የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ያወጡት ወጪ እንዲተካላቸው ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ።
በኮቪድ-19 ምክንያት በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለኪሳራ እና ተጨማሪ ወጪ ተጋልጠዋል።
ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የኮቪድ-19 መከላከል አገልግሎቶች የሚሰጡ
ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውም ተሰምቷል።
ባለፈው ዓመት ለለይቶ ማቆያነት ያገለገሉ ዩኒቨርሲቲዎች ለጥገና የሚሆን ተጨማሪ በጀት ቢጠይቁም ምላሽ እንዳላገኙ ይገልፃሉ።
ገንዘብ ሚኒስቴርን ለጥገና የሚውል 26 ሚሊዮን ብር የጠየቀው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ፕሬዝዳንቱ ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል በሚሰጠው የኮቪድ-19 ህክምና ምክንያት ፤ የኦክስጅንና የመድኃኒት እጥረት እንደገጠመው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አያኖ በራሶ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ ለኮቪድ-19 መከላከል ባወጡት ተጨማሪ ወጪ ምክንያት የበጀት ጉድለት እንዳይገጥማቸው ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ለኮቪድ-19 መከላከል ያወጡት ወጪ እንዲተካላቸው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።
@AUSUE