Abu furayhan


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Yassin

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


✳️✳️ነሲሓ ✳️✳️( በሼይኸ አ/ሀሚድ ሀፊዘሁላህ)

ከሚዳሰሱ ነጥቦች:

🎤 በአላህ ማመን ሲባል ምን ማለት ነው??

✳️🎤ሙርጂዓዎች

✳️🎤 ኸዋሪጆች

✳️🎤ሙዕተዚላዎች

✳️🎤ጃህሚያዎች

✳️🎤ኩላቢያዎች ና ሌሎችም ተዳሰበዉታል።

ክፍል 1


✍📩ትዳር የዘገዬብሽ እህቴ ሆይ !

ትዳር ትልቅ ከሆኑ የአላህ ተኣምራቶች አንዱ ነው ።

የሚድርሽም ሆነ የሚነፍግሽ አላህ እራሱ ብቻና ብቻ ነው።

ይህን ትልቅ ተኣምር ለመታደል ለጌታሽ ያደረግሽው ሰበብ ምን ይሆን?

ኡኽታ ! ለትዳር ያለሽ ጉጉት ቢጨምርም፣ ወግ ማረግ ለመብቃት ብትቻኮይም ፣ልጆችን ለመሳምና ለማሳደግ ብታስቢም፣ ሁሉም የሚሆነው በአላህ ውሳኔ ( ቀደር) ነውና ሶብሪ ።

ከሶብርሽ ጋርም ዱኣ፣እስቲግፋር፣ተውበት፣...መልካም ኢባዳዎችን በቻልሽው አቅምሽ ፈጽሚ ።
እህቴ ሆይ አደራ የምልሽ አንድ ሃሳብ አለኝ
እሱም ፦
ለጌታሽ ያለሽን ሁስነ ዞን (መልካም ጥርጣሬ ) አደራሽን ።

ሁልጊዜ ጌታሽን በመልካም ነው መጠርጠር።

የጓደኞችሽና የእህቶችሽ ትዳር ያላማረና የተወሳሰበ አስቸጋሪ ሁኖባቸው ተመልክተሽና ሰምተሽ ይሆናል።

በዚህ ምክንያትም ትዳር ምን ያደርጋል፣ባልስ የታለ ፣ቁሜ እቀራታለሁ እያልሽ መጥፎ ሃሳቦችን አታምጭ ።

ይህ ሁሉ ሃሳብሽና ውሳኔሽ ከጌታሽ ውሳኔና ቀደር ጋር የማይስማማ ትልቅ ስህተት ነው ።

እስኪ አስቢውማ እህቴ
!ለአንች የወሰነልሽን ሪዝቅና ህይወት ለእህትሽና ለጓደኞችሽ፣ለአንች የሰጠሽን ውበትና ቁንጅና ለእህትሽና ለእናትሽኮ ፣አንችጋር ያለው ስነምግባርና ድን ለቅርብ ጓደኛሽ አላደረገውም አይደል!

ስለዚህ ልክ እንድሁ የአንችም የትዳር ህይወት በአላህ ውሳኔ እንጅ እንደ ጓደኞችሽ ወይም እንደ እህቶችሽ ላይሆን ይችላልና በጌታሽ ላይ ያለሽን መጥፎ ጥርጣሬ አስወግደሽ ከላይ እንደነገርኩሽ
ሶብረሽ፣በዱኣ፣በተቅዋ፣በኢባዳዎች... እየታገዝሽ በመልካም ጥርጣሬ የጌታሽን ውሳኔ ለመቀበል ዝግጁ ሁኚ።

ጌታዬ ሆይ! ትዳር አልባ እህቶችን መልካም የሆነ ትዳርን ወፍቃቼው ባለ ትዳሮችንም ፍቅርና መተዛዘን የተሞላበት መልካም ህይወትን አኑራቸው።


https://telegram.me/Abufurayhan


እህቴ ሆይ መች ይሁን ምትመከሪው?!
።።
አለም ላይ ያለ ህዝብ በእጁ በሰራው ኃጢያት ሰበብ ጭንቀት ውስጥ በገባበት በዚህ ኮሮኖ የአለምን ሁኔታ ሰጥ ረጭ ባደረገበት ወቅት፣ የአለም ህዝብ የመጣበት ነገር ግራ አጋብቶት መፍትሄ አጥቶለት በዋለለበት ወቅት፣ የአንድ ሀገር ህዝብ ከሌላ ሀገር ህዝብ ጋር ያለው ግንኙነት በተቋረጠበት በዚህ አስጨናቂ ወቅት፣ 24 ሰዓት ዒባዳ የሚደረግባቸው የመካና የመዲና ታላላቅ የአላህ ቤት የሆኑ መሳጂዶችን ጨምሮ በሶላት በቂርኣት የሚደምቁ የነበሩ መሳጂዶች ተዘግተው በጭርታ በተሞሉበት በዚህ ጊዜ፣ ወንድ ከወንድ ጋር ሴት ከሴት ጋር እንኳን መጨባበጥ በጥብቅ በተከለከለበት በዚህ አስደንጋጭ ወቅት፣ አንቺ ግን ዛሬም አልተመከርሺም! መስቀሉን ካንጠለጠለው፣ ኢስቲንጃ አድርጎ ከመያውቀው፣ ከዚና አልፎ በሰዶማዊነት ባህሪሽን ሁሉ ጨርሶ ቀያይሮ ስምሽ ብቻ ሙስሊም እንዲባል ከሚያደርግሽ ከሀዲ ወንድ ጋር ሻሽሽን ጠምጥመሽ እንደ መስቀሉ አንገቱ ላይ ተንጠልጥለሽ የገባበት ገደል መግባት ዛሬ ተመክረሽ ካላቆምሽ መች ይሁን ተመክረሽ የምታቆሚው?!።

ዘውትር ለሚመክሩሽና በረመዷን ወር እንኳን ወደ አላህ ከተመለሽ ብለው ተስፋ አድርገው ለሚመክሩሽ እህቶችሽ፣ የአላህና የመልእክተኛው የዚያ ከመቀበር ያዳናሽ ታላቅ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጠላት የሆነውን ከሀዲ "ወላጆቼን ፈርቼ እንጂ በጣም ስለምወደው ብወልድለት ደስ ይለኛል" ትያቸዋለሽ?!፣ በዝሙት መውለድሽ አላሳሰበሽ! ዲቃላ መውለድሽ አላስጨነቀሽም!። ወላጆችሽን የፈጠረውን ሀያሉን አምላክ፣ አለምን በአንዲት በዐይን በማትታይ ቫይረስ ያንበረከከውን፣ "ሀያላን ነን" ባዮችን አንገት ያስደፋውን፣ የሀያሎች ሁሉ ወደር የሌለውን ሀያል አምላክ፣ የንጉሳን ሁሉ ንጉስ የሆነውን አላህን ሳትፈሪ ወላጆችሽን መፍራትሽን መናገርሽ ውሸት ነው!!። ሲጀመር የነሱን ክብር የገፈፍሺው፣ የወላጅነት ሀቃቸውን አሽቀንጥረሽ የጣልሺው፣ ለውርደት የዳረግሺያቸው፣ በወጉ አሳምረው በክብር ከነ ክብረ ንፅህናሽ ሊድሩሽ እያለሙ በህገ ወጥ መንገድ (በዝሙት) ክብረ ንፅህናሽን በተራ ቦታ የጣልሺው እለት ነው!!።

እርግጥ አንቺ አሁን ሌላ አለም ላይ ነሽ!!። በስሜት ስካር ላይ ነሽ። የሚገባሽ ይህ አንገቱ ላይ የተንጠለጠልሽበት ወይም ወዳጅሽ መስሎ የተንጠለጠለብሽ፣ ህይወትሽን ብልሽትሽት ያደረገው በጌታው የካደው መሰሪ ጠላትሽ፣ የብልግና አይነት ሁሉ እንደ ሀላል የሚቆጥረው ከሀዲ ወንድ፣ በመርዛማ ምላሱ ሸንግሎሽ እንደ ፌስታል ተጠቅሞብሽ የሚጥልሽ፣ ይህን አስነዋሪ ተግባሩንም እንደ ጀብድ እየቆጠረው ከጓደኞቹ የሚሳለቅብሽ አረመኔ ከሀዲ፣ ከእለታት አንድ ቀን አስካሪ መጠጥ አቅምሶሽ በስካር ስትጃጃይ (አሁንም በስሜት ስካር ላይ ነሽ) በተሽከርካሪ አደጋ ሽባ ሆነሽ፣ ያ ሁሉ ለዝሙት መቀባባቱ መጋጌጡ ቀርቶ፣ አላህ መንቀሳቀስ እንደማትችይ አድርጎሽ ቤት ቁጭ ብለሽ ያለፈውን "ተይ ተመለሺ" እየተባልሽ ስትመከሪ እንቢ ብለሽ ያሳለፍሺውን ዘግነኝ ህይወት ማስታወስና ጥፋት መሆኑ በደንብ ገብቶሽ ቁጭ ብለሽ ያለቀሽ ቀን ነው የሚገባሽ!!። ይህም አላህ አዝኖልሽ ለተውበት እድሉን ከሰጠሽ ነው!። አለያ ግን በድንገተኛ አደጋ ሞት በበዛበት በዚህን ጊዜ ሞት ድንገት መጥቶ ጎሮሮሽን አንቆ ሲይዝሽ በስሜት ስካር ያሳለፍሺው የህይወት አለም ትዝ ብሎሽ ከስካርሽ ትነቂያለሽ!። ግን ምን ዋጋ አለው?! አንድ ኣፍታ እንኳን መልሱኝ ተውበት ላድርግ ብለሽ እንባ ቀርቶ ደም ብታለቅሺ ለሰከንድ እድሉን የማታገኚበት ከባድ ወቅት ነው!!።
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:–

حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ 🔘
لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

«አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል "ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡ በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡" (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡» አል–ሙእሚኑን 99–100

አሁን እድሉ እያለሽ ከስሜት ስካር ወጥተሽ ወደ አላህ ተፀፅተሽ መመለስ ካልቻልሽ ድንገት ሞት መጥቶ ሲይዝሽ አልያም የቂያማ ቀን ብቅ ባለ ጊዜ ቁጭቱ ምንም አይጠቅምሽም!!። አላህን ይህን የአመፅ ኮተትሽን (ወንልሽን) ተሸክመሽ ተውበት ሳታደርጊ የተዋረድሽ ሆነሽ ልትገናኚው ነው?! ወይስ ሞቶ በመቀስቀስ አላህን በመገናኘት ክደሻል?!፣ ካልነበርሽበት ከትንሿ ፈሳሽ ነገር ያስገኘሽ የሆነው ሀያሉ አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:–

قَدْ خَسِرَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِلِقَاءِ اللَّهِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَتْهُمُ السَّاعَةُ بَغْتَةً قَالُوا يَا حَسْرَتَنَا عَلَىٰ مَا فَرَّطْنَا فِيهَا وَهُمْ يَحْمِلُونَ أَوْزَارَهُمْ عَلَىٰ ظُهُورِهِمْ ۚ أَلَا سَاءَ مَا يَزِرُونَ

«እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉ በእርግጥ ከሰሩ፡፡ ሰዓቲቱም በድንገት በመጣቻቸው ጊዜ እነሱ ኃጢኣቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲኾኑ «በርሷ (በምድረ ዓለም) ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ቁጪታችን» ይላሉ፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ነገር ከፋ፡፡» አል–አንዓም 31

አህቴ ሆይ! ተይ ተመከሪና ወደ ጌታሽ አላህ ተናናሽ ሆነሽ፣ አልቅሰሽ ከወንጀልሽ ተመለሺ!! ያ ከሀዲ ሙጅሪም ድግምት ሰርቶብሽም ከሆነ ይቀራብኝ በይ!! እነዚያ በፈጠራቸው የካዱ አረመኔዎች ደጋሚ መተተኞች ናቸውና በአቅልሽ እንኳ አይመስለኝም!!!
ላ! ሀውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ: ሸዋል 14/1441 ዓ. ሂ

#join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa


https://telegram.me/Abufurayhan




قال العلامة ربيع -حفظه الله-: «انشروا للواضحين»


የከሰር ዘማን ያተራፍ እመስላን በለ ስልጤ

ሙመይዓ ይኜ ዛማን የብራገገ መሰላያን

ዮደቃ ዛማን የብራገገ መሳላያን

አለሀ ተውደቆት የቂራነ ሰብቸው

Good እኮ ነው።

https://telegram.me/Abufurayhan


ثناء العلماء على الشيخ ربيع المدخلي حفظه الله تعالى

(❶) ❍ قَـالَ العلّامــة بنُ بـازٍ رَحِمهُ الله :
《 الشيخ ربيع من خيرة أهل السنَّة والجماعة ، ومعروف أنَّه من أهل السنَّة ؛ ومعروف كتاباته ومقالاته »
[ شريط بعنوان ثناء العلماء على الشيخ ربيع ] .

(❷) ❍ قَـالَ العلّامــة الألْبَاني رَحِمهُ الله :
《 إنَّ حامل راية الجرح والتعديل اليوم في العصر الحاضر وبحقٍّ هو أخونا الدكتور ربيع ، والذين يردون عليه لا يردون عليه بعلم أبداً ، والعلم معه »
[ شريط الموازنات بدعة العصر ] .

• وقال رحمه الله :《 فهؤلاء الذين ينتقدون الشيخين -كما ذكرنا ( يعني الشيخين مقبل الوادعي وربيع المدخلي )
إما جاهل فيُعلَّم ، وإما صاحب هوى فيُستعاذ بالله من شره ، ونطلب من الله عز وجل إما أن يهديه وإما أن يقصم ظهره 》
[ س.الهدى والنور (851) ] .

(❸) قال الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله فيمن يطعن في الشيخ ربيع : «رأيُنا أنَّ هذا غلطٌ وخطأٌ عظيم، والشيخ ربيع من علماء السنة ، ومن أهل الخير ، وعقيدته سليمة ، ومنهجه قويم ، لكن لما كان يتكلم على بعض الرموز عند بعض الناس من المتأخرين وصموه بهذه العيوب »
[ شريط كشف اللثام ].

(❹) قال العلامة مقبل الوادعي -رحمه الله :
• وقال رحمه الله : « والشيخ ربيع بن هادي المدخلي فهو آيةٌ من آيات الله في معرفة الحزبيين »
[ تحفة القريب والمجيب ] .

(❺) قال العلامة محمد بن عبد الوهاب البَنَّا رحمه الله :
«أنا أقول : إنَّ ربيع هادي يحيى بن معين هذا الزمان »
[ الثناء البديع ] .

• وقال رحمه الله : « فَأَنَا أَعرِفُ السَّلَفِيَّ وَغَيرَ السَّلَفِيِّ وَأنتُم كَذلِكَ وَنَحنُ نَستَدِلُّ عَلَى سَلَفِيَّةِ الإِنسَانِ وَاستِقَامَتِهِ فِي هذَا الزَّمَانِ بَل عِندَ الأَجَانِبِ بِحُبِّ رَبِيعٍ » .
[ مسائل العلامة محمد البَنَّا ] .

(➏) قال الشيخ العلامة أحمد بن يحيى النجمي رحمه الله :
« فالذي يطعن في الشيخ ربيع هذا دليلٌ على أنَّه مبتدع ، على أنَّه يحبِّذ المبتدعين ويلمِّع أصحاب البدع »
[ فتاوى عبر الهاتف (12) ] .

(➐) قال العلامة زيد بن محمد المدخلي رَحِمهُ الله : « الردود التي قام بها الشيخ ربيع هي جهادٌ في إعلاء كلمة الحق وهي نصحٌ للمسلمين وبالأخص طلاب العلم المبتدئين ومن في حكمهم ممن ليس له عنايةٌ في التوسع في فن العقائد والمناهج والردود لئلا يقعوا في المحظورات والمحاذير » .
[ مقدمة كتاب (جماعة واحدة لا جماعات) ].

የሰለፍያፁሁፎች።ቻናልይቀላቀሉ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@AbuTolhaAhmedmusa


https://telegram.me/Abufurayhan


‏(( فـوائد عـظيمة فـي حـليب الأم ))

قـالـ العــلامة : #صـالح_الفــوزان حـفظـه الله :

ولـما للرضـاعة مـن أثـر فـي المـرتضع فقـد نـهى النبـي صـلى الله علـيه وسـلم أن تسـترضع الحمقـاء .

قـالـ ابن قـاسم رحـمه الله فـي حاشـية الـروض تعلـيقًا علـى هـذا الحـديث :

لأن للـرضاعة تأثـير ‏فـي الـطـباع.
ثـم قـال : وحكـى القـاضي أن مـن ارتضـع مـن امـرأة حمـقاء خـرج الـولد أحمـق

ومـن ارتضـع مـن سيـئة الخـلق تعـدى إلـيه، ومـن ارتضـع مـن بهيمـة كـان بليـدًا كالـبهيمة

وقـال ابن قـدامة رحمـه الله فـي المغني :

▫️فإنـه يـقال : إن الرضـاع يـغير الطـباع فكيـف ‏بأصـحاب الحـليب الصـناعي الـذي لا يـدري مصـدره ولا مـن صنـعه .

[ كتـاب تـربية الأولاد فـي ضـوء الكـتاب والـسنة : صــ (٢٨) ]

https://telegram.me/Abufurayhan


እህቴ ሐብት ንብረት እያየሽ ቁመሽ ከምትቀሪ
ዲኑን ምረጪና ትዳርን ሞክሪ
እርዚቅ ከ አሏህ ነው ፍፁም እንዳትፈሪ
ይሁንልሽ እንጂ እሱ አሏህን ፈሪ
እሱን ለማግኘት በብዙ ጠንክሪ
ድሀ ነው መባሉን አይዞሽ አትፍሪ እሽ

https://telegram.me/Abufurayhan


ሊሸይክ መሐመድ አልመድከሊይ የሆነች አለህ ይጠብው


☝️☝️☝️



https://telegram.me/Abufurayhan




أسد السنة شيخ محمد بن هادي المدخلي
سيف المسلول على المميعة المخذلة
حفظه الله تعالي ☝️☝️☝️

https://telegram.me/Abufurayhan










#እነዚህን #ተጠንቀቋናቸው #በሃገራችን
#ያሉ #መርዞች #ናቸው።

1,አቡ በከር አህመድ🚫 ምን ይላል፦
ሁላችንም የፈጣሪ ልጆች ነን ይላል።‼️

2,ያሲን ኑሩ 🚫 እንዲህ ይላል፦
ስለ መውሊድ ሲጠየቅ እንዲህ አይነት አርስቶችን አታንሱ ፕሊስ ፕሊስ መውሊድ ነው እንዴ የሚለያየን ብሎ ደረቱን ነፋብን።
ሌላ ቦታ ላይ እንዲህ ይላል ፖለቲካ ኢባዳ ነው ይላል።‼️

3,በድሩ ሁሴን 🚫እንዲህ ይላል፦
በመውሊድ ምክንያት አንከፋፈልም አንድ ነን‼️

4ካሚል ሸምሱ🚫 እንዲህ ይላል፦
የሀገራችን ሶፍዩች የተውሂድ ሰዎች ናቸው።‼️

5,አደም ካሚል 🚫 እንዲህ ይላል፦
ወላሂ ወቢላሂ ብሎ አሁን የመጣልንን እድል ነቢዩላህ ሙሳም ቢመጡ፣ ነብዩላህ ኢሳም ቢመጡ፣ ነብዩ መሐመድም(ﷺ) ቢመጡ፣ አሁን የመጣልንን እድል አናገኘውም ብሎ የነብያቶችን ክብር በአንድ ሙርተድ
ካፊር መለወጡና ክብራቸውን መጣሱ‼️

6,መሐመድ ሀሚዲን🚫 እንዲህ ይላል፦
አንዳንድ ሰዎች ደስ ባይላቸውም በሃገራችን ሁሉም አህለ ሱንና ነው ይላል።

7,ሰምሃር ተክሌ አህባሽን የምንቃወመው በፖለቲካ አጀንዳው ብቻ ነው ይላል።‼️

አላህ ከኢኽዋን በሽታ አላህ ይጠብቀን።
Ibnu Mohammed

https://t.me/Ibnumohammedseid


አደረችሁን እችን ክታብ አንብቧት የሙማይዓን ምሽግ ትበትነለች

አዳረችሁን አሰረጯት


https://telegram.me/Abufurayhan




━━━━━━━━🎀
#መልካም_ሚሰት___ምን_አይነት_ናት_ካልከኝ??

💐የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ ቁጥብና በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

🌹ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

💐ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

🌹ቤትና ንብረቱን እንዲሁም ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

💐እሱ የማይፈልገውን ሰው አትጠጋም አታስጠጋምም

🌹ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም ከቤትም አትወጣም

💐 የባሏንና የቤቷን ሚስጥር በሚገባ ትጠብቃለች

🌹 ባሏን በመልካም ነገር ላይ ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣ሲረሳ ታስታውሳለች

💐ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች

🌹ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥ እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት
በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

💐በሚያደርግላት ነገር በሙሉ ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

🌹 ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!

💐 አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች። አጠቃላይ ስራዋ በዱኒያም በአኼራ በአላህም በሰወችም ያስወድድሀል።።

ይህ ከላይ የተዘረዘሩት የያዘች መልካም ሚስት ትባላለች #አስበህዋል ? ታዳ ይችን አገኘህ ማለት ከዚህ በላይ ሪዝቅ የለምና ለዛም ነው ረሱል (ሰ.አ.ወ) መልካም ሚስት ሪዝቅ ናት ያሉህ።

🌾🌾🌾🌾ይችን መልካም ሴት(ሚስት) ለማግኘት ለትዳር መሰረት ዲን ካልተደረገ መናዱ የማይቀር ነው ትንሽ እያደገ፡፡
#በርግጥ ረሱል (ሰ.አ.ወ) ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ትገባለች ካሉ በኋላ ለዱንያም ለአኼራም ዲን ያላትን ምረጥ ብለው አበክረው ነግረውሀል እኮ። ሲሆን ሁሉም ከተገኛ እሰየው አለበለዚያ ግን ከላይ የዘረዘርኩትን አይገኝም
አላህ መልካሞችና የተግባር ሰው ያድርገን!!

أبو فريحان

https://telegram.me/Abufurayhan

20 last posts shown.

205

subscribers
Channel statistics