Event Addis/ ሁነት አዲስ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


EventAddis/ሁነት አዲስ
የሁሉም ሁነቶች ደሴት!
የሙዚቃ ፣የፊልም ፣ቴአትር ፣ የቢዝነስ እና የተለዩ ሁነታዊ መረጃዎች እና ዝግጅቶች የሚቀርቡበት የናቲ ማናዬ ቻናል ነው።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም?

ጋዜጠኛ ህይወት ፍሬስብሃት እና ጋዜጠኛ ብርቱካን ሐረግወይን የተጣምሩበት አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም ምሥራብ!


ምሥራብ በግእዝ የሚታወቅ ቃል ነው። ቀጥተኛ ትርጉሙ፥ አሸንዳ፣ መዘውር፣ ውኃን ከታች ወደ ላይ አውጥቶ ወደ ታች በመርጨት የሚያጠጡት ከብረት ወይም ከዕንጨት የተሠራ መንጮረር፣ ቦይ፤ በአካላችን ውስጥ ምግብ እና መጠጥ የሚተላለፍበት መንገድ(ሠረገላ) ነው።

ከቀጥተኛ ፍቺው እንደምንገነዘበው፤ መነሻ፣ ሒደት እና መድረሻ ያለውን የፈሳሽንና የምግብን የመተላለፍ እና የመፍሰስ ሥርዓት(system) ያመለክታል።

ሎጅስቲክስም የአንድን ነገር መገኛ፣ መጓጓዣ፣ ክምችት(ክዘና)፣ አቅርቦት እና ሥርጭት ሥርዓት(ፍሰት) የሚመለከት ስለኾነ ይህ ቃል ለሥያሜነት ተመርጧል።


በዚህ ፕሮግራም የባህር የአየር የየብስ የንግድ እንቅስቃሴ የፖስታና መሰል የመላላኪያ ስልቶች የገቢና ወጪ ጭነቶች ዝርረዝር መረጃ ፤ የወደብ አጠቃቀማችን ኪራይ መርከብና ኮንቴር በአጠቃላይ የምንሸምተው ዋጋ እንዴት ተጓጉዞ እንደሚደርስልን ያትታል ፡ ዕቃ ቀሎን እጃችን የሚገባበትን የመብት ጥያቄ ያነሳል ፣ ዐለም አቀፍ አሰራርና ሁኔታዎችን ይቃኛል ፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውየሬድዮ ዝግጅት ( ነገረ ጭብጡን ሎጅስቲክስ ላይ ያደረገ ) ነው ብዙ የማታውቋቸው ሙያተኞች ትንታኔ ይሰጡንል ረቡዕ ከ8-9 በተጨማሪም እሁድ 8-9 ይቀርባል ። ዋና አዘጋጅ ሕይወት ስትሆን በco host በመኾን ብርቱካን ሐረገወይን አለች።

https://t.me/EventAddis1


በነጻ የጡት ካንሰር ምርምር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነት?


ቅዳሜ ሰኔ 11 2014 ዓ.ም የጡት ካንሰር ምርምራ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነት በግዮን ግሮቨ ጋርደን ዋከ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ ይካሄዳል።


https://t.me/EventAddis1


የመጽሐፍ ምርቃት?

የዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ "የብርሃን እናት" የተሰኘው መጽሐፍ ሰኔ 26 2014 ዓ.ም በኢትዮ ስካይላይት ሆቴል በ8:00 ይመረቃል።


https://t.me/EventAddis1


በቅዳሜ ጋዜጣና መጽሔቶች?

ቅዳሜ "ፍትህ" መጽሔት ሦሰተኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኔ 2014 ዓ.ም እትሟን ይዞ ትወጣለች።


https://t.me/EventAddis1


በቅዳሜ ጋዜጣና መጽሔቶች?

ቅዳሜ "አዲስ ማለዳ " ጋዜጣ ቅጹ 4 ቁጥር 189 ሰኔ 11 2014 ዓ.ም እትሟን ይዛ ለገበያ ትበቃለች።


https://t.me/EventAddis1


የሎሚ ሽታ ፊልም በነጻ?

በምስራቅ አፍሪቃ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል የፊልም ትርዒት ሰኔ 9 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከ10:00 ጀምሮ መክፈቻውን አድርጓል ።

ቅዳሜ ከ11:00 ጀምሮ "ሎሚ ሽታ" ፊልም በነጻ ለታዳሚው ይቀርባል ተብሏል።


https://t.me/EventAddis1


ዛሬ!

ዛሬ ሰኔ 10 2014 ዓ.ም በዋልያ መጻሕፍት የይፍቱስራ ምትኩ "በተለይ አስራ አንደኛው " መጽሐፍ በይፋ ተመርቋል።

https://t.me/EventAddis1

ለአስተያየት @Tmanaye


የሀሳብ ውይይት?

የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 11 2014 ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ዓለም ጋለሪ "አእምሮ እና ሀሳብ" በሚል የሀሳብ ውይይት ይደርጋል።


ይህን የመሰለው ውይይት ቀጣይነት ያለው ነው።


https://t.me/EventAddis1


በዚህ ሳምንት ሃይኪንግ(ጉዞ)?

የእነማን ቡድን Hiking አለው?

የፊታችን ሰኔ 12 እሁድ ካሉ የሃይኪንግ ጉዞዎች ውስጥ ለመረጃ ያህል ከላይ ተያይዞል።


https://t.me/EventAddis1


"የአዳም ቃል " ፊልምን በነጻ?

በምስራቅ አፍሪቃ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል የፊልም ትርዒት ሰኔ 9 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከ10:00 ጀምሮ መክፈቻውን አድርጓል ። ዛሬ አርብ ከ11:00 ጀምሮ "የአዳም ቃል" ፊልም በነጻ ለታዳሚው ይቀርባል ተብሏል።


https://t.me/EventAddis1


ቅዳሜ ምን አለ?

ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ በሰሜን ሆቴል የሚኖረ የኪነጥበብ ዝግጅት። መረጃው ከላይ ተያይዞ🙏

https://t.me/EventAddis1

ለአስተያየት @Tmanaye


ዛሬ ምን አለ?

ዛሬ በዋልያ መጻሕፍት የይፍቱስራ ምትኩ "በተለይ አስራ አንደኛው " መጽሐፍ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይመረቃል።


https://t.me/EventAddis1

ለአስተያየት @Tmanaye


የራዲዮ ፕሮግራሞች ጥቆማ!

የሸገር 102.1
የFm Addis 97.1
የአሐዱ ራዲዮ 94.3
የፋና 98.1

ክፍል አንድ!


ሸገር 102.1

ሸገር ሙዚቃ (በብሌን ዮሴፍ )

ከሰኞ እስከ አርብ (ማታ ከ5:00 እስከ 6:00)

እሁድ ጠዋት ከለሊቱ 12:00 እስከ 2:00

ከምሽቱ 3:00 እስከ 6:00

ምዕራፍ (በጋዜጠኛ ንጋቱ ሙሉ)

እሁድ ጠዋት (ከ2:00 እስከ 3:00)

ሸገር ካሬ

እሁድ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 5:00

ስንክሳር

እሁድ ከ6:00 እስከ 7:00

ማምሻ

ሀሙስ ከ9:00 እስከ 10:00

የቅዳሜ ጨዋታ

ቅዳሜ ከቀኑ 7:00 እስከ ምሽቱ 1:00

ፋና 98.1


ሙዚቃ እና ወግ

አርብ ከምሽቱ 3:30 እስከ 6:00

ማረፊያ

ቅዳሜ ከ5:00 እስከ 9:00

የእርቅ ማዕድ

ማክሰኞ ከ7:00 እስከ 9:00
ሀሙስ ከ9:00 እስከ 11:00


እርሶዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

ቅዳሜ ጠዋት ከ3:30 እስከ 5:00

ኢትዮፒካሊንክ

ማክሰኞ እና አርብ ከ9:00 እስከ 11:00

ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00 እስከ 6:00


አሐዱ ራዲዮ 94.3


አሐዱ መናገሻ

ቅዳሜ ከ12:00 እስከ 3:00


በጥበብ እንሻገር

ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00 እስከ 7:00

አራት ዓይን

ማክሰኞ ከረፋዱ 5:00 እስከ 6:00

አዲስ መንገድ

አርብ ከ10:00 እስከ 12:00



Fm addis 97.1

መሰንበቻ

ቅዳሜ ከ4:00 እስከ 6:00

መጽሔት ጥበብ

ቅዳሜ ምሽት ከ12:00 እስከ 2:00

ጣፋጭ ህይወት

አርብ ከምሽቱ 10:00 እስከ 12:00


ማስታወሻ : ይህ የራዲዮ ፕሮግራሞች ጥቆማ ሰዓት ቀጣይነት አለው።


https://t.me/EventAddis1

ለአስተያየት @Tmanaye


የሀገር ፍቅር ቴአትር?


"የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከ40 ቀናት በኋለ ለተመልካቾች ቴአትር ያቀርባል ተባለ

በእድሳት ላይ ከዓመት በላይ የቆየዉ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በአሁን ወቅት በሁለት ምእራፍ ሲከናወን የነበረዉ ግንባታ ተጠናቆ የርክክብ ሂደት መከናወኑን የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም ጀማል በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የህንጻ ዉስጥ ክፍልን በተመለከተ የአዳራሽ ወንበር ፣ መጋረጃ እና የመድረክ ጀርባ ስራዎች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን የመብራት ስራዎች ወደ ሀገር ዉስጥ ለማስገባት ረጅም ጊዜ በመጠየቁ ከዚህ ቀደም የነበረውን ለመግጠም መገደዳቸውን አስረድተዋል፡፡ሆኖም ቴአትር ቤቱ ትርኢት ለማሳየት በቂ ሁኔታ ላይ በመሆኑ ከ40 ቀናት በኋላ ለተመልካች ክፍት ይሆናል ያሉት ኃላፊዉ ቴአትር ለተመልካች እየቀረበ ዘመናዊ መብራቶቹ የመግጠም ሂደቱ እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡

ቴአትር ቤቱ ለተመልካች ክፍት በሚሆንበት ወቅት ከዚህ ቀደም በተመልካች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉ ሆኖም ብዙ ጊዜ ያልታዩ እንዲሁም አዳዲስ ስራዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በቴአትር ቤቱ ቅጠር ግቢ ውስጥ የነበረዉ መጠጥ ቤት በተመልካቾች ዘንድ ቅሬታ ሲፈጥር በመቆየቱ ወደ አርት ጋላሪ እንዲቀየር መደረጉን አክልዋል ፡፡

የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በአዳራሹ ሆን በቅጥር ግቢው ከዚህ ቀደም ለእይታ ምቹ ያለሆኑት ነገሮች በሙሉ በአዲስ መልክ ተቀይረው ለቴአትር አፍቃሪው ምቹ በሆነ መልኩ መዘጋጀቱን አቶ አብዱልከሪም ጀማል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። "

ዘገባው የቤቴልሄም እሸቱ ነው።


https://t.me/EventAddis1


"ቁራኛዬ " ፊልምን በነጻ?

በምስራቅ አፍሪቃ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል የፊልም ትርዒት ሰኔ 9 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከ10:00 ጀምሮ መክፈቻውን አድርጓል ። እሁድ ከ11:00 ጀምሮ "ቁራኛዬ" ፊልም በነጻ ለታዳሚው ይቀርባል ተብሏል።


https://t.me/EventAddis1


ነገ ስድስት ኪሎ ምን አለ?

https://t.me/EventAddis1

ለአስተያየት @Tmanaye


አዲስ ቴአትር?

"ላጤው ባለትዳር " የተሰኘ የቴአትር እና ፊልም ባለሞያዎችን ያጣመረ አዲስ ቴአትር ለእይታ ሊበቃ ነው።

በዳንኤል ሙሉነህ ተደርሶ በሄኖክ ብርሃኑ ፕሮዲዩሰርነት እና አዘጋጅነት ለመድረክ የሚበቃው ቴአትሩ ሰኔ 28 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር ለእይታ ይቀርባል።


https://t.me/EventAddis1


ለአስተያየት @Tmanaye


የጥበብ ቤት?

"የጥበብ ቤት" እስላማዊ የጥበብ ዝግጅት የፊታችን እሁድ ሰኔ 12 2014 ዓ.ም"የውድቀት እንባ" በሚል በአንባሳደር ቴአትር ከ2:30 ጀምሮ ይካሄዳል።
የዚህ ዝግጅት መግቢያ 150 ብር እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።



https://t.me/EventAddis1


የስዕል ትርዒት?

ጋለሪ ቶሞካ 33ኛው ዙር የስዕል ትርዒት አሰናድቷል።

ሰዓሊ ዮሐንስ ከበደ ባለተራው ሰዓሊ ነው።

መቼ? ነገ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይከፈታል።

የት? ጋለሪ ቶሞካ ( ካናዳ ኤንባሲ ፊትለፊት)


https://t.me/EventAddis1


ሂሩት አባቷ ማነው ፊልምን በነጻ?

በምስራቅ አፍሪቃ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል የፊልም ትርዒት ነገ ሰኔ 9 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከ10:00 ጀምሮ መክፈቻውን ያደርጋል። በመክፈቻው "ሂሩት አባቷ ማነው?" ፊልም በነጻ ለታዳሚው ይቀርባል ተብሏል።


https://t.me/EventAddis1

20 last posts shown.

711

subscribers
Channel statistics