Ambo university students' union


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


These channel help students to get information concerning education, journals.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Congratulations for all fresh students those placement is sent for ambo university we are happy to have you all.
Welcome home!
Office of students union

@AUSUe


የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የህክምና (Medicine) ተመዛኞች ከሚያዚያ 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple/ ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት እንደምትችሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115324185 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።

@AUSUE


Urgent.
For engineering students.
Architecture and urban planning department registration news.

@AUSUe


For fresh students pleas follow this step for collage selection online.


ቦርዱ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መመዝገቢያ ሊንክ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተዘጋጀ የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ አድርጓል። በዚህም ይህን http://www.nebe.org.et/ovrs ሊንክ በመጫን መመዝገብ እንደሚቻል ቦርዶ ገልጿል።

@AUSUE


#ማስታወቂያ

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የሆናችሁ በሙሉ በነገው ዕለት ማለትም ሚያዚያ 18 ቀን 2013 ዓ/ም በዋናው ካምፓስ በአሁኑ ሰዐት በሀገራችን የጤናው ዘርፍ ትልቅ ስጋት ስለሆነው የኮሮና ወረርሽኝ እና በሀገራችን ባሉት የደም ባንኮች ውስጥ ያለው እና በጣም እየቀነሰ የሚገኘው የደምን ቀረጢት ክምችት እጥረት ለብዙዎች ህልፈት ምክንያት እየሆነ ይገኛል።

ተማሪዎች እንደምናውቀው ደም ህይወት ነው፤በአሁኑ ሰዐት በየሆስፒታሎቹ እና በየጤና ጣቢያዎቹ ብዙ ሰዎች በደም እጥረት ምክንያት ለህልፈት እየተዳረጉ ነው።

ይህን ደግሞ ሁላችንም ደም በመለገስ መግታት ይቻላል።

በመሆኑም በነገው ዕለት በግቢያችን የደም ልገሳ እና የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ስለሚኖር ሁላችሁም በሀላፊነት እንድትታደሙ እናሳስባለን።

#ደም #በመለገስ #ህይወት #እናትርፍ።
#አሁንም #ትኩረት #ለኮሮና #ቫይረስ።

@AUSUE




Duula dhiiga gumaachuu fi Hubannoo Dhimma COVID-19 Kennuu

Dhiiga Gumaachinee, Lubbuu Haa Baraarru!!

Yuuniversitii Ambootti Gumii Barattoota Fayyaa ,Gamtaa Barattootaa Waliin Ta’uun!!
Ebla,2013
Yuun.Amboo
@AUSUE


Campaign for blood donation and Community Awareness on COVID-19 Prevention.

Donate Blood, save Life

Ambo University Health Club in Collaboration with Students' Union
April, 2021
Ambo University
@AUSUE


የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ኦክሲጅን ማምረት ጀመረ።

ሆስፒታሉ በቀን 300 ሲሊንደር ኦክሲጅን የማምረት አቅም ያላቸው ሁለት የኦክሲጅን ፋብሪካዎችን አስመርቋል።

ለፋብሪካዎቹ ግንባታ 52 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል ተብሏል።

የጥራት ደረጃውን ለማረጋገጥ በተደረገ የሙከራ ምርት ፤ 99 በመቶ ንፁህ ኦክሲጅን ማምረት መቻሉን ሆስፒታሉ ገልጿል።

@AUSUE




የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ለምርጫ 2013 ወደ ቤተሰቦቻቸው አይሄዱም❗️

"The national election registration database is now open for students to access so please be aware this for students that the election will be decided to be hold in university,no any kind of students movement for election."

Regards

@AUSUE


ኦንላይን_የመራጮች_ምዝገባ_ስርዓት_መምሪያ.pdf
2.2Mb
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል።

ቦርዱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን እንዲሁም ይህንን ሂደት ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማቅረቡ እና ምክክር እንደተደረገበት አስታውሷል።

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የመመዝገቢያ ሊንክ - http://www.nebe.org.et/ovrs

@AUSUE


የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ያወጡት ወጪ እንዲተካላቸው ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ።

በኮቪድ-19 ምክንያት በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለኪሳራ እና ተጨማሪ ወጪ ተጋልጠዋል።

ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የኮቪድ-19 መከላከል አገልግሎቶች የሚሰጡ
ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውም ተሰምቷል።

ባለፈው ዓመት ለለይቶ ማቆያነት ያገለገሉ ዩኒቨርሲቲዎች ለጥገና የሚሆን ተጨማሪ በጀት ቢጠይቁም ምላሽ እንዳላገኙ ይገልፃሉ።

ገንዘብ ሚኒስቴርን ለጥገና የሚውል 26 ሚሊዮን ብር የጠየቀው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ፕሬዝዳንቱ ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል በሚሰጠው የኮቪድ-19 ህክምና ምክንያት ፤ የኦክስጅንና የመድኃኒት እጥረት እንደገጠመው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አያኖ በራሶ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ለኮቪድ-19 መከላከል ባወጡት ተጨማሪ ወጪ ምክንያት የበጀት ጉድለት እንዳይገጥማቸው ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ለኮቪድ-19 መከላከል ያወጡት ወጪ እንዲተካላቸው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።

@AUSUE


የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለረመዳን ጾም በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል። የረመዳን ጾምን በምናከናወንበት ወቅት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን ሳንዘናጋ በመተግበር ራሳችንንና አከባቢያችንን እንድንታደግ ጥሪያችንን እያቀረብን ወሩ የሰላም የይቅርታ የፍቅር የአንድነት ጊዜ እንዲሆን እንመኛለን።

Let’s enjoy the divine season of Ramadan by filling love and peace in society! Lets’ pray that may Allah forgive us for our mistakes. Let these 30 days of fasting be the start of change in our attitudes. Have a blessed Ramadan!

ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺳﻌﻴﺪ ﻟﺠﻤﻴﻊ ﺍﻹﺧﻮﺓ ﻭﺍﻷﺧﻮﺍﺕ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ

@AUSUE


የ1442ኛው የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል !

የ1442 ኛው የረመዳን ፆም ነገ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት አሳውቋል።

ምክር ቤቱ እንደገለጸው ÷ ህዝበ ሙስሊሙ በፆም እና በጸሎት የሚየሳልፈው የረመዳን ወር ነገ የሚጀምረው ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ÷ ወሩን በመረዳዳት እንዲሁም በመተሳሰብ ከምንም በላይ ደግሞ ለሰብአዊነት ቅድሚያ በመስጠት ህዝበ ሙስሊሙ እንዲያሳልፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@AUSUE


Good morning
For all 1st year students we wish good luck.
Office of students union


#አስቸኳይ #ማሳሰቢያ

የሳይንስና ከፍተኛ ሚንስቴር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተማር ስራን ለመምራት በሚል መመሪያ(መመሪያ ቁጥር 31/2013) ባወጣው መሰረት በአሁኑ ወቅት የበሽታው አሳሳቢት መጨመሩን ተከትሎ ለድንጋጌው አፅንኦት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን እንገነዘባለን።

ስለሆነም ሁሉም የተቋሙ ተማሪዎች የፊት መሸፈኛ ጭምንብል(ማስክ) ሳትለብሱ በተቋሙ ግቢ ውስጥ መንቀሳቀስ በግቢው ህግና ደምብ መሰረት ተገቢውን ቅጣት ያስቀጣል።

በመሆኑም ተማሪዎቻችን በመማሪያ እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የፊት መሸፈኛ ጭምብል ሳትለብሱ መገኘት የማይፈቀድ ሲሆን ይህን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ተማሪ በመመሪያው መሰረት የሚቀጣ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

@AUSUE


አስቸኳይ የዕርዳታ ጥሪ!
ለወገን ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ!
***************************************************
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሜድስን ዲፓርትመንት የመጨረሻ አመት ተማሪ የሆነው ዶክተር ጎንፍ ጋማ ጫላ ባጋጠማው ከባድ የኩላሊት ህመም ምክንያት አልጋ ላይ ውለው ይገኛሉ፤ በተደረገላቸውም የህክምና ምርመራ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ስራ በማቆማቸው የዲያሊሲስ ህክምና እየተሰጣቸው ቆይተዋል፤ነገር ግን በአሁኑ ሰዐት ህክምናው ከሚጠይቀው ከባድ ወጪ አንፃር የአቅም ማነስ ስላጋጠማቸው እርዳታችንን ፈልገዋል።በመሆኑም ያለንን መልካም የሆነ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል በማሰብ ለወንድማችን እንድንደርስለት የተቻላችሁን ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉ በትህትና እንጠይቃለን።

#ነግ #በእኔ #ነው።
#የዛሬ #መልካምነት #የነገ #ስንቅ #ነው።


Are you ready to take on the world? If yes, we are here to help you do just that! Join Dereja Academy and build your soft and professional skills, allowing you to succeed in your career! Apply today and find your next step at Dereja.

🔅Apply on : Dereja.com
🔅 For more information :
Join our telegram @DerejaOfficial
🔅 Contact us : +251 966753435 , +251 978043158

#Dereja
#Findyournextstep
#YoungAfricaWorks

20 last posts shown.

5 800

subscribers
Channel statistics