የብልጽግና ሚስጥራዊ ስብሰባ መረጃ!
የዐብይ አህመድ አገዛዝ ከሰሞኑ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጉ ይታወቃል።
ስለ ትግራይ እና አማራ የቀረቡ ሃሳቦች በብልጽግና ስብሰባ ላይ የቀረበው ሀሳብ በፋኖ የደህንነት መዋቅር ተመንትፎ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው!
1ኛ. በምክክር ኮሚሽን በኩል በቶሎ በፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብነት እርቅ ይደርግ በክልል መንግስታት መካከል መግባባት በመፍጠር እና የተቋረጡ የንግድ እና መሰል ተግባራትን በክልል መንግስታት ደረጃ መስራት። ይሄን ማድረጋችን የትግራይ ሃይሎች ከፋኖ ጋር ጥምረት እንዳይፍጥር ያደርጋል። አወዛጋቢ ቦታዎች በፌደራል ቁጥጥር ስር የተዳደራሉ።
2ኛ. የትግራይ ሃይሎችን ከፌደራል መንግስቱ መካከል ያለውን አለመግባባት በማርገብ ከህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፌደራል ስልጣን በመስጠት ውጥረቱን በማላላት ጊዜ መግዛት አለብን። በተጨማሪም የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሪፎርም ላይ ስለሆነ የሚመጡት አመራሮች በአማራ ሃይሎች በኩል በቀላሉ ተቀባይነት ሊያገኙ ይችላሉና ለእኛ ጥሩ ነው።
3ኛ. በጀነራል ብርሃኑ በቀለ አማካኝነት ማይጠብሪ ላይ እንዲበተን የተደረጉ የሚሊሻ አባላት ወደ ማይጠብሪ መልሶ ማስገባት እና የብሄር ዘውግ ያለው ግጭት ማስነሳት አለብን። በተመሳሳይ በሰሜን ጎንደር ያሉ የትግራይ ዘር ሃረግ ያላቸው ላይ ተመሳሳት ግጭት ማስነሳት አለብን።
4ኛ. በሱማሊያ እና ኤርትራ መሪነት ጦርነት ሊኖር እንደሚችል መጠቆም ያስፈልጋል። ትግራይንም በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መክተት አለብን።
አማራ ክልልን በተመለከተ!
1ኛ. ለሚሊሻ እና አድማ ብተና የውጊያ አበል መጨመር
2ኛ. የፋኖ ሃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ማድረግ። ለዚህም ከፍተኛ የማዳከም ስራ በመስራት ተስፋቸው ድርድር እንዲሆን ማድረግ።
3ኛ. የሚሊሻ እና አድማብተና እና ከወረዳ በታች ያሉ አባላት እንዳይከዱ ከህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነጠሉ ማድረግ እና ህዝቡ እንዳይሸሽጋቸው ማድረግ።
4ኛ. ስለድሮን አሁን ካላቸው እውቀት የተለየ እና የተሳሳተ እነሱን አደጋ ላይ የሚያጋልጥ መረጃ ማስተጋባት
5ኛ. የካቲት 1 ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪ እንዲቀበሉ ማድረግ (ከዚህ በፊት ጥር 1 ላይ እንጀምራለን ብለው የነበረ ያልተሳካላቸው)
6ኛ. የጥር 3 ኦፕሬሽን የተሳካ እንዲሆን ለሚሊሻ እና አድማብተና ደሞዝ ቅድሚያ መስጠት።
ይቀጥላል...
©ሙሉጌታ አንበርብር
@hulumedia1