#አዲሱ_የጠበቆች አዋጅ
ጠበቆች ለፓርላማ በተላከው ረቂቅ አዋጅ ውስጥ መካተት የለባቸውም ባሏቸው ድንጋጌዎች ላይ ተወያዩ
***
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንታት በፊት አፅድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው ‹‹የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ›› ረቂቅ ውስጥ ተካተው የሚገኙ ድንጋጌዎች መካተት እንደሌለባቸውና ከአዋጁ ሊወጡ እንደሚገባ መስማማታቸውን፣ የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ባደረገው ውይይት አስታወቀ፡፡
የማኅበሩ አባላት ባደረጉት ውይይት ላይ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተላከውና በቀጣይ ውይይት እንደሚደረግበት የተገለጸው ረቂቅ አዋጅ፣ ለዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች አንፃር ሲገመገም ጠንካራ ጎኖችና ሊሻሻሉ ወይም መውጣት ያለባቸው ድንጋጌዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር በሕግ እንዲቋቋም የሚፈቅድ የመጀመርያ ረቂቅ ሕግ መሆኑ ሁሉንም ያስማማና መሆንም ያለበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አዋጁ መውጣቱ በጎ ጎኖች እንዳሉት ያብራሩት የውይይቱ ተካፋዮች፣ የጥብቅናውን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር፣ ለጠበቃው ሥልጠና ለመስጠት፣ ክህሎቱን ለማሳደግ፣ ጠበቆች የጥብቅና ድርጅት (ፈርም) አቋቁመው አገልግሎቱን በጥራትና ሁሉን ባሟላ መልኩ ለመስጠት፣ ለባለጉዳዮች (ለዜጎች) ተደራሽ ለማድረግና ዋስትና ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጥብቅና ማኅበር ሕግ መሠረት አድርጎ መቋቋሙ ከውጭ ለሚመጡ ኢንቨስተሮች ጭምር ጠቀሜታ ያለው መሆኑንና በሚቋቋሙ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ የማኅበሩ አባላት አብላጫ ድምፅ በሚይዘበት ደረጃ አባል እንደሆኑ በአዋጁ መካተቱ፣ በጎ ጎን መሆኑን የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ፊልጶስ ዓይናለም ገልጸዋል፡፡
እንደ አቶ ፊሊጶስ ገለጻ፣ በአዋጁ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ድንጋጌዎች፣ ፈቃድ መስጠት፣ ማደስና እስከ መሰረዝ የሚደርሰው ሥልጣን ሲሆን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስጠት የለበትም፡፡ የቀድሞውም አዋጅ ይህንን ሥልጣን ሲሆን፣ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሰጥቶ የነበረ ከመሆኑ አንፃር፣ አሁንም በድጋሚ ተመሳሳይ መሆኑ ተገቢ አለመሆኑን አክለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ እንደ በጎ ጎን የሚታየው ሥልጣኑን በውክልና ለማኅበሩ የሚያስተላልፍ ቢሆንም፣ ማኅበሩ ግን ሙሉ ነፃነቱን እንዳይጎናፀፍ እንደሚያደርገው አስረድተዋል፡፡
አዋጁ በሌሎችም አገሮች እንደሚደረገው ማንኛውም ጠበቃ በዓመት ውስጥ የክህሎት ሥልጠና እንዲወሰድ የሚያስገድድ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ በዓመት አሥር ቀናት ወይም 80 ሰዓታት፣ በቀን ለሦስት ሰዓት መሠልጠን እንዳለበት ማካተቱ እንደሆነም አቶ ፊልጶስ ጠቁመው፣ ነገር ግን ይኼንን ማኅበሩ ወደፊት በሚያወጣቸው መመርያዎችና ደንቦች ውስጥ እንደሚቀርብ ጠቁሞ ማለፍ እንጂ፣ በአዋጅ ውስጥ መካተት እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡
ቀደም ብሎ በነበሩት ዘመናት ጠበቆች የጥብቅና ፈቃዳቸውን ለማሳደስ የሚጠበቅባቸውን ግብር መክፈል ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ክህሎቱ መመዘን እንዳለበት ማለትም ወቅታዊ ሕጎችን፣ ለውጦችንና የተሻሻሉ ሕጎችን፣ የሙግት ክህሎትን የሚያሳድጉ ሥልጠናዎች በየዓመቱ በመውሰድ ሰርተፊኬት ሲያቀርብ ብቻ ፈቃዱን እንዲያሳድስ በአዋጁ ቢደነገግም፣ መሆን ያለበት ግን አዋጁ ከፀደቀ በኋላ በሚወጡ መመርያዎችና ደንቦች ላይ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ለጠበቆች ሥልጠና የሚሰጡ ተቋማት ተመርጠው ብቃታቸው ከተገመገመ በኋላ፣ ዕውቅና ተሰጥቷቸው እንዲያሠለጥኑ ይደረጋል የሚል እምነት እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ አዋጁ ግን ስለተቋማቱ የሚለው ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡
ዋናው አከራካሪ ጉዳይ እንደሆነና ጠበቆቹ ያነሱት የግብርን ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ጠበቆቹ ገለጻ፣ ግብርን በሚመለከት በረቂቅ አዋጁ ላይ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ወደ ሚኒትሮች ምክር ቤት ከሄደ በኋላ (ወይም ሲወሰድ) የጠበቆች ማኅበር 30 በመቶ ይከፍላል ተብሏል፡፡ አባላት ደግሞ አሥር በመቶ እንደሚከፍሉ መካተቱ ተገቢ አለመሆኑን ተወያይተዋል፡፡
የጥብቅና ድርጅት (ፈርሞ) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ አገልግሎቱ የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን ገልጾ እያለ፣ ለትርፍ እንደተቋቋመ (ቢዝነስ ካምፓኒ) ቆጥሮ ያልመከረበትን ድንጋጌ ማካተቱ ተገቢ ባለመሆኑ ሊካተት እንደማይገባ በመወያየት ተመሳሳይ አቋም አሳይተዋል፡፡ ይህ በተዘዋወሪ የጥብቅና ድርጅቶች (ፈርሞች) እንዳይቋቋሙ የሚከለክል መሆኑንም አክለዋል፡፡
አገልግሎት የሚሰጥና ክህሎት የሚያዋጣ ባለሙያ፣ እንደ ትርፍ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍል ማድረግ ተገቢነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በጥቅሉ ጥብቅና የመንግሥት የጋራ አስተዳደር እንጂ የቢዝነስ ባህሪም የሌለው፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ (መንግሥት)፣ በኮሚቴ አባልነት፣ በቦርድ አባልነት የሚገባበት ሆኖ፣ አስተዳደሩ ግን ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ ለጠበቆች ማኅበር ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ሆና ስተቀላቀልም እንደ አንድ መሥፈርት ሆኖ የሚጠቅም (ፈርም መቋቋሙ) መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ሪቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመራቱን በማስታወስ፣ የተወያዩበትና መካተት አለባቸው ያሏቸውን ነጥቦች ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያደርጋቸው ውይይቶች እንደ ግብዓት ይጠቀምባቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
#ሪፖርተር