Tikvah-University dan repost
አምስት መፅሀፍትን ለአንባቢያን ያደረሰው ተመራቂ ተማሪ
አንዷለም እንዳሻው ይባላል። 👆 የ25 ዓመት ወጣትና
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቲያትር ጥበባት ተመራቂ ተማሪ ነው።
በቅርቡ ያስመረቀውን "እርግማን 2" የተሰኘ የግጥም መድብል ጨምሮ አምስት መፅሀፍትን በተለያዩ ጊዚያት ለአንባቢያን አድርሷል።
የግጥም መድብሉ "በምፀታዊ አጻጻፍ የቀረበና የኑሮ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ጉዳይ፣ ወጣትነት እንዲሁም በርካታ
ሀገራዊ ጉዳዮች የተዳሰሱበት መሆኑን" ገጣሚ አንዷለም ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።
መድብሉ ጥሩ ተቀባይነት እንዳገኘ እና ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ዕትም እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።
በዮዳሄ ማተሚያ ድርጅት የታተመው የግጥም መድብሉ፤ 111 ገፆች ያሉት ሲሆን በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል።
ገጣሚና ደራሲ አንዷለም ከዚህ ቀደም የሪከርድ ተስፋ፣ እርግማን 1፣ የክስታኔ አርማ እና አዲስ ጎዳና የተሰኙ መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አቅርቧል፡፡
@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot