የሴቶቻችን ዩኒፎርም
የሃይ ስኩል ተማሪ የሆናችሁ ሴት እህቶቻችን፣
እንደ ዩኒፎርም እየተለበሰ ያለው አጭር "ቀሚስ " ሃይማኖታችንንና ማንነታችንን በፍፁም የሚቃረን ነውና ልብሱን በመለወጥም ሆነ በማስቀጠል (በማስረዘም) ዲናችንን ፣ ማንነታችንን እንጠብቅ ። አላህን እንፍራ!
ባለባበስ የተጀመረ ግድ የለሽነት ነገ የከበደን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ። እግራችሁን በካልሲ መሸፈናችሁ አለባበሱን ሸሪዐዊና መልካም አያደርገውም— በጭራሽ! የሰውነት ቀለም አለመታየቱ ብቻ በቂ አይደለም ። የስውነት ቅርፅ መሸፈን አለበትና! ! ዲናችንን እንጠብቅ ። ቅድሚያ ለተከበረው ዲናችን! !
ቤተሰቦች ሆይ፣ ይህንን ቁራጭ ጨርቅ በመዋጋትና ከሴቶቻችን በማስጣል፣ በማስቀየር ላይ ድርሻችንን እንወጣ!
አላህን እንፍራ ‼
ማሳሰቢያ ፣ ልብሱ ላይ ያለውን ችግር በተጠቀሰው ላይ ብቻ ማሳጠሬ አይደለም ። ለግዜው ይህንን ነጥብ ለማንሳት ፈለግኩ እንጂ።
t.me/Muhammedsirage