የሀገር ፍቅር ቴአትር?
"የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከ40 ቀናት በኋለ ለተመልካቾች ቴአትር ያቀርባል ተባለ
በእድሳት ላይ ከዓመት በላይ የቆየዉ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በአሁን ወቅት በሁለት ምእራፍ ሲከናወን የነበረዉ ግንባታ ተጠናቆ የርክክብ ሂደት መከናወኑን የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም ጀማል በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የህንጻ ዉስጥ ክፍልን በተመለከተ የአዳራሽ ወንበር ፣ መጋረጃ እና የመድረክ ጀርባ ስራዎች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን የመብራት ስራዎች ወደ ሀገር ዉስጥ ለማስገባት ረጅም ጊዜ በመጠየቁ ከዚህ ቀደም የነበረውን ለመግጠም መገደዳቸውን አስረድተዋል፡፡ሆኖም ቴአትር ቤቱ ትርኢት ለማሳየት በቂ ሁኔታ ላይ በመሆኑ ከ40 ቀናት በኋላ ለተመልካች ክፍት ይሆናል ያሉት ኃላፊዉ ቴአትር ለተመልካች እየቀረበ ዘመናዊ መብራቶቹ የመግጠም ሂደቱ እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡
ቴአትር ቤቱ ለተመልካች ክፍት በሚሆንበት ወቅት ከዚህ ቀደም በተመልካች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉ ሆኖም ብዙ ጊዜ ያልታዩ እንዲሁም አዳዲስ ስራዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በቴአትር ቤቱ ቅጠር ግቢ ውስጥ የነበረዉ መጠጥ ቤት በተመልካቾች ዘንድ ቅሬታ ሲፈጥር በመቆየቱ ወደ አርት ጋላሪ እንዲቀየር መደረጉን አክልዋል ፡፡
የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በአዳራሹ ሆን በቅጥር ግቢው ከዚህ ቀደም ለእይታ ምቹ ያለሆኑት ነገሮች በሙሉ በአዲስ መልክ ተቀይረው ለቴአትር አፍቃሪው ምቹ በሆነ መልኩ መዘጋጀቱን አቶ አብዱልከሪም ጀማል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። "
ዘገባው የቤቴልሄም እሸቱ ነው።
https://t.me/EventAddis1