@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
@sebhhobekhlotu
ሰላም እንዴት ናችሁ እንኳን አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም የፍቅር በዓል እንዲሆን እየተመኘሁ ዛሬ ደሞ ስለ ጥምቀት በጥቂቱ ላካፍላችሁ
ጥምቀት፦የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ አጠመቀ ዘፈቀ ነከረ ነው በዚህኛው በርባታው ጥምቀት አጥምቀ ነው የዚህ ፍች መጠመቅ መነከር መዘፈቅ ከውሀ ገብቶ መዉጣት ማለት ነው ስርዓቱም በዘፈቀደ እና እንደተፈለገ ሳይሆን የራሱ የሆነ ስርዓተ ክዋኔ አለው።
አስፈላጊነቱ
👇👇👇👇👇
👉ድኅነት(ድህነት) በጥምቀት ነው።
👉ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ያልተጠመቀ አይድንም የተጠመቀ ይድናል።
👉ከውሀና ከመንፈስ ዳግም እንወለዳለን፣እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሀና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት አይገባም።
👉በጥምቀት የኃጢአት ስርየት ይገኛል።
👉እምነት መሰረት ነው ፍጹም የሚሆነው ደሞ በጥምቀት ነው።
👉በጥምቀት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንሞታለን።
👉በጥምቀት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንነሳለን።
👉በጥምቀት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን
👉በጥምቀት አዲስ ህይወት ይገኛል።
👉በጥምቀት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን።
👉ጥምቀትን የጀመረው ማን ነው❓፦ እውነተኛዋን ጥምቀት የጀመረው ወይም የመሰረተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
👉ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛዋን ጥምቀት የመሰረተው መቼ ነው❓፦ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ተወልዶ እድሜው 30 ዓመት ያህል ሲሆን በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ መሰረተው-(ሉቃ 3፥21-23)
👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ❓፦
✝ቅዱስ ዳዊት ገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ(መዝ113፥3)
✝ዮርዳኖስ ለጥምቀት ታሪካዊ ምሳሌ ያለው መሆኑ
✝ዮርዳኖስ ለምስጢረ ሥላሴ ምስጢራዊ ምሳሌ ያለው በመሆኑ
✝በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ እንደሚገኘው ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የደበቀውን የአዳምንና የሔዋንን የዕዳ የባርነት ደብዳቤ ይደመስስ ዘንድ
✝እኛ ኦርቶዶክሶች በጌታችን የጥምቀት እለት የምንጠመቀው ከክርስቶስ ጥምቀት እረድኤት በረከት እናገኝ ዘንድ ነው
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በአጭሩ እንዲህ ነው
✝ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ዮሐንስ ግን እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባኛል አንተ ግን ወደ እኔ ትመጣለህ?ብሎ ከለከለው ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ተው እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባልና አለው።ያን ጊዜም ፈቀደለት።ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሀ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲቀመጥ አየ እነሆም ድምፅ ከሰማይ መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው አለ "(ማቴ 3፥13-17) ማር 1፥9 ሉቃ 3፥21 ዮሐ 1፥32።
የተሳተውን የተረሳውን የነጠበውን የጎደለውን በቀና መንፈስ አቃንታችሁ አንብቡ።በተረፈ በአፈ መላእክት ያሟላልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣
ወለወላዲቱ ድንግል፣
ወለመስቀሉ ከቡር ይቆየን።