የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
ሸይኽ ሙሐመድ ብን ኢብራሒም አሊ ሸይኽ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ፡-
ጥያቄ፡- የነብዩ ሙሐመድ ﷺ መውሊድን በተመለከተ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው? ሶሃቦች ፣ ታብዕዮች እና ሌሎችም ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ሰርተውታልን?
መልስ፡- የነብዩን ﷺ መውሊድ ማክበር በዲን ላይ የተፈጸመ አዲስ ፈሊጥ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በኢስላማዊው ዓለም ማህይምነት ከተሰራጨ በኋላ ለጥመት ፣ ለብዥታ እና ለውዥንብር ጥርጊያ መንገዶች ተከፍተዋል፡፡ አይኖች ታወሩ ፣ ጭፍን ተከታይነት ጉልበት አግኝቶ ተንሰራፋ፡፡ አብዛኛው ሰው እከሌ ወደተናገረው ወይም እከሌ ወደወደደው .. እንጅ ሸሪዓዊ ወደሆኑ ማስረጃዎች ለመመለስ ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ ጸያፍ ስለሆነው የመውሊድ በዓል ከረሡል ﷺ ባልደረቦች ፣ ከታብዕዮች እንዲሁም ከታብዕዩ ታብዕይ ዘንድ አንድም የተገኘ ማስረጃ የለም፡፡
ረሡል ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي تمسكوا بها وعضوا عليها بالنوجذ ، وإياكم ومحدثات الأمور فإن كل محدثة بدعة ، وكل بدعة ضلالة"
“የእኔን ሱና ከእኔ በኋላ የቅን መሪዎችና ምክትሎቸን ሱና አደራ አጥብቃችሁ ያዙ! በመንጋጋ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! ከነገሮች አዳዲስ ፈሊጦችን አስጠነቅቃችኋለሁ! ማንኛውም አዲስ ፈሊጥ ቢድዓ ነው ፤ ማንኛውም ቢድዓ ደግሞ ጥመት ነው፡፡” (አህመድ: 17144, አቡዳውድ: 4607, ኢብኑ ማጀህ: 42)
አሁንም በተጨማሪ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد"
“በዚህ (በዲናችን) ከእርሱ የሌለን አዲስ ፈሊጥ ያመጣ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” (ቡኻሪ: 2697, ሙስሊም: 1718)
መውሊድን የሚያከብር አካል ረሡልን ﷺ ለማላቅ እና ህያው ለማድረግ አላማ አድርጎ ከሆነ ፣ ጸያፍና መጥፎ ነገሮች ከተዋሃዱበት የመውሊድ በአል ውጭ ረሡልን የሚያከብርበት ፣ የሚያልቅበት መንገድ መኖሩ የሚያጠራጥ አይደለም፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴿وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ﴾
“መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል፡፡” (አሽ`ሸርህ፡ 4)
የረሡል ﷺ መወሳት በአዛን ፣ በኢቃማ ፣ በኹጥባ ፣ በሶላቶች ፣ በተሸሁዶች ፣ በሶለዋቶች ወይም በዱዓዎች ላይ ሁሌም የሚገኝ ጉዳይ በመሆኑ አዳዲስ ፈሊጦችን መጨመሩ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ረሱል ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"البخيل من ذكرت عنده فلم يصل علي"
“ንፉግ ማለት እኔ ከእርሱ ዘንድ ተወስቸ በእኔ ላይ ሶለዋት የማያወርድ ነው፡፡” (አህመድ: 1736)
እርሳቸውን በመታዘዝ ፣ የተናገሩትን እውነት በማለት ፣ የከለከሉትን በመከልከል እርሳቸው በደነገጉት ህግ እንጅ አላህን ባለመገዛት እርሳቸውን ማላቅ ይገኛል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ረሱልን በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ከማውሳትም የላቀ ተግባር ነው፡፡
ይህ ክብረ በዓል መልካም ቢሆን ኖሮ ደጋግ የሆኑ ቀደምቶች ወይም ሰለፎች በዚህ ነገር ከእኛ የበለጠ ተሳታፊዎች ይሆኑ ነበሩ፡፡ ሰለፎቹ ለረሱል ያላቸው ውዴታ እና ክብር በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ ለመልካም ነገሮች ያላቸው ጉጉትም የላቀ ነው፡፡
የመውሊድ ባለቤቶች ጉዳይ አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች ከሚያወሱት የዘለለ አይደለም፡፡ እርሱም ሰዎች የድክመት ፣ የውርደት ባህሪዎች ሲገጥማቸው መሪዎቻቸው ሲፈጽሙት ከነበረው ትክክለኛ ተግባር በማፈንገጥ ደካማ የሆነች ነፍስ በቀላሉ ልትፈጽመው የምትችለውን እና ልፋት የማይጠይቅ በሆነው አመታዊ የማስታወሻ በአል አከባበር ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
እውነተኛው አክብሮት ማለት የሚያከብረውን አካል መታዘዝ ፣ ለእርሱ ታማኝ መሆን ፣ መልእክተኛም ከሆነ ዲኑ ልቅና የሚያገኝበትን ፣ እርሱ ያዘዘውን መተግበር ፤ ንጉስም ከሆነ ንግስናው የሚስተካከልበትን ተግባር ብቻ መፈጸም ይገባዋል፡፡ ወደኋላ ከመጡ አካላት ይልቅ ቀደምት ሰለፎች ለረሡልም ﷺ ይሁን ለሶሃቦች ያላቸው ክብር ከፍተኛ ነበር፡፡ በእንዲህ አይነት መሰል የቢድዓ ተግባር ገንዘብህን ፣ ነፍስህን መስዋእት ከማድረግም ይከለክሉ ነበር፡፡ ሰለፎች ለረሡል ﷺ የሚሰጡት ክብር በመመራትም ይሁን በመከተል የሰለፎች ጎዳና የጠፋበት ዘመን ላይ ለመሪዎቻቸው ባዶ የሆነ ልቅና ከሚሰጡ የጥመት ጎዳና ተከታዮች የተለየ ነበር፡፡
ረሡል ﷺ በማንኛውም ልቅናና ክብር ከሰዎች ሁሉ ተገቢ መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለማላቅ ብለን በዲን ላይ መጨመር ፣ መቀነስ እና መቀያየር ደግሞ ተገቢ አይደለም፡፡ የአላህን ሀቅ አሳልፈን ለረሡል ﷺ መስጠት ይህ እርሳቸውን ማላቅ ሳይሆን የእርሳቸውን ክብር መቀነስ ነው፡፡ መልካም አስተሳሰብ መኖር በዲን ላይ የሚደረግን ቢድዓ የተፈቀደ አያደርግም፡፡ አብዛኛው ከዚህ ቀደም የነበሩ ሀይማኖት ተከታዮች በዲን ላይ የሚያደርጉት ፈጠራ ከመልካም አስተሳሰብ የተነሳ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን መልካም አስተሳሰብን መሰረት በማድረግ በዲናቸው ላይ አዳዲስ ነገሮችን ከመፍጠር አልተወገዱም፡፡ በዚህ ምክንያት እምነታቸው መልእክተኞች ከመጡበት ውጭ ሆኗል፡፡ ቀደምት ወይም ሰለፎቻችን ልክ ኸለፎች (ወደኋላ የመጡት) በዲን ጉዳይ እንደተዘናጉት ቢዘናጉ ኖሮ የዲን መሰረቱ ሙሉ በሙሉ ይጠፋ ነበር፡፡
ነገር ግን ቀደምቶቹ ለእኛ ዲኑን ጠብቀው አስረክበዋል፡፡ ስለዚህ ወደዲናችን መመለስ ፣ ዲናችንን በመንጋጋ ጥርሳችን ነክሰን መያዝ በእኛ ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة