ነቃ ነቃ
(Mujo amin)
.
ፍቅር... የህይወት ሚዛን ነው። የአላህ ፍቅር... የነብያችን (ሰዐወ) ፍቅር... የሙስሊም ወንድምና እህት ፍቅር... የፆታ ፍቅር... ሁሉም ያስፈልገናል።
ሁሉም ሚዛኑን ጠብቆ በህይወታችን ውስጥ ሲኖር መልካም ነው። የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ግን ደግሞ በጣም ዲነኛ ለመባል ስለፆታዊ ፍቅር ሲነሳ ዝም በሉ የማለት አባዜ ብዙም አያግባባም።
ሀቢቢ እየተዋወቅን ለምን እንሸዋወዳለን? ሁሉንም ስሜት በብልህነት ማስተናገድ አለመቻል ግብዝ እንጂ ዲነኛ አያስብልም።
እኔ እና ቤቴ ግን ሴት ልጅን እናፈቅራለን። ሰሀባው ላጤ ሆኖ አላህን መገናኘትን ጠልቶ ሚስቱ በሞተች በቀናት ውስጥ አግብቷል። ላጤነት በጣም ስለሚደብር ነው። የወራዳነት መንፈስ ስላለው ነው።
አሁን አሁን ትዳርን የእስር ቤት አይነት ስዕል እየሰጠነው በአዕምሯችን ውስጥ ያልተገባ ምስል ፈጥረናል። እራሳችንን እያታለልን ነው ወገን! ዝሙት እንዲህ እያላጋ በሚቀልድብን ሰዓት ትዳር እስር ሳይሆን ነፃነት ነው። ከአመፃ መጥራት! ከወንጀል እስር መፈታት ነው!
አስበው ከንፈሯን ሀቢቢ! አስበው እቅፏን ወገን! አስቢው ደረቱን! አስቢው (ወንድ እንደማያምር የገባኝ እዚህ ጋ የማስገባው ሳጣ)... ለማንኛውም ለሴት ልጅ ትዳር ጥላ ነው። የራሷን ጎጆ የምትመሰርትበት የሷ ህይወት የሚጀምርበት ነው።
ለማግባት ፈልጋችሁ ባል ያጣችሁ ሴቶች አብሽሩ በተፃፈው ቀን ይመጣል። ጠያቂ ሲመጣ ግን አታክብዱ። አላገባሁም በሚል ጭንቀትም ወደማይሆን ትዳር አትምዘግዘጉ። አሁን ያለው የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ወንዱን እንዳሻው ጉጆ የሚመሰርትበት አቅም እንዲፈጥር አላደረገውም። በእርግጥ ይህ በወንጀላችን የመጣ ቅጣት ነው።
ልባችሁን አዘጋጁት! አላህ አዛኝ ነው። ልብሳችሁን ይሰጣችኋል። ለትዳር ያላችሁን አመለካከት ግን አስውቡ። ያ ረቢ ፍቅር! ያ ረቢ መውደድ! አቦ ያጋጥመን።
ላጤ አይዞህ ነቃ በል። እኛስ ከነቃን ቆየን።
.
@mujo_gtm