Forward from: 🎀ጥቂት ማስታወሻ ለሙስሊሟ እህቴ🎀
ኒቃቤ
አዎ እንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ
ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ
ድንጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ
ይመክትልኛል ዐልዩ ከቢሩ
ሰሚ ነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ
ነቢዩን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ
ይህ ነው መሰረቴ የመኖሬ አላማ
አላህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ
ነገ እንዳጭድበት የአኼራን ምንዳ
ፍጻሜዩ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ
ኒቃቤ! መማሬን አያቅብ መሰራቴን አይገታ
ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ
አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ
ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንጾ
ይህን የቸረኝ አምላኬ ምስጋና ተገባው
እኔስ ተደነቅኩኝ ለታላቅ ልእልናው!
ይቀጥላል ……
✍ bint hashim
https://t.me/Hanu_bint_hashim
አዎ እንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ
ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ
ድንጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ
ይመክትልኛል ዐልዩ ከቢሩ
ሰሚ ነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ
ነቢዩን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ
ይህ ነው መሰረቴ የመኖሬ አላማ
አላህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ
ነገ እንዳጭድበት የአኼራን ምንዳ
ፍጻሜዩ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ
ኒቃቤ! መማሬን አያቅብ መሰራቴን አይገታ
ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ
አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ
ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንጾ
ይህን የቸረኝ አምላኬ ምስጋና ተገባው
እኔስ ተደነቅኩኝ ለታላቅ ልእልናው!
ይቀጥላል ……
✍ bint hashim
https://t.me/Hanu_bint_hashim