╔════ ❁°✿°❁ ════╗
🌏 ስለ #መውሊድ ተከታታይ ፅሁፍ🌍
╚════ ❁°✿°❁ ════╝
╭─••─═••═─•••─╮
💧 #ክፍል_አስር 💦
╰─••─═••═─•••─╯
➴➘➴➘➴➘➴➘➴
#ሰኞ እና #መውሊድ ‼️
➚➚➚➚➚➚➚
➲ #መውሊድ አክባሪዎች “ነብዩ ﷺ ሰኞን #የተወለዱበት ቀን ስለሆነ ፆመዋል፡፡ ይህም #መውሊድን (ልደታቸውን) ለማክበር #ማስረጃ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
➲ #በአላህ ፍቃድ እና እገዛ #ማስረጃ ብለው ያቀረቡት፣ #ማስረጃ መሆን እንደማይችል #በሰፊው እንየው፡፡
➲ ነብዩ (ﷺ) #ሰኞን ቀን እንደሚፆሙ በትክክለኛ #ሀዲሶች ተረጋግጧል፡፡
የሚከተሉትን ሀዲሶች እንይ
➽ #የአላህ_መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን ለምን #እንደሚፆሙ ተጠየቁ፣
➱ እሳቸውም
➳ “በዛ ቀን #ተወለድኩ፣ እናም መለኮታዊ ራእይም በዛው ቀን #መጣልኝ”
ሰሂህ ሙስሊም 1162
➽ በሌላ ዘገባ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ
➳ “ስራዎች ሰኞ እና ሀሙስ (ወደ አላህ) #ይወጣሉ፡፡ ስራዬ ፆመኛ ሆኜ #እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ”
ቲርሚዚ 747
➲ ከነዚህ ሁለት #ሀዲሶች የምንማራቸው #ትምህርቶች እንደሚከተለው ይቀርባሉ
❶ኛ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን የፆሙት #ለሶስት_ምክንያቶች ነው
⓵➭ #የተወለዱበት ቀን ስለሆነ፣
⓶➭ ቁርኣን ለእሳቸው #የወረደበት ቀን ነው፣
⓷➭ ስራዎችም ወደ አላህ #የሚወጡበት ቀን ስለሆነ እና እሳቸው ስራቸው ፆመኛ ሆነው #እንዲወጣላቸው ስለፈለጉ፡፡
➽ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የፆሙት ከላይ #በተጠቀሱት ሶስት #ምክንያቶች እንጂ ሰኞን #ስለተወለዱበት ብቻ አልነበረም፡፡
❷ኛ ከዚህ #ሀዲስ ሰሃባዎች አመት #ጠብቀው በረቢዓል አወል የነብዩን (ﷺ) ልደት #ማክበርን አልተረዱም፡፡ ሰሃባዎች ደግሞ #ለኢስላም በጣም ቅርብ፣ ኢስላምን ጠንቅቀው #አዋቂዎች እና ኢስላምን ከማንም በላይ የተረዱ #ከመሆናቸውም ጋር “መውሊድ” የሚባል በአል #አያከብሩም ነበር፡፡
❸ኛ ታቢኢን በመባል #የሚታወቁት የሰሃባ #ተማሪዎች ከዚህ ሀዲስ #መውሊድ የሚባል በዓል አለ ብለው አልተረዱም፡፡
❹ኛ አራቱ ታላላቅ #የፊቂህ_ኢማሞች
➞ አቡ ሀኒፋ፣
➟ ኢማሙ ማሊክ፣
➨ ኢማሙ ሻፊኢ እና
➠ ኢማሙ አህመድ ይህን #ሀዲስ እያወቁ፣ ሀዲሱን #መውሊድ (የነብዩን ﷺ ልደት) #ማክበር ይቻላል ለሚል #ማስረጃ አልተጠቀሙትም ፡፡
❺ኛ በዚህ #ሀዲስ የተገደበው አምልኮ #ፆም ነው፡፡ ስለዚህ #ፁሙ፡፡ ከዚህም አትለፉ፡፡ ዲኑ #ገር ነው፡፡
➴➘➴➘➴➘➴➘➴➘
➠ ነብዩ (ﷺ) የሰሩትን እንስራ ያልሰሩትን አንስራ፡፡
➲ አንዳንድ ሰዎች ይገርማሉ #ሀዲስን ትርጉሙን ያዛባሉ፣ ይጠመዝዙታል ለምን ሲባል #ቢድዓን ለማንገስ፡፡
➟ እኛ #ከሰሃባዎች በላይ አላህን
➲ አዋቂ፣
➲ ፈሪም፣
➲ አላህ ዘንድ እውነተኞችም አይደለንም፡፡ እኛ #ከሰሃባዎች በላይ ነብዩን (ﷺ) አንወድም፣ አናከብርም፣ መስዋትም አልሆንም፡፡ ስለዚህ #አደብ አድርገን እንቀመጥ፡፡
➽ እንዲህ አይነት #ጥፋቶችን ስናጋልጥ እናንተ በእድሜ #ከጠገቡት ታላላቅ
➟ ኡለማዎች፣
➨ ሙፍቲዎች፣
➠ ዶክተሮች፣
➨ ኡስታዞች ትበልጣላችሁን? ሲሉ ይጠይቃሉ
#መልሱም_ቀላል_ነው!
➽ እነዚህ እናንተ #ኡለማ ብላችሁ የምትከተሏቸው ሶዎች #ከሰሃባዎች አላህን በመፍራት፣ አላህ እና መልክተኛውን በመውደድ፣ በእውቀት ይበልጣሉን?
አይበልጡም
ስለዚህ #ሙፍቲም፣
#ዶክተርም፣
#ኡስታዝም፣
#ሙነሺድም፣
#ድቤ_መቼም አርፈው #ይቀመጡ፣ ዲን #አይበጥብጡ፡፡
ኡማውን #አይከፋፍሉ፡፡ #ሺርክ እና #ቢድዓን አያንግሱ፡፡
➲ አላህ ከሺርክ፣ ከቢድኣ፣ ከዘረኝነት የፀዳ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡
➲➳➦➲➨➟➳➳➳➦➟➨➺➲
https://t.me/AbuImranAselefy/1571https://t.me/AbuImranAselefy/1571https://t.me/AbuImranAselefy/1571➲➳➦➲➨➟➳➳➳➦➟➨➺➲