊት ገና በትዳር ላይ ሳይጣመሩ አንድ ልጅ ነበራቸው። ይህ ልጃቸው ገና በልጅነቱ ብዙ እየተስቃየባቸውና ሊያሳድጉበት ወደማይችሉት ደረጃ ሲመጣ ለማደጎ ስጡት።
እትዬ መርየም ይህ ልጃቸው ከአመታት ለማግኘት ቢፈልጉት እንኳን ሊያገኙት አልቻሉም። የማደጎ አስተዳዳሪዎች ልጁ ከፍተኛ የሆነ ጭንቅላት ስለነበረው ስኮላርሺፕ (የውጪ የትምህርት እድል) አጋጥሞት መሄዱን ነገሯቸው። በዚህም ይመስላል እትዬ መርየም ወንድ ልጅ አብዝተው ሚወዱት...በዚህም ለሰሚር ልባቸው ሚከፈተው ሁልግዜም ይሉታል። ሙና በዚህ ትቀናለች። ምክንያቱም እትዬ መርየም ሙናን ብዙ ግዜ አያሞካሿትም ብዙ ግዜ ይሰድቧታል...ይናገሯታል..አንቺ አታውቂም ታጠፊያለሽ ይሏታል። ነገር ግን የሩቅ ልጅ የሆነውን ሰሚርን ሲያዳንቁ ታስተውላለች።
ሀዋ አባቷን አብዝታ ትወድ የነበረች ለአባቷ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ ነበር። አባቷ ሲሞቱ በወጣትነቷ ከ አንድም ሁለት ግዜ እራሷን ለማጥፋት ሞክራለች። ነገር ግን አዲሱ ባሏ ሰሚር ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብ ነገሮችን ትታ ወደነበረችበት እንድትመለስ ሂወቷን መልሳ እንድትኖር ብዙ እጅግ ብዙ ረድቷታል። ለዚህም ነው አብዝታ የምትወደው....ሰሚር እና ሀዋ የተገናኙት እጅግ በሚያስገርም በሚይስደንቅ ድራማ በመሰለ አጋጣሚ ነውና ሁሌም ሁለቱ ለግንኙነታቸው ልዩ ቦታ አላቸው። ሰሚር እና ሀዋ የትገናኙት ድንገት በአንድ ምሽት ሰሚር መኪና እየነዳ በፍጥነት እያሽከረከረ ድንገት ሀዋ ትገባበታለች...ሳያስበው ክፉኝ ገጭቷት ይሄዳል። ትንሽ እንደራቀ ሰአቱ መምሸቱን ሰው ሊደርስላት እንደማይችልና በጣም ቆንጆ ለጋ ወጣት አሆኗን ሲያውቅ ብዙ ሂወት የሚጠብቃትን ይቺን ልጅ አበላሸው ብሎ ራሱን ወቀሰ። ትንሽ እንደተጓዘም አእምሮ ከለከለውና መኪናውን አንድ ዳር አቁሞ ልክ እንደ እግረኛ ገጭቷት የሄደ ሳይሆን ድንገት መንገድ ላይ እንዳገኛት መልካም ሰው አርጎ እራሱን ወደ ሆስፒታል ይዟት እሮጠ። ድንገት መኪና ገጭቷት መንገድ ላይ ወድቃ ነው ያገኘኋት ብሎ ዶክተሮቹን አሳመነ። በዚህም በፍጥነት ህክምና ተደረገላት ሀዋ ለቀናት እራሷን ስታ ሳትነቃ ከሆስፒታል ቆየች።
ሰሚር ስራውን ፈቶ እቤቱን ጥሎ እሷን ማስታመሙን ተያያዘው ለቀናት በቆየው ህክምና እየተመላለሰ በእጅጉ ተንከባከባት በልዩ እንክብካቤ አጠገቧ ሆኖ ማስታመሙን ተያይዞት ሳለ እራሷን መሳቷን ተገን አድርጎ ሁሌም ቢሆን በጆሮዋ አንድ ነገር ሹክ ይላት ነበር። እያለ ጆሮዋ ላይ ያሾካሹካል። ነገር ግን ሀዋ እራሷን ስታ የማትሰም ይምሰለው እንጂ አካሏን ማቀሳቀስ አይኗን መግለጥ አንገቷን ማዟዟር ይሳናት እንጂ ጆሮዎቿ ግን እያንዳንዱን ቃላት መስማት ይችላሉ። ሀዋ እኮ እጅግ በጣም መልካም የዋህ ሴት ናት ገና ከታመመችበት ሳትነቃ በጆሮዋ በምትሰማው ገና መልኩን እንኲን ሳታየው እዛው ነበር ይቅር ያለችው። እዛው ነበር የወደደችው።እዛው ነው ለህይወቷ ያጨችው።
አቶ ዩሱፍ ለሀዋ እና ለሙና ቀድሞ ለሚያገባ ሰው የንብረቴን ሰባ አምስት ፐርሰት አወርሰዋለሁ ትልቁን ንብረት ይወስዳል በማለታቸው ሁለቱም የባል ፍልጋ ላይ ነበሩ። የሚያፈቅሩትን የሂወታቸው ጀግና እያፋለጉ የነበሩት ሁለቱ ሴቶች ሀዋ የቀደመች ይመስላል። ይህን ሁሉ ሀሳብ በእዝነ ህሊናቸው የሚያመላልሱት እትዬ መርየም ትክዝ ብለው ስለ ድሮ በማሰብ ላይ ስሉ ድንገት ሙና አጠገባቸው ቆማ ከ ሀሳብ አባነነቻቸው። ፊት ለፊታቸው እንደ ጅብራ ተገትራ ያስደነገጣቸውን ጥያቄ ጠየቀቻቸው። ብላ ጠየቀች እውነትም ሙና ምናልባት ትልቁ መኝታ ቤት የሀዋ እና የሰሚር መኝታ ቤት ነበር የሄደችውና እዛ እትዬ መርየም ገብተው ሰሚር ወጥቶ ነው? ወይንስ እቤት ተቀያይረው ነው? ወይንስ እሱ ውስጥ ነበር? ለረጅም ደቂቃ ሙና ተመስጣበትና ተጨንቃበት የነበረው ሀሳብ ነው። ጥያቄውን ስታቀርብ እትዬ መርየም ደንገጥ አሉ።
ይቀጥላል......