Muhammed Mekonn dan repost
ወሰጢያ....
ሁሉ ሚሞግትሽ የኔ ናት እያለ
ከክልልሽ ወቶ ካንች እርቆ ሳለ
በፅንፎች መካከል ያለሽ ብቸኛ ሀቅ
የመዳኛው መርከብ የሡና መልህቅ
ለሸላይ ሽለላ ለአቅራሪ ቀረርቶ
እውቅና የማትሰጭ ለወጣ አንችን ትቶ
ከፍትሀዊ ዳኛ በፍትህ የተላክሽ
ታማኝ መልእክተኛ ለኛ ያደረሠሽ
በላጮቹ ዘንዳ በእውነት የተወደድሽ
ከዘመናት በፊት ተግብረው ያለፉሽ
ከአጉራ ዘለልነት ፈፅሞ የፀዳሽ
ጥራዝ ነጠቅነት ከቶ የማያቅሽ
ከማለባበስም በሽ ማይል የራቅሽ
ከድኩም አካሔድ ከዝቅጠት የጠራሽ
መካከል ላይ ያለሽ መዳኛ ቀጠና
የቀደምቶቻችን የደጎቹ ፋና
ካልደፈረሰው ወንዝ ከምንጭ የተቀዳሽ
አር-ረህማኑ ከላይ የመሠከረልሽ
የእዝነቱ ነቢይ በውል ያፀደቁሽ
ሁሉ የሚመኝሽ ነፍሱን ሊያስጠጋብሽ
ከጥፋት ይድን ዘንድ ሊጠለል ከጥላሽ
የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና
መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሱና
በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ
ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ
ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ
መንሀጀ-ሠለፍ ወሰጢያ እምነቴ!!!
📝✍ ⓊⓂⓊ ⓞⓗⓐⓜⓜⓔⓓ
https://t.me/AbuImranAselefy
ሁሉ ሚሞግትሽ የኔ ናት እያለ
ከክልልሽ ወቶ ካንች እርቆ ሳለ
በፅንፎች መካከል ያለሽ ብቸኛ ሀቅ
የመዳኛው መርከብ የሡና መልህቅ
ለሸላይ ሽለላ ለአቅራሪ ቀረርቶ
እውቅና የማትሰጭ ለወጣ አንችን ትቶ
ከፍትሀዊ ዳኛ በፍትህ የተላክሽ
ታማኝ መልእክተኛ ለኛ ያደረሠሽ
በላጮቹ ዘንዳ በእውነት የተወደድሽ
ከዘመናት በፊት ተግብረው ያለፉሽ
ከአጉራ ዘለልነት ፈፅሞ የፀዳሽ
ጥራዝ ነጠቅነት ከቶ የማያቅሽ
ከማለባበስም በሽ ማይል የራቅሽ
ከድኩም አካሔድ ከዝቅጠት የጠራሽ
መካከል ላይ ያለሽ መዳኛ ቀጠና
የቀደምቶቻችን የደጎቹ ፋና
ካልደፈረሰው ወንዝ ከምንጭ የተቀዳሽ
አር-ረህማኑ ከላይ የመሠከረልሽ
የእዝነቱ ነቢይ በውል ያፀደቁሽ
ሁሉ የሚመኝሽ ነፍሱን ሊያስጠጋብሽ
ከጥፋት ይድን ዘንድ ሊጠለል ከጥላሽ
የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና
መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሱና
በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ
ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ
ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ
መንሀጀ-ሠለፍ ወሰጢያ እምነቴ!!!
📝✍ ⓊⓂⓊ ⓞⓗⓐⓜⓜⓔⓓ
https://t.me/AbuImranAselefy