@sebhhobekhlotu
የዓለምን በደል
የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ
ፅድቅን ለመፈፀም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
የሰማዮች ሰማይ የማይችለው ንጉስ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
አዝ = = = = =
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረ ዳዊት በትንቢቱ
አዝ = = = = =
ልጁ በዮርዳኖስ ፅድቅን ሲመሰርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
አዝ = = = = =
እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
በእርግብ ምሳሌነት ክንፉን አሰይፎ
አዝ = = = = =
ባህር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
አለም በዛሬው ቀን አየች ይንን ምስጢር
መዝሙር
በማህበረ ቅዱሳን
" ባሕር አየች ሸሸችም፥
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ
ተራሮች እንደ ኮርማዎች ኮረብቶችም
እንደ ጠቦቶች ዘለሉ "
መዝ፲፵፬፥፩-፮
የዓለምን በደል
የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ
ፅድቅን ለመፈፀም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
የሰማዮች ሰማይ የማይችለው ንጉስ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
አዝ = = = = =
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረ ዳዊት በትንቢቱ
አዝ = = = = =
ልጁ በዮርዳኖስ ፅድቅን ሲመሰርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
አዝ = = = = =
እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
በእርግብ ምሳሌነት ክንፉን አሰይፎ
አዝ = = = = =
ባህር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
አለም በዛሬው ቀን አየች ይንን ምስጢር
መዝሙር
በማህበረ ቅዱሳን
" ባሕር አየች ሸሸችም፥
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ
ተራሮች እንደ ኮርማዎች ኮረብቶችም
እንደ ጠቦቶች ዘለሉ "
መዝ፲፵፬፥፩-፮