@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
ጥምቀት_በኢትዮጵያ_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን_ጥምቀተ_ባሕራት፡፡
፠ በኢትዮጵያ ለጨዠመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀውና ሥርዐተ ጥምቀት የተጀመረው የንግሥት ሕንደኬ በጅሮንድ አቤላክ(ባኮስ) ‹‹እነሆ ውኃ አለ!፣ ታድያ መጠመቅን ማን ይከለክለኛል?›› /የሐዋ. ፷፥፳፱-፴፮/ ብሎ በሐዋርያው ፊልጶስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡
፠ ይህ ሥርዐት ግን ተስፋፍቶ የቀጠለው በነገሥታቱ በአብርሃ ወአጽብሐ (315-351ዓ.ም.) ለቤተ መንግሥቱ ቅርብ በነበረውና ኋላ ጳጳስ በሆነው በፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ) ዘመን ነው፡፡
፠ በዓሉ ግን አሁን በምናከብረው ዓይነት ስዕላዊ በሆነ መልኩ መከበር የጀመረው ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ዜማ መስፋፋት ጋራ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (530-544ዓ.ም.) እንደሆነ ይነገራል፡፡
፠ ገዳማቱና አድባራቱም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የውኃ ምንጮች በተናጥል በመውረድ በዓለ ጥምቀትን ያከብሩ ነበር፡፡
፠ ተቀራርበው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያሳድሩ ዐዋጅ የታወጀው፥ ትእዛዝ የተላለፈው በጻድቁና በጠቢቡ ንጉሥ #ላልይብላ (1140-1180ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በዚሁ ዘመን የነበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአኵሱም በመቀለና በመርጡለ ማርያም ያሉ ጥምቀተ ባሕሮችን ባርከዋል፤ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን ደግሞ በአቡነ ተክለሃይማኖት አሳሳቢነት ሥርዐተ ጥምቀቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዐዋጅ ታውጇል፡፡
፠ እስከ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስም ታቦታቱ ዕለቱን ጠዋት ወጥተው ማታ ይመለሱ ነበር፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ታቦታቱ በዋዜማው ጥር 10 ከሰዐት በኋላ ወደ ትምቀተ ባሕር ወርደው እንዲያድሩ፤ አገሩንም በኪደተ እግር እንዲባርኩ፤ በሄዱበት መንገድም እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡
፠ ቀጥሎም ዐፄ ናዖድ ሕዝቡ ታቦታቱን አጅቦ ወደ ጥምቀተ ባሕር እንዲሄድ በዐዋጅ አስነገሩ፡፡ ይህ ሥርዐትም እስካሁን ከኛ ዘንድ ደርሷል፡፡
፠ በዘመናት ውስጥም በሃገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥምቀት በዓል ሲከበርባቸው ከነበሩ ቦታዎች ዐበይቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤
#እስራኤል_ጋዛ_ጃንደረባው_የተጠመቀበት_ቦታ
#በአኵሱም_የንግሥተ_ሳባ_መዋኛ_ ‹‹#ማይ_ሹም››
#በቅዱስ_ላሊበላ_የዮርዳኖስ_ወንዝ
#በዝዋይ ገዳማት
#በሸዋ_የአፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_ፍርድ_መስጫ_ዐደባባይ
#41ድ #ታቦታት_የሚያድሩበት_የሸንኮራ_ሜዳ ‹‹#ኢራንቡቴ_ጥምቀተ_ባሕር››
#በጎንደር_የአፄ_ፋሲል_መዋኛ_ገንዳ
#በአዲስ_አበባ_የእንጦጦ_ማርያምና_ቅዱስ_ራጕኤል_ታቦት_ማደሪያ #ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ
#በአዲስ_አበባ_የጃንሆይ_ሜዳ_ (ጃንሜዳ) ዐበይቶቹ ናቸው፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት መካከል 2ቱን እንመልከት፤
ሀ) #ጥምቀት_በኢራንቡቲ_
#ኢራንቡቲ_ጥምቀተ_ባሕር (#ሸንኮራ_ወንዝ_ዳርቻ) ፥ ምንጃር፡፡ #41_ታቦታት_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_የሚወርዱበት፡፡
ከ600 ዓመታት በላይ ያስቈጠረው፤ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ የተጀመረውና ታሪክ፣ ባህል፣ እምነትና የሀገር ወግ የሚንጸባረቁበት፤ የኢራንቡቲ ጥምቀተ ባሕር እስከዛሬም ድረስ በሃገራችን በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል በደማቅ ከሚከበርባቸው ቦታዎች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በበዓሉ ላይም እናቶች በእልልታ የታላቁን የደብረ ኤረር ተራርን አልፎ እስከሚያስተጋባ ድረስ ያደምቁታል፡፡
ከ41ዱ ታቦታት መካከል ጥቂቶቹ፤
፠ ሸንኮራ ዮሐንስ
፠ ባልጪ አማኑኤል
፠ በሳ ሚካኤል
፠ ጅማ ገብርኤል
፠ ኢቲቻ ተክለ ሃይማኖት
፠ አረካ ዋርካ ይልፋታ ሥላሴ
፠ አክላል ኪዳነ ምህረት
፠ እንጆረራ አማኑኤል
፠ ወረቀት ሀገር ቅዱስ ጊዮርጊስ
፠ ውሪ ጊዮርጊስ
፠ ክርሥቶስ ሠምራ
፠ ክራርጌ አቦ
፠ እግዚአብሔር አብ …. ይገኙበታል፡፡
ለ) #ጥምቀት_በጎንደር_
ከ44ቱ_ #ታቦታተ_ጎንደር_መካከል_ወደ_ፈጥምቀተ_ባሕር_የሚወርዱት_የሚከተሉት_8ት #ታቦታት_ናቸው፡፡
/ታቦታቱ የሚወጡት በጥር 10፣ 11፣ 12፣ 18 (ስባረ ዓፅሙ)፣ 21 (አስተርዕዮ)፣ 22 (ዑርኤል) ናቸው፡፡)
#፩ኛ) #በጥር_10፣ 11ና 12 #በጎንደር_ፋሲለደስ_መዋኛ_ገንዳ (#ቀድሞ_የሰማዕቱ_ቅዱስ_ፋሲለደስ_ቤተ_ክርስቲያን_በነበረበት ቦታ ላይ) የሚወጡ ታቦታት፤
1ኛ. ቀሃ ኢየሱስ
2ኛ. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3ኛ. ዕልፍኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ
4ኛ. ሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ (አብሮ ከቀሃ ኢየሱስ ጋር ይወጣል)
5ኛ. መንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም (መ.መ.መ)
6ኛ. አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት
7ኛ. ፊት ሚካኤል
8ኛ. አጣጣሚ ሚካኤል፡፡ ናቸው
#፪ኛ) #በጥር 10፣ 11 #በልደታ_ሜዳ_(ኮሌጅ አጠገብ) (ከአፄ ፋሲል መዋኛ ገንዳ በፊት በጥንቱ የታቦታት ማደርያ)
፠ መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም
#፫ኛ) #በጥር_18 #ጎንደር_የመምህራን_ኮሌጅ_ወደ_ጊዮርጊስ_መሄጃ_ጋር (የጥር 18 ስባረ ዓፅሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት)
፠ ርዕሰ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ
#፬ኛ) #በጥር_21 #በአዘዞ_ድማዛ_ወንዝ_አጠገብ_ (የጥር 21 የአስተርዕዮ ዕለት)
አዘዞ ሎዛ ማርያም (ድፍን ጎንደር ተሰባስቦ የአስተርእዮ ዕለት የሚያከብርበት)
#፭ኛ) #በጥር_22 #በበዓታ_ጠበል_ቤት (ጥር 22 የቅዱስ ዑርኤል ዕለት)
ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ ዑር(ራ)ኤልና በዐታ፡፡