MuhammedSirage M/Nur TextPosts


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ለግጥሞች እና ለፅሁፎች የተዘጋጀ ቻናል

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: قناة السنة سفينة نوح
ابن حبــــان البُستــــي - رَحِمَهُ الله - يقول :
« العـــــــــــــاقلُ لاَ يُصــــــادِقُ المــــــتَلون ، وَلاَ يـؤاخِي المـــــــــــتَقَلب ! ».
روضة العقلاء ( 93 )
t.me/Menhaj_Salafiya


Forward from: Abdulsemed M/Nur DifferentPosts
📘 ዓቂዳ 📘

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

الحمد لله رب العالمين،    وصلى الله وسلم على رسوله (صلى الله عليه و سلم)

🔴➡ አላህ ከሰማይ በላይ፣ ከዓርሽ በላይ ለመሆኑ ማስረጃዎች።

1⃣ ክፍል 1

📖  إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ ۚ  10 :سورة فاطر

📖  መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል፡፡ [35:10]  

🔴🔵 መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል ማለት መልካም የሆነው ንግግራችን ወደ ላይ አላህ ወዳለበት ይወጣል ማለት ነው። ይህ ደግሞ በግልፅ አላህ ከሁሉም በላይ እንዳለ ያሳያል። በቋንቋን ይወጣል የሚለውን ቃል የምንጠቀመው ከላይ ወዳለ ነገር ሲሄድ ነው።

በ ዓብዱሰመድ መሐመድኑር

➖➖➖


إنا لله وإنا إليه راجعون
የሱና ወንድም ሞት ቀላል አይደለምና ብዙ ያጎድላል!
መቀመጫቸውን ሳውዲ ካደረጉትና በሰለፊያ ዳዕዋ ላይ በተለያዩ መንገዶች ጥሪን ሲያደርጉ ከነበሩ ወንድሞቻችን ውስጥ አንዱ ነበር ። በትግርኛ ቋንቋ ሰለፊያን ለመርዳት ከመታገሉ ጋር በአማርኛም የቻለውን ያህል ይሰራ ነበር ።

በደረሰበት ህመም ምክንያት ከጥቂት ወራት በፊት በሳውዲ ጂዳ ህክምና ሲደረግለት በነበረ ሰአት በቴሌግራም አናግሬው በትንሹ ተጫውተን ነበር ። ለ 3 ወራት ያህል በሽታ ላይ እንደሆነ ነገረኝ ። ህመሙ እየጠናበት እንደመጣ ከገለፀልኝ በሇላ የሚሆነውን አዋቂው አላህ ነው ነበር ያለኝ ።
በጠናበት በሽታ ላይ ሆኖ እንኳን ስለ ዳዕዋ ያወራኝና ይጠይቀኝ ነበር ። ለሰለፊ ወንድሞቹም ሰላምታን እንዳደርስለት አደራውን አደረሰኝ ።

በዛሬው እለት ሞቱን ከአንዳንድ ወንድሞች ሰማሁ ።
ውድ ወንድማችን
أبو بتول إبراهيم آدم
በአካል ባላውቀውም ሞቱን መስማቴ ለኔ ቀላል አልነበረም! የሱና ወንድሜ ፣ "የማላውቀው" ወዳጄ ፣ የሱና ወንድሜ ነውና ‼ ወዳጄ አላህ ይማርህ!

اللهم اغفر له وارحمه وأكرم نزله ووسع مدخله ونقه من الذنوب كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس ..


Forward from: M. A.
በአንፎ መርከዝ የእሁዱን ደርስ ለምትከታተሉ!
~~~~
የፊታችን ሰኞ ለሚውለው የጥምቀት በአል ከእሁድ ጀምሮ ዝግጅት ስለሚያደርጉ ከሩቅ ለሚመጡ፣ በተለይም ለእህቶቻችን ጥንቃቄ ማድረጉ የተሻለ እንደሆነ ስላመንን ደርሱን ለመሰረዝ ወስነናል።
በተጨማሪም የዚያኛውም እሁድ በመርከዙ ፕሮግራም የተነሳ ደርስ እንደማይኖር ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።
ስለዚህ ደርስ የሚኖረው ጥር 24/2012 ይሆናል ማለት ነው። መልእክቱን ላልሰሙ አሰሙልን።


Forward from: قناة السنة سفينة نوح
➡️ ሸይኽ ሙቅቢል አል ዋዲዒይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ :-
" ሰዎች በአህለ ሱና ዳዕዋ እንዲተማመኑ ያደረጋቸው በየጊዜው የሚቀያየር አለመሆኑ ነው "
ቱህፈቱል ሙጂብ ( 114 )
t.me/Menhaj_Salafiya


MuhammedSirage M.Nur G:
"ሞት"
ትናንት ያኗኗረን አብሮን የደገሰ
በቤት በመንደሩ ስቆ እንዳልነገሰ
የሱም ቀን አክትሞ ጥሎን ገሰገሰ
ያ ሁሉ አለፈና አፈር ተንተራሰ ።
እንዲያ እንዳልተሳቀ አጭቶና አግብቶ
ከብሮም እንዳልታየ ሽጦና ገብይቶ
በሄደበት መሬት ዛሬ አየንው ገብቶ።

የወጣት ጉልበቱ ላልቶና ደካክሞ
የልጅነት ወዙ ወይቦና ከስሞ
ስንቱ ሰው ተለየን አብሮን ሲስቅ ከርሞ!!

ስንቱም "ልጅ" ተለየን ጉተናው ሳይጠና
ገና እንደጀመረ የኑሮን ጎዳና
ገና ሳይደርስበት የሶስቱን ጉልቻ
ሳይደገስለት ለትዳር ጋብቻ።

ከቶ ስንቱ ሄደ ስንቱ ሰው አለቀ
የተፃፈለትን ቀን እየጠበቀ! !
ተው ወንድሜ ይብቃን ይሙት መታወሩ
በቤት በመኪና ጠምብዞ መስከሩ
ቀብሩን መዘንጋቱ በቃ ያክትምለት
በመልካም እንተካው ያለፈን ያመፅ ‘ለት!!
t.me/MSirageText


ግድ የለኝም ለዘር!

አማራ ነህ ትግሬ ወይንስ ኦሮሞ
ከቤኒሻንጉል ነህ ከአፋር ከኦሞ
ከስልጤ ብትሆን ወይም ከጉራጌ
ኤርትራ ቢያፈልቅህ ብታድግ አምባላጌ
ግድ የለኝም ከቶ ላንተ ቋንቋና ዘር
የቱን ብትናገር ከምን ብትፈጠር!
ሚዛኑ ተውሒድ ነው የነብዩ ሱና
የሚያስተሳስረን የሰለፍ ጎዳና!!
t.me/MSirageText


ማን የሚሉህ ባለጌ ነህ ?!
ማን የሚሉህ ባለጌ ነህ ማን የሚሉህ ደፋር አራጅ ?!
ታላቅ ቤቴን አቃጥለኸው ደሞ ደፍረህ በኔ ፈራጅ! !
ጉድኮ ነው!
ያውሬን ስራ ሰርተህ አድረህ ፣ ያረድከውን ጧት ስትከሰው
ግፍህ አንተን ባያጠግብህ ፣ ስትራገም ንፁሁን ሰው
አይቀፍም ፣ ግን አንተ ሰው? !

ዳሩ ላንተ ፣ እብለት ክህደት መች ሊከብድህ
ካፄዎችህ አብራክ ወ’ተህ ማረድ ግፉ ምን ሊገድህ? !

ግን ልንገርህ ???...
ባይ ባስተውል የሱ ልጅ ነህ ቁርጥ እሱን
ዘመን ብቻ ያራራቀህ ሃይ ኮፒ ነህ ርካሽ ነፍሱን! !

t.me/Muhammedsirage

(መስጅዶችን ለሚያቃጥሉና ይህን እኩይ ምግባር ለሚደግፉ እኩይ ፊታውራሪዎች )


ንፉግ አትሁን ! ንፉግነት የአይሁዶች ሱና ነው!

ወንድሜ ሆይ አርአያህ የሆኑት ታላቁ ነብይ ተጠይቀው የለኝምን የማያውቁ ቸር ነበሩ! !
ወንድሜ!
ድልን ትጎናፀፍ ዘንድ በንብረትህ ላይ የተጣለብህን ሸሪዓዊ ግዴታ ተወጣ ። አላህ በሰጠህ ፀጋ ቀኝና ግራህን ተመልከትበትና ተገቢውን መጠን በተገቢው ቦታ ላይ አሳርፍ ።
ነገን እየቃዠህ ዛሬን እትቆራመድ ! እጅህ በራስህ ላይ ንፉግ አይሁን! ለራሰህ ፈታ በል! አትሰስት! የነፍስህን ስስት ታግለህ ዘርረው!

وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡

እጆችህ ለቤተሰብና ለወገን የተፈቱና በልኩ የሚዝዘረጉ መሳሪያዎችህ ይሁኑ ። አባካኝ ሳትሆን በልኩ ቸር ሁን ። የወጪ ርእስ በተነሳ ቁጥር እያለህ የምትጨናነቅ ንፉግ አትሁን!

#### አላህ በሰጠህ ፀጋ ላይ " ላቤን ጠፍ አድርጌ ያመጣሁት !" እያልክ አትመፃደቅ! ላብህን አይደለም ደምህን ጠፍ ብታደርግ ሰባራ ሳንቲም ላታገኝ ትችላለህ — አላህ ካልወሰነልህ !

እናማ ወንድማለም! በአላህ ፀጋ ላይ አላህን አመስግን! የታዘዝከውን ፈፅምበት !
እጆችህን ወደ ኸይር የማይንቀሳቀሱ ሙታን አታድርግ! በርግጥ ማባከንንም ተጠንቀቅ!



وَلَا تَجْعَلْ يَدَكَ مَغْلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبْسُطْهَا كُلَّ الْبَسْطِ فَتَقْعُدَ مَلُومًا مَّحْسُورًا

እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና፡፡

ስስት የሙጅሪሞቹ አይሁዶች ባህሪ ነው ። ንፉግነትን ሰንቀህ እነዚህን የዘቀጡ ከሃዲያንን አትመሳሰል ። ስስት የጥንት ህዝቦችን ያወደመ ቆሻሻ ባህሪ ነው እና ተጠየፈው!
ነብዩ صلى الله عليه وسلم
እንዲህ ብለዋል
واتقوا الشح فإن الشح أهلك من كان قبلكم ...

ስስትን ተጠንቀቁ ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ( ህዝቦች) አጥፍቷልና ።
ንፉግነት ማንም ላይ አያምራም የሱና ሰው ላይ ግን እጅጉን ያስጠላል ። ከዚህ ርካሽ መገለጫ እንራቅ!

ምልእክቱ ሴቶች እህቶቻችንንም ይመለከታል ። ወንድሜ ባልኩበት ሁሉ " እህቴ"ን አስገቡበት።
አላህ ይመልሰን!
http://t.me/Muhammedsirage


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሰለምቴነት ማሸማቀቂያ አይደለም!
~
አንዳንድ ሰዎች በእምነታዊ ጉዳዮች ላይ ስሜታቸውን ለመከተል፣ ከወረዱበት ለመውረድ ፈቃደኛ ያልሆላቸውን ሙስሊም ወደ ኋላ ታሪኩ በማጠንጠን “አንተ ሰለምቴ አይደለህ? ምን ታውቃለህ?” እያሉ ሊያሸማቅቁ ይጥራሉ። የተለየ አውቀው፣ የተሻሉ ሆነው ሳይሆን እንዲሁ የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላላጨበጨበ ብቻ አንድን ሙስሊም በዚህ መልኩ ለማሸማቀቅ መሞከር ጋጠ-ወጥነት ነው።
ሰለምቴነት ክብር እንጂ ነውር አይደለም። ሰለምቴነት ገድል እንጂ ማሸማቀቂያ አይደለም። በዚህ ፈተናው በበዛበት፣ የጥፋት ሃይሎች በሚርመሰመሱበት፣ ኢስላምን የሚያጠለሹ አካላት እንደ አሸን በፈሉበት፣ እጅግ ከባባድ ማደናገሪያዎች ያለ ገደብ በሚለቀቁበት ዘመን በምንም ሰበብ ቢሆን ወደ ኢስላም የሚመጡ ሰዎች ሊከበሩ እንጂ ሊጠለሹ አይገባቸውም። ድክመትም ካለባቸው መሸፈ፞ን እንጂ ማጋለጥ አይገባም። ከቻልን ሞራል እንስጥ። ይህን ማድረግ ካቃተን በማሸማቀቅ ገፍተን እንዳናስወጣቸው እንጠንቀቅ።
ክርስቲያን ወይም አይሁድ የነበረ ሰውኮ ወደ ኢስላም ቢገባ በእጥፍ እንደሚመነዳ ነብዩ ﷺ ተናግረዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] አልኢማም አልቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሐቸው بَابُ فَضْلِ مَنْ أَسْلَمَ مِنْ أَهْلِ الكِتَابَيْنِ የሚል ርእስ እንዳሰፈሩ እናስተውል። ‘ፈድል’ ማለት ልቅና፣ ብልጫ ማለት ነው። ነብያችን ﷺ ለሮማው ንጉስ ሒረቅል በፃፉት ደብዳቤ ላይ ወደ ኢስላም ሲጠሩት ምን ነበር ያሉት?
أَسْلِمْ تَسْلَمْ، يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ
“ስለም። ትድናለህ። አላህ ምንዳህን #ሁለት_ጊዜ ይሰጥሀል።” [ቡኻሪና ሙስሊም] ይሄ መልእክት በሒረቅል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። የኢብኑ ሐጀርን ማብራሪያ ይመልከቱ። [ፈትሑል ባሪ፡ 8/221]
በነገራችን ላይ አንድ ካፊር ወደ ኢስላም ከገባ ከመስለሙ በፊት ሲፈፅማቸው የነበሩ መልካም ስራዎች ይታሰቡለታል። ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ረዲየላሁ ዐንሁ “በዘመነ ጃሂሊያ ስፈፅማቸው ስለነበሩት ዒባዳዎች፤ ሶደቃ፣ ባሪያ ነፃ ማውጣት፣ ዝምድናን መቀጠል በተመለከተ ንገረኝ እስኪ። ምንዳ ይኖራቸዋልን?” ብለው ነብዩን ﷺ ቢጠይቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱላቸዋል፡-
أَسْلَمْتَ عَلَى مَا أَسْلَفْتَ مِنْ خَيْرٍ
“ካሳለፍከው መልካም ስራ ጋር ነው የሰለምከው።” [ሶሒሕ ሙስሊም]
ልብ በል! ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ከመካ መኳንንት የነበሩ ሲሆን በድር ላይ ከቁረይሾች ጋር ተሰለፈው ጦርነቱን ተካፍለዋል። አላህ ሲያድላቸው እንደ አጋሪ ጓደኞቻቸው በድር ላይ ሳይገደሉ በመትረፋቸው ኋላ ላይ ሰልመዋል። ለዚህም ነበር “የበድር ቀን ከመገደል ባተረፈኝ ጌታ ይሁንብኝ” እያሉ ይምሉ የነበሩት።
ወንድሜ ሆይ!
1. እስኪ የነ ዑመርንና ሌሎችም በጀነት የተመሰከረላቸውን ሶሐብዮች ታሪክ እናንብብ። ከነዚያ ታላላቅ የኢስላም ፈርጦች ውስጥ ቀድሞ ጣኦት አምላኪ የነበሩትኮ እጅግ በርካታ ናቸው።
2. እስኪ የነ ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም፣ የነብያችን ﷺ ሚስት ሶፍያን ታሪክ እናገላብጥ። ከነዚያ እንቁ ሶሐብዮች ውስጥ ቀድሞ አይሁድ የነበሩት ብዙ ናቸው።
3. እስኪ የነ ሰልማኑል ፋሪሲ፣ ዐዲይ ኢብኑ ሓቲምና መሰል ሶሐቦችን ታሪክ እንፈትሽ። አዎ ከነዚያ ወደር የለሽ የኢስላም ጀግኖች ውስጥ ከመስለማቸው በፊት በክርስትና ውስጥ ያለፉ ነበሩ።
4. ከሶሐቦች ጊዜ ወዲህም ታሪክ የሰሩ፣ ለኢስላምና ለሙስሊሞች በዋጋ የማይተመን ውለታን የዋሉ በርካታ ሰለምቴዎች አልፈዋል።

ልብ በል ወንድሜ! ልብ በይ እህቴ! ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት እንጂ የማንም ግላዊ ንብረት አይደለም። ኢስላም ለሰው፣ ለጂኑ ባጠቃላይ የቀረበ አምላካዊ መድህን እንጂ ያሰኘንን የምናስገባበት፤ የደበረንን የምናስወጣበት ያባታችን ግቢ አይደለም። ኢስላም ልክ ቄሶች “ውጉዝ ከመ አሪዮስ!” ብለው እንደሚያባርሩት ሸይኾችም እንዳሻቸው የሚፈርዱበት ቀልደኛ ቀኖና የለውም። ስለዚህ ወንድሜ! እስልምናን ከአባት ከአያት የወረስከው አንተ፣ በኢስላም ላይ ከሰለምቴው የተለየ የባለቤትነት መብት የለህም። ከአላህ ዘንድ ያለህ ደረጃ ከፍ የሚለው በተቅዋህ ብቻ ነው። ለሰለምቴው ኢስላምን የሰጠው የፈጠረው ጌታ እንጂ እኔ ወይም አንተ አይደለንም። እኛ ይህን የጌታ ፀጋ አከፋፋዮች አይደለንም።
ምናልባት “በሰለመ በማግስቱ ፈትዋ ካልሰጠሁ ብሎ የሚገላገል ሰለምቴስ ዝም ይባል ወይ?” የሚል ሊኖር ይችላል። ይሄ ሌላ ርእስ ነው። እያወራሁ ያለሁት ሰለምቴነትን ለማንቋሸሻነት ስለሚጠቀሙ አካላት ነው። የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላልፈሰሰ ብቻ “እሱኮ ሰለምቴ ነው?” በማለት ለማንጓጠጥ መሞከር ምን ማለት ነው? እስኪ አስቡት! በሚያጋጥሙ አንዳንድ አለመግባባቶች የተነሳ “እሱኮ መስለሙንም እንጃ!”፣ “እሱኮ የሰለመ ጊዜ ቄሶች በደስታ እንኳን ሄደልን ያሉት ነው”፣ “እሱኮ እንደገና ወደ ክርስትና ሳይመለስ አይቀርም”፣ “እሱኮ ሶላት አይሰግድም"፣ "እሱኮ ውዱእ ሲያደርግ ታይቶ አይታወቅም"፣ "እሱኮ ይሰክራል …” ወዘተ በሚሉ እጅግ ሰቅጣጭና ፀያፍ ውንጀላዎች በሃሰት የሚወ፞ነጀል ሰለምቴ ምን እንደሚሰማው አስቡ እስኪ!! በተጨባጭ የተከሰቱ ሃሰተኛ ውንጀላዎችን ነው በምሳሌነት የጠቀስኩት። ተወንጃዮቹ ደካሞች ቢሆኑ ኖሮ በቀላሉ ወደ ኩፍር ተገፍተው ከኢስላም በሸሹ ነበር። ግና ኢስላም ማለት የነዚህ ዋልጌዎች የግል ንብረት እንዳልሆነ ጠንቅቀው ማወቃቸው በጃቸው። ግና ሰዎቹን ከማወቃቸው በፊት ኢስላምን ማወቃቸው ጠቀማቸው። እንጂ እንደዋዛ አኩርፈው በበረገጉ ነበር።
ወላሂ! አንድ ስንት ስራ የሰራ ወንድም ፈፅሞ ይዋሻሉ ብለን በማንገምታቸው ሰዎች በተደጋጋሚ በመወ፞ንጀሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች እስልምናውን እስከሚጠራጠሩት የደረሱበት ሁኔታ በተጨባጭ አውቃለሁ። መነሻው ግን የእነዚያ ታማኞች የመሰሉን ሰዎች ክፋት ነበር።
በተረፈ ሰለምቴ ሆነው ስንቶችን ቁጭ አድርገው እየገሩ ያሉ ኡስታዞች አሉ?! ሰለምቴ ሆነው ለስንቶች መስለም ሰበብ የሆነ ስራ ላይ በሰፊው የዘመቱ አሉ?! ካረገዙ በኋላ በባሎቻቸው ተከድተው ብዙ ፈተና ቢደርስባቸውም ከነ ችግራቸው በኢስላማቸው ላይ እንደፀኑ ያሉ ስንት ሰለምቴዎች አሉ?! ወንድ ወይም ሴት ተከትለው ስንቶች በሚከፍሩበት ዘመን ለኢስላም ሲሉ ከቤተሰብ የተቆራረጡ፣ ትዳራቸውን የበተኑ ስንት ቆራጥ ሰለምቴዎች አሉ?! ነባር ሙስሊሞች በእርዳታ በቆሎ እምነታቸውን በሚቀይሩበት ምድር ለኢስላም ሲሉ ሁለ ነገራቸውን አጥተው ለእለት ጉርስ የተቸገሩ ስንት ፈተና ያልበገራቸው ሰለምቴዎች አሉ?!

ደግሞም አላዋቂ ሰለምቴ እውቀት በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ያላቅሙ ገብቶ ካገኘን ብቃቱ ካለን በአደብ ማስተማር እንጂ ሰለምቴነቱን ለማሸማቀቂያ መጠቀም፣ ሰለምቴነቱን እንደ ነውር በመቁጠር በየደረሱበት ማማት የለየለት ብልግና ነው። መሀይም የሆነ ሰው ሰለምቴም ባይሆን ያላቅሙ እንዲያወራ የተሰጠው የተለየ ስልጣን ወይም መብት የለውም። ስለዚህ ሰለምቴው በተለየ የሚኮነንበት ምክንያት ምንድነው? ሰለምቴ ሆኖ ከብዙዎቻችን የተሻለ ግንዛቤ ያለው ስንት ሰው አለ? ከውልደት እስከ እርጅና እድሜውን ኢስላም ውስጥ አሳልፎ አሊፍ ትቁም ትጋደም የማያውቅ እልፍ አእላፍ ህዝብስ የለም ወይ? እውቀትኮ በመማር እንጂ በውልደት የሚገኝ አይደለም። “ሸንበቆ አስር አመት ውሃ ውስጥ ቢቆይ አዞ አይሆንም” ይባላል። ለውጥ ከአላህ እገዛ ጋር በጥረት እንጂ በምኞትም በጉራም አይገኝም።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 01/2012)


Forward from: MuhammedSirage M.Nur.
ታመናል በጠና!

ውጫችን ተውቦ በሱና አሸብርቆ
የሚያስደምም ሆኖ ዟሂራችን ደምቆ

ቀልብ ካልረባማ ከተቆራመደ
የድብቅን ወንጀል ከተለማመደ

ከባድ አደጋ ነው ታመናል በጠና
ፈውሱን እንፈልገው ከቁርአን ከሱና

ጀግና መስለን ውለን በቀን በጠራራ
ሌቱን ከገፋንው ከኢብሊሱ ጋራ
ምኑን ተከተልንው የነብዩን ስራ?!
ልባችን ደካክሞ ባጋንነቶች ጭፍራ!

ይብቃን አረ ይብቃ እንዲህ መዳከሩ
በድብቅ ወንጀሎች ሌት ቀን መነከሩ
መንገዱን እንጀምር በዲን በመስመሩ!!


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አኽጦል እና አሻዒራ
~~~~~~~~~~~
አሽዐርዮች ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር እንደሆነ አያምኑም። ለዚህ ከንቱ እምነት ያበቃቸው ስለ አላህ የንግግር ‘ሲፋ’ ያላቸው የተዛባ እምነት ነው። የአህሉ ሱና አቋም አላህ በፈለገ ጊዜ በፈለገው ሁኔታ ይናገራል የሚል ሲሆን እነሱ ግን የአላህ ንግግር የሚስሰማ፣ ሲፈልግ የሚናገረው፣ ሲፈልግ የሚያቋርጠው እንደሆነ አያምኑም። ይልቁንም መጀመሪያም መጨረሻም የሌለው፣ አንድ ወጥ የሆነና የማይቋረጥ፣ ድምፅና ፊደል የሌለው በነፍሱ ውስጥ ያለ ውስጣዊ ንግግር ነው ይላሉ።
ይህ “ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም” የሚለው ዐቂዳቸው ሲነሳ አንዳንድ ጀማሪ ደጋፊዎቻቸው እየዋሸንባቸው ይመስላቸዋል። ነገር ግን የታላላቅ ሰዎቻቸውን ኪታብ የተመለከተ በቀላሉ የሚያገኘው ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ በአላህ ፈቃድ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ። ለጊዜው የፈለግኩት ከአኽጦል ጋር ያላቸውን ቁርኝት መግለፅ ብቻ ነው።
አኽጦል የታወቀ ገጣሚ ነው። በሃይማኖቱ ደግሞ ክርስቲያን። በመሰረታዊ የዐቂዳ ጉዳይ ቁርኣንና ሐዲሥ ማስረጃ አይሆኑም የሚሉት አሽዐርዮች በሚያሳፍር ሁኔታ ግን የዚህን ቆሻሻ ገጣሚ ንግግር በዐቂዳ ጉዳይ ደጋግመው ሲያጣቅሱ ይታያሉ። ለምሳሌ፡-

{አንደኛ፡- “ኢስተውላ”}

“ኢስተዋን” “ኢስተውላ” (ተቆጣጠረ) ሲሉ የሚያጣቅሱት
قد استوى بشر على العراق...
የሚለው የዚህን ክርስቲያን ስንኝ ነው።

ሁለተኛ፡- "የድ/ እጅን በፀጋ ወይም በሃይል ሲተረጉሙ

ለአላህ እጅ መኖሩን ሲያስተባብሉ ማስረጃ የሚያደርጉት
أعاذل أن النفس في كف مالك إذا ما دعا يوماً أجابت بها الرسلا
የሚለው ስንኝም የዚሁ ሰውየ ስራ እንደሆነ አሽዐርዩ ኢብኑ ፉረክ መስክሯል። [ሙሽኪሉል ሐዲሥ፣ ኢብኑ ፉረክ፡ 235]

ሶስተኛ፡- "ለነፍሳዊ ንግግር"

ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም ለሚለው አቋማቸው የሚያጣቅሱት
إن الكلام لفي الفؤاد وإنما ... جعل الكلام على اللسان دليلا
የሚለው ማስረጃቸውም የዚሁኑ ሰውየ ስንኝ እንደሆነ አሽዐርዮች እራሳቸው አስረግጠዋል። [ተብሲረቱል አዲላህ፡ 118] [ሸርሑል ዐቃኢዲ ነስፊያ፡ 54]
“ንግግር ማለት በልብ ውስጥ የሚታሰበው ነው። ከምላስ የሚወጣው ያን አመላካች እንጂ በሐቂቃ ንግግር አይደለም” ማለቱ ነው በግርድፉ። ቁርኣንና ሐዲሥን ጥለው ከዚህ ክርስቲያን ጋር ምን እንዳጣበቃቸው ግራ የሚያጋባ ነው። ይህ ስንኝ አሽዐርዩም ማቱሪዲዩም ሲራኮቱበት የሚታይ ነው። በተጨማሪም የሙርተዷ ዘቢዲን ምስክርነት መመልከት ይቻላል። [ኢትሐፍ፣ ዘቢዲ፡ 2/146]
በዚህ በመጨረሻው ስንኝ ስር ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፡-
" ملعون ملعون قائل هذا البيت وملعون من جعل هذا النصراني حجة في دين الله "
“የዚህ ስንኝ ገጣሚ እርጉም ነው፣ የተረገመ!! የዚህን ክርስቲያን ንግግር በአላህ - ዐዘ ወጀል - ዲን ላይ ማስረጃ ያደረገም እንዲሁ እርጉም ነው! የተረገመ።” ቀጥለውም ይሄ ካፊርም ቢሆም ማጣቀስ ከሚቻልበት የቋንቋ ጉዳይ እንዳልሆነ ዘለግ አድርገው ተንትነዋል። [አልፈስል፣ ኢብኑ ሐዝም፡ 3/122]
የሚያጣቅሱትን ስንኝ መነሻ አድርገን ስናየው ንግግር ማለት ከአንደበታችን የሚወጣው ሳይሆን በልባችን ውስጥ የሚብሰለሰለው ነው ማለት ነው። የዚህ እምነት አራማጅ የሆነው አሽዐርዩ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐሳኪር በኢብኑ ቁዳማ ዘንድ ሲያልፍ ሰላምታ ያቀርባል። ኢብኑ ቁዳማ ግን አይመልሱለትም። ለምን እንደማይመልሱ ሲጠየቁም “እሱ በነፍሳዊ ንግግር የሚያምን ነው። ስለዚህ እኔም በነፍሴ እየመለስኩለት ነው” አሉ። [ጦበቃት ሱብኪ፡ 8/184]
እንግዲህ ተመልከቱ! ቁርኣንና ሐዲሥን አሽቀንጥረው የአንድ ቆሻሻ ክርስቲያን ንግግር ማስረጃ አድርገው እያቀረቡ ነው። አቡል በያን አዲመሽቂ (551 ሂ.) ረሒመሁላህ ለአሽዐርዩ አቡ ተሚም አልአሚን እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“ወዮልህ! ሐንበልዮች (አህሉ ሱና ማለታቸው ነው) ‘ቁርኣን በፊደልም በድምፅም የአላህ ንግግር ለመሆኑ ማስረጃው ምንድን ነው?’ ሲባሉ ‘አላህ እንዲህ ብሏል መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል’ ይላሉ። (አንቀፆችንና ሐዲሦችን ዘረዘሩ።) እናንተ ግን ‘ቁርኣን (ንግግር?) በነፍስ ውስጥ ያለ ለመሆኑ ማስረጃው ምንድን ነው’ ስትባሉ? ‘አኽጦል ንግግር በልብ ውስጥ ያለ ነው ብሏል’ ትላላችሁ። ምንድን ነው ይሄ አኽጦል?! ቆሻሻ ክርስቲያን ነው!! መዝሀባችሁን በሱ የግጥም ስንኝ ላይ ገንብታችሁ ቁርኣንና ሱናን ትታችኋል!!” [አልዑሉው፡ 266]
ጌታችን በሆነ ጉዳይ ብትጨቃጨቁ ወደ ቁርኣንና ሐዲሥ መልሱት ብሎን ነበር። ግና ምን ዋጋ አለው። “ቁርኣንና ሐዲሥ በዐቂዳ ጉዳይ ማስረጃ አይሆንም” የሚል ጠማማ አንጃ ተከስቷል። ይሄ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ፣ እጅጉን የሚሰቀጥጥ ስከሆነ እየዋሸንባቸው ሊመስል ይችላል። የራሳቸውን ንግግር በሌላ ጊዜ እዘረዝራለሁ። ብቻ፡-
- የቁርኣን ማስረጃ ሲቀርብላቸው “ዟሂሩ ኩፍር ነው” ይላሉ።
- የሐዲሥ ማስረጃ ሲቀርብላቸው “ቡኻሪና ሙስሊም ቢዘግቡትም ሙተዋቲር ያልሆነ ሐዲሥ በዐቂዳ ላይ ማስረጃ አይሆንም” ይላሉ።
- የሰለፎች ንግግር ሲቀርብም ፈፅሞ እጅ አይሰጡም።
እነሱ ግን ለዒቀዳዊ ልዩነት ማስረጃ አድርገው አንድ ክርስቲያን ገጣሚን ያጣቅሳሉ። ማፈር የሚባል የለም። ቁርኣን ጥሎ የክርስቲያን ግጥም?
قبحٌ لِمَن نبذ القرآنَ وراءهُ وإذا استــدلّ يقـــول: قال الأخطل
“አይ ያጣቀሱት እኮ ለቋንቋዊ ማስረጃ ያክል ነው” እንደሚባል እጠብቃለሁ። እና ቁርኣንን አሽቀንጥረው እየጣሉ ነው የክርስቲያን ግጥም የሚያጣቅሱት?! ህሊና ላለው ሰው አይደለም የነሱን ስራ ሊሰራ እነሱ ስለሚሰሩትም ይሸማቀቃል። አዎ ቁርኣንና ሐዲሥ እየቀረበ የአኽጦል ቀርቶ የማንም ንግግር ማስረጃ አይሆንም። ሐቅ ማለት ቁርኣንና ሐዲሥ ነው። ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ?!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 15/2012)


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እውነተኛ ገጠመኝ
~~~~~
ከገጠር ወደ ሸገር የመጣች ሙስሊም ናት። ክርስቲያን ዘመዶቿ ልጃቸው ትምህርት ጨርሶ ተመርቆ ኖሮ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅተዋል። እቤታቸው እንደገባች ግድግዳ ላይ የተሰቀለ "የእየሱስን" ምስል ተመለከተች። እሷ እንዴት ብላ የ"ፈጣሪያቸውን" ምስል ይሰቅላሉ ብላ አስባ ?
"ይሄ ነው የተመረቀው ልጃችሁ?" አለቻቸው።

ከነሳራ ቅጥፈት ጥራት ይገባህ ጌታዬ!


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በቃሲም ሱለይማኒ አስከሬን ሽኝት ላይ በተፈጠረ መገፋፋት አምሳ ያላነሱ ሰዎች ሞቱ። ሐጅ ላይ ከስንት አንዴ የሚያጋጥመውን መሰል አደጋ መነሻ አድርጋ ሳዑዲን ስታብጠለጥል የነበረችዋ ኢራን ይሄው እንዲህ አይነት እጣ ገጥሟታል። አሁንም ትማራለች ተብላ አትጠበቅም።
ቃሲም ሱለይማኒ በቅርቡ ባግዳድ ውስጥ በአሜሪካ ጥቃት የተገደለ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ሲሆን እጁ በብዙ ሙስሊሞች የተጨማለቀ ቆሻሻ ፍጡር ነው።


Forward from: Sadat_Text_Posts


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዛምቢያ ውስጥ አንድ "ነቢይ" በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከወንጀላቸው ለማንፃት ‘ጂክ’ የተሰኘ መጠጥ አጠጥቷቸው 28 ሰዎች ሞቱ። 18 ሰዎች አሁንም አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው። ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ ነርሶች ሲሆኑ አራቱ አስተማሪዎች ናቸው።

https://www.branapress.com/2019/11/17/28-people-die-after-pastor-gave-them-jik-to-drink-to-cleanse-their-sins/


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"መውሊድ አይለያየንም" ያሉት ለእስትራቴጂ እንጂ መውሊድን ደግፈው አይደለም" ስትሉ የነበራችሁ!
አሁንስ የአዲስ አበባ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት ከሆነው ሓሚድ ሙሳ ጀምሮ እነ አቡበክርና ሌሎችም መውሊድን ሲያከብሩ ምን አላችሁ?! ኢኽዋን አላማው ወንበር እንጂ ዲን አይደለም የምንለው በምክንያት ነው።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ካድሬ ናችሁ" ሲሉን እንዳልነበር ሙስሊሞችን እንዲያጠፉለት እነ መለስና አባይ ፀሃየን ሲወተውት የነበረን ሰው "ተቀዳሚ ሙፍቲ" እያሉ ይቆልላሉ። ኢኽዋን ማለት መርህ አልባ ቆሻሻ የዲን ነጋዴ ነው።


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አንድነት አንድነትን በመዘመር፣ ልዩነትን በማውገዝ ብቻ አይመጣም። ከልቡ አንድነትን ማረጋገጥ የሚሻ ሰው የልዩነት በሮችን መዝጋት፣ አንድነትን የሚያቀጭጩ አረሞችን መንቀል ይጠበቅበታል። በጀርባ በወንድሞቹ ላይ እያሴረ፣ በፊት ለፊት ስለ አንድነት የሚሰብክ ሰው አላማው አንድነት ሳይሆን የጭፍራ ግንባታ ነው።


Forward from: قناة السنة سفينة نوح
"ቁርኣንና ሱና፞ን የሚፃረር ሰው እውቀቱና ኪታቡ የበዛ ቢሆንም ሙብተዲዕ ነው።
( አልኢማም አልበርበሃሪ ሸርሑ ሱና፞: 270 )
t.me/Menhaj_Salafiya

20 last posts shown.

2 410

subscribers
Channel statistics