የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሳኒታይዘር ማዘጋጀት ጀመረ
የኮሮና ቫይረስን ለማከላከል በምደረገው ጥንቃቄ እጅን በአግባቡ በውሃና በሳሙና መታጠብ አልያም በሳኒታይዘር ማጽዳት አንዱ መንገድ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ተነሳ በሳኒታይዘር አቅርቦት እና ፍላጎት ላይ ክፍተት ይታያል፡፡ ይህንን ክፍተት በማየት የዩኒቨርሲቲያችን የኬሚካል ምህድስና ትምህርት ክፍል (Chemical Engineering Department) ሳንታይዘር (Hand Sanitizer) ማዘጋጀት የጀመረ ሲሆን፤ቀደም ብሎ በሙከራ ደረጃ ለተወሰኑ የስራ ክፍሎች ስሰጥ የነበረው፤ ከትላንትና /16/07/2012ዓ.ም/ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲው ማህብረሰብ በሙሉ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን ከቫይረሱ እንዲከላከል በነፃ እየታደለ ይገኛል፡፡ የትምህርት ክፍሉ እንደገለጸው ውህዱን ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ የንጥረነገሮች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ ከተገኘ፤ምርቱን ለአከባቢ ማህብረሰብ ጭምር ለማዘጋጀት ይቻላል፡፡