Open reading 🕊⃤


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


🈴 Join our association to participate in open book club events!
_ Participatory reading session
- Question and answer contests
- Experience exchange and seminar events for Stay tuned to our Telegram channel!

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


📌ማስተወቂያ፡ ለማህበራችን አባላት የተለያዩ ቋሚ እና ጊዜያዊ ወይም እለታዊ የስራ እድሎችን እያመቻቸን ነው!

እኛ እናንተን ለማገዝ ዝግጁዎች ነን!
በስራው ውስጥ ቅድሚያ ለማግኘት የማህበራችን አባል መሆን አለቦት!

❗️ለአባልነት ለመመዝገብ 👇 ይህንን ቦት ይጠቀሙ!

@Membersapplicantbot


#ሼር ማድረግዎ*አይዘንጉ
▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1






አሁኑኑ ማሳወቅ የምትችሉ!

•  ከ ዿግሜ 4 ጀምሮ ለ 20 ቀናት የሚሰራ አክቲቬሽን ስራ፡፡
•  የስራ ሰዓት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት – ማታ 12፡00 ሰዓት
•  ደሞዝ፡-4500 ብር + ኮሚሽን
- በዚህ ስራ ላይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ጠንክሮ ለሰራ ሰዉ ሽልማት አለው።

    - ከደሞዙ በተጨማሪ የብርና የሰርተፍኬት ሽልማቶች የኖራሉ።
•  መስራት የምትችሉ በእዚህ ቴሌግራም @teddy_mark ቴክስት አድርጉ

ብዛት ሶስት ሴት ብቻ!

•  እናመሰግናለን!
👇👇👇
0933758181 የሚሰራ አሁኑኑ ደውሉ::

የምንፈልገውን የሰው ብዛት ስናገኝ ማስታወቂያውን እንደምናጠፋው አሳስባለሁ!


ከፍቃዱ አየልኝ “ግርባብ” ዉስጥ የተጠቃቀሱ ዉብ ሀሳቦች!
===========================

…በል ንሳማ ዐደራህን፣ለሚፈለፈለዉ ጫጩትህ ንገረዉ፣ሳይታቀፍ የቀረ እንዴት ሆኖ እንደገማ አሳየዉ።

… ቢሆንም ክብደት ከሸክም ሳይሆን ከመንገድ ነዉ።ቀላል ሸክም በዳገት መንገድ ከባድ ነዉ።እንዲሁም ፣ነገር በሚቋጥር ሰዉ ፊት ዝርዉ ሁሉ ቅኔ ነዉ።”

ልብ ማለት ያለብህ ግን ፣የሰዉ ሁሉ ንግግር ስላንተ እንጂ አንተ እንዳልሆንህ ነዉ።

… እናም ፣በሆዷ ቀለም ከሞላች ብዕር ይልቅ ቀለሟን በትና የጨረሰች “ምሁር” ናት።ምክንያቱም ፣ተብከንክና አዉቃለች፣ክፉና ደግ ፅፋለች ብለን እንደገና አካሄዷን ስንመረምርዉ… ነገር ሁሉ ሀሳብ ነዉ።

…እንደ ቆሎ ተማሪ አኩፋዳ በልቤ ዉስጥ ሰዉ የሰጠኝን ኹላ እከት ነበር።ለካ፣ኹሉም ተጥፎ ካልተቀመጠ ብርድ አይከላከልም…

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


በእኛ አምሳል የመጣ ጂበራል ነው።
=====================
(ደረጄ በላይነህ)

አንዳንዴ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ እንዳይሆን የዚህ ዐይነቱን ድንቅ መለየት ያሻል። መጽሐፉን ሳይታተም አይቸዋለሁ፤ሌላኛው በእኛ ልክ፣በእኛ አምሳል የመጣ ጂበራል ነው። መጽሐፉ ዝም ብሎ የሚሸመጠጥ አይደለም፤እንደቡና እሸት የሚለቀም ነው። ደግሞ ደጋግሞ ማንበብ፣ማሰላሰል ይፈልጋል፤እውነት ለመናገር ወጣት የጻፈው ሳይሆን ምራቁን የዋጠ፣የማስተዋሎች እርከኖችን ያለፈ ሰው ድርሰት ይመስላል።

ኪናዊ ለዛውን ስናይ በየአንጓው የየራሱ ጣዕምና ለዛ አለው። የተንዠረገገ ፍሬም ጎምርቶ ፣ያጓጓል። መጽሐፉን ሳነብብ የተሠማኝ ስሜት ደግሞ፣ታላቁ ኀያሲና ገጣሚ ጆን ድራይደን እንዳለው የየዘመኑ ጂኒየስ ዐይነት ሆኖ ነው። እያንዳንዱ ዘመን የየራሱ ከሳቴ አለውና በርግጥም በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ የተለየ ቅርጽ፣ጥልቀትና ውበት ያለው ነው። እንደዚህ በሌላ በር ማንኳኳት ደስ ይላል፤መጋረጃው ሌላ ቀለም ሲኖረው ድባብ ይቀይራል።
እንደ ግጥም ባለዜማ፣እንደ ዝርው ዝርግ ነው፤ብዙ ተሸክሟል፤ብዙ ዐይኖችም አሉት፤ የባለሞያ እንጀራ ይመስል ሺህ ቦታ ያያል።

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


ሕይወት አዙሪት ናት፣ ረጅም እርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ||ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ!

ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ። በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ። የሕይወትን ትግል እየዳዳህ ትጀምራለህ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ።

ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል። ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ። የጀመርክበትን አትርሳ መጨረሻህ ነውና። የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና። ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ፣ ተምረህ እውቀት ብትጨምር፣ ነግደህ ሀብት ብታገኝ፣ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሰለጥን፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፣ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።

ልብ በል!

ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ እውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም። በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ። በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ።

ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል?

ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል?

ሕይወት መጨረሻዋና መጀመሪያዋ አንድ ነው። በዚህ የተነሳ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው። ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም። ልብ በል! የዓለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው። ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በጸጸተን ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


ሰውዬው በሞት ጣዕር ተይዞ በተኛበት አልጋው አጠገብ የቆሙት ካህን ``ልጄ! እንግዲህ በዚህ ሰዓት ካንተ መስማት የሚገባኝ ኑዛዜ አለ`` ይሉታል። ሰውዬውም የካህኑን ጥያቄ ለመመለስ መስማማቱን በአንገቱ ንቅናቄ ገለፀ።

ካህኑም ``በዚህ ሰዓት ዲያብሎስን ክጃለሁ በማለት ተናዘዝ`` አሉት። ሰውዬው ግን በካህኑ ጥያቄ አልተስማማም። ከአንገቱ ቀና ለማለት እየሞከረ በጣዕር ድምፅ “አባቴ፤ ከዚህ በኋላ ጠላት የማፈራበት ሰዓት ላይ አይደለሁም” በማለት ተመልሶ ተጋደመ።🙂

   ፦ ጥበብ ከጲላጦስ - ቅጽ ሁለት! / ሃይለጊዮርጊስ ማሞ
▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


“Buddha was asked is What did you gain from meditation ? He replied. NOTHING. However. let me tell you what i lost : Anger.. Anxiety.. Depression.. Insecurity.. Fear of old Age and Death.”


`` ቡድሃ በተመስጦ ምን ጥቅም አገኘህ ተብሎ ተጠየቀ። ‹ምንም› ብሎ መለሰ።  ይሁን እንጂ ያጣሁትን ልንገርህ፡ ቁጣ...ጭንቀት...ድብርት...አለመተማመን...የእርጅና እና የሞት ፍርሃት። ``



                   @Open_reading1


“ሰዎች እጅ ላይ በባርነት ተይዘን ሳልን እንኳን የራሳችን ገዢ ስላደረከን ፈጣሪ ሆይ እናመሰግናልን አለ። አየህ እራስን መግዛት ሌሎችን ከማስገበር በላይ ጀግንነት ይጠይቃል።” ገፅ 200

****

እስኪ ልብ ብለህ አጢነው፤ እዚህ ቤተ-እግዚአብሔር ስንመጣ የምናገኘው ሰላም መተኪያው ምንድነው? ብድራችን እንደተከፈለ፣ ዕዳችን እንደተሰረዘ፣ ችግራችን እንደተቀረፈ ሁሉ ፍፁማዊ ሠላምና መፅናናት የምናገኘው እንዴት ነው? አንድ ሙጭቅላ ከእናቱ እቅፍ ሌላ ርስት አለው? የሰው ልጅም እንደዚያው ነው፤ በእምነት አምላኩ እቅፍ ውስጥ ከማረፍ ውጭ የአለም ውጣ ውረድ የሚያሻውን ሰላም አይሰጠውም። ገፅ 20

****

መውደቅ መነሳት ለሰው ልጅ ሁሉ የተዘጋጀ መንፈሳዊ ገዞ ነው። ድፋትና ቅናት የሌለበት የህይወት ሙዚቃ፤ ፍፁማዊ ፀጥታ የሰፈነበት የሙታን ግቢ ነው።  ገፅ 189

||ቤባኒያ - አለማየሁ ገላጋይ!
▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


ቤባንያ (በተገኘበት ይነበብ)…. ለቅምሻ

“አንድ ሰው ስጦታ ይዞላችሁ መጣ እንበል” አሉ ሊቁ

“እ-ሺ”

“ያንን ስጦታ ባትቀበሉ ስጦታው የማን ይሆናል?” ሲሉ ጠየቁ።

“የአምጪው”

“ጥሩ ስድብም እንደዚያው ነው፤ ካልተቀበላችሁት ለተሳዳቢው የመላሽ ይሆናል።”

ለእንደዚህ ያለ ማህበረሰብ ገመናውን በመሸፋፈን የሺህ አመታት ልምድ ላለው ህዝብ ስድብህን ወደ ኋላ ደብቆ አክብሮት በማሳየት የሚያገለማ ጥንጣን ህብረተሰብ ፈትሎ ሚያድር ያስፈልገዋል።

የውርደት መሰረት ላይ ኩራትን ለገነባ ሰው ከስድብ ሌላ መፍትሔ ስራይ አለው? ….. የለውም!! 64

****
▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!


- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


||በአገራችን ብዙ ሀብታሞች አሉ፤ ብዙ ባለ ጸጎች ግን የሉንም! /ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ - ችቦ/

ሀብታሞች ከባለጸጎች የሚለዩት ገንዘብ የሚያገኙት የሌሎችን በመቀማትና እንዲያም ሲል በማደህየት ሲሆን ባለጸጎች ግን ሀብትን በድካማቸው ይፈጥሩታል፡፡ ታላቁ የአሜሪካ የመኪና አምራች ኩባንያ ባለቤት ሚስተር ፎርድ ሥራውን የጀመረው አካፋና ዶማ በማምረት ነበር፡፡ ባለጸጎች ለሌሎች ይተርፋሉ እንጅ አይቀሙም፡፡ ሀገራችን ባሳለፈቻቸው ሠላሳና አርባ ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገት ጭላንጭል ቢታይባትም በሞራልና በሕግ ባለመመራቱ ብዙ ባለ ሀብቶችን እንጅ ብዙ ባለ ጸጐችን አልታደለችም።

እነዚህ ድካምን ሳያዩ፣ ልፋትን ሳይቀምሱ ገንዘብ ያግበሰበሱ ባለ ሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ከማናጋታቸው በላይ በወጣቱ ሥነ ልቡና ላይ የፈጠሩት ጠባሳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከጠባብ ወደ ሰፊ፣ ከውድቀት ወደ ስኬት፣ ከኮረኮንች መንገድ ወደ ደልዳላ ጉዞ፣ ከመሳሳት ወደ መታረም በመጨረሻም ከማጣት ወደ ማግኘት ከአካልና ከአዕምሮ ብስለት ጋር እንደሚታደግ ለወጣቶች ያስተማራቸው አርዓያ የሚሆናቸው አልነበረም። ትናንት ምንም ያልነበረው ድንገት ዛሬ በርካታ ሚሊዮን ብሮች፣ ብዙ ህንጻዎች፣ ተሽከርካሪዎች፤ ድርጅቶች እንዳሉት ይሠማሉ። በቃ የሀብት መንገድ አጭርና አቋራጭ ብቻ እንደሆነ፣ በድካም በጊዜ ሂደት መበልፀግ ሞኝነት እስኪመስላቸው ድረስ ስነ ልቡናቸውን አጣመምናቸው፡፡

በጥቅሉ ከባለጸጎች ስኬት ጀርባ ብዙ የፈሰሰ ወዝ፣ የተንጠባጠበ ላብ፣ የተኮማተረ ጅማት፣ የታጠፈ አንጀት፣ የተላጠ ትከሻ አለ፡፡ ከሀብታሞች ታሪክ ጀርባ ግን ቅሚያ፣ ውንብድና እና ማጭበርበር ይኖራል፡፡ ሀብት ከፈጠረው የቀላ ደረት፣ የወዛ ፊት ጀርባ የቆሸሸ ኅሊና ሊኖር ይችላል።

@Open_reading1
@Open_reading1


''አይዞህ! በተለያየ መንገድ ብንጓዝም በቅንነት እስሆነ ድረስ ፈጣሪ ቅን ፍርዱን አይነሳንም''

⇲ ⇲  ሚተራሊዮን ⇲ ⇲

....እኔ ትክክል ሆኜ ከአላህ ፊት ስቀርብና ስባል አንተ ስህተተኛ ሆነክ ስትባል ቸሩ አላህ ሆይ ኪብሩን ጀነት አብረህ ካላስገባህ ብቻዬን አልገባም እላለሁ ወይም ደግሞ አንተ ትክክል ሆነክ ክርስቶስ ፊት ስትቀርብ ሲባል ትላለህ። በዚሁ መልኩ ሁለታችንም safe እንሆናለን'' አለ።

ንግግሩ የዶ/ር ክብረ በዓልን ብቻ ሳይሆን የኔንም እንባ አስመጣው።

ድንገት ክብረ በዓል ብድግ ብሎ'

''አይዞህ! በተለያየ መንገድ ብንጓዝም በቅንነት እስሆነ ድረስ ፈጣሪ ቅን ፍርዱን አይነሳንም'' አለው።

ደራሲ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ሚተራሊዮን ገፅ 9

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ [Ethiopian Readers Association!]
◎ {Book Lovers Union!}

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1




Susan E. Schwartz's "The Absent Father Effect on Daughters" is not just about dads who walk out, but also about emotionally distant dads who might be physically present but not truly connected. Here's a breakdown of some key takeaways:

1. Not Just About the Empty Chair: We often think absent fathers are the ones who leave the family. This book goes deeper. Even dads who are physically there can be emotionally distant, like a workaholic dad who's always busy. This lack of emotional connection can leave a daughter feeling unseen and unheard, leading to similar struggles as a truly absent father.

2. Deeper Than "Daddy Issues": Forget the stereotype. This book explores the profound impact a father, present or not, has on his daughter's sense of self. It's about confidence, self-worth, and the ability to express yourself authentically. If a daughter doesn't feel secure in her father's love and support, it can leave a lasting mark on how she sees herself in the world.

3. Creating a "Fake You": Imagine a chameleon constantly adapting its colors. That's kind of what the book suggests daughters of absent fathers might do. They create a "false self" to gain their father's approval. This can involve hiding their true feelings and desires, morphing into who they think their dad wants them to be, instead of embracing who they truly are.

4. The Wound That Ripples Out: The impact of an absent father doesn't stop at the father-daughter relationship. It can be like a pebble tossed in a pond, creating ripples that affect a daughter's relationships with other men and even her own sense of self-worth. It can make it harder to trust men or feel comfortable expressing her needs in relationships.

5. Unveiling the Hidden Symbols: This is where things get interesting. The book uses Jungian psychology, which explores archetypes like deep-seated symbols and patterns in the psyche. It suggests the father figure can be seen as an archetype, like the "wounded king" who represents unfulfilled potential. Understanding these archetypes can offer a deeper understanding of the father-daughter dynamic.

6. Healing is Possible: Here's the good news! The book isn't just about the pain. It offers tools and strategies for daughters of absent fathers to heal from the "father wound" and build a strong sense of self. It's about processing those emotions, understanding the impact, and ultimately moving forward.

7. Finding Your Voice Again: Imagine a voice that's been silenced. "The Absent Father Effect on Daughters" encourages daughters to reclaim their voice, to rewrite the narrative of their lives. It's about understanding their experiences and moving forward with newfound strength and confidence.

8. The Focus is You: This book isn't about blaming fathers. It's about empowering daughters to take charge of their own emotional well-being and build healthy relationships. When you understand the profound impact of an absent father, daughters can learn to navigate the complexities of this relationship and move towards healing and personal growth.

BOOK: https://amzn.to/3MwQQc9

You can get the Audiobook for FREE when you register for Audible Membership through the same link above

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ [Ethiopian Readers Association!]
◎ {Book Lovers Union!}

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


የነስሩዲን ዳኝነት ~~~
    ሙላ ነሱሩዲን በዳኝነት ተሰይሞ በሚሰራበት ችሎት ላይ አንድ በሌቦች የተዘረፈ ሰው  ይቀርብና  በሰፈሩ ውስጥ በሚገኝ አሳቻ ስፍራ ሌቦች ልቡሱን ጭምር አስወልቀው እንደዘረፉት ይናገራል።
     ሙላ ነሱሩዲንም  ተዘራፊውን ሰው ከዳመጠ በኃላ ፡-  "እንደማይህ ሙታንቲ እና ካነቴራ ትተውልሃል?" ሲል ጠየቀው ።
"አዎ ጌታዬ!" አለ  የተዘረፈው ሰውዬ
ሙላ ነስሩዲንም ገራሚ ብይኑን እንዲህ ሲል ሰጠ ... አለ ተአምረኛው ሙላ ነስሩዲን ።
        
      ~ከፌስቡክ ድህረገጽ ~

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ [Ethiopian Readers Association!]
◎ {Book Lovers Union!}

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


የዓለም ፍፃሜ

        ሙላ ነስሩዲን አንድ የሰባ ሙክት ፍየል ነበረው ።ይህንን ፍየል ለመብላት የቋመጡ የነስሩዲን ጎረቤትና ወዳጆች "ይህን ፍየል አርደህ አብላን" እያሉ ወተወቱ ።ኑስሩዲን ግን አሻፈረኝ አለ ። በመጨረሻም ዘዴ ያሉት ዘይደው በመምጣት እንዲህ አሉት  "ይሄውልህ  ሙላ ከሶስት ቀን በኃላ የዓለም ፍፃሜ ነው ፣ለጠፊ አለም ብለህ ይህንን ፍየል ሳታበላን ብንሞት ለአንተም ከነኔ ነው " ቢሉት የአለም ፍፃሜ ዋዜማ ምሽት አርዶ እንደሚያበላቸው ቃል ገብቶ ተለያዩ ።ቀኑ ደረሰ ፣ድግሱን የደገሰው ነስሩዲን አብላቸው አጠጣቸውና መኝታ አዘጋጀላቸው።ሁሉም የደረቡትን ልብስ አወላልቀው ተኙ ።ሙላ ነስሩዲን ንዴቱን የሚወጣበት ሰአት ደረሰ ።ያወለቁትን ልብስ ስብስቦ በእሳት እያጋየ ሲሞቅ ጠዋት ሲነሱ  ተመለከቱና ተንጫጩበት ።ነስሩዲንም ተረጋግቶ ብሎ ንዴቱን ተወጣ ።

      ~ከፌስቡክ ድህረገጽ ~

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ [Ethiopian Readers Association!]
◎ {Book Lovers Union!}

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1




➬ መግቢያው ፍቅር፣ መውጫው ክብር የሆነበት ድግስ እነሆ!

ሰሞኑን በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከምንጠብቃቸው የጥበብ ድግሶች አንዱ የሆነው ብዙ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ሰዎች የተሳተፉበት የደራሲ እና ኢንጅነር ሚካእኤል አስጨናቂ መፅሀፍ ምርቃት በዛሬው ዕለተ አርብ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ኢ ክላስ ህንፃ ዋልያ መፅሀፍት አዳራሽ ሞቅ ደመቅ ባለ ፕሮግራሞቹ ታጅቦ ደምቆ የሚውል ይሆናል ።

ይሄ ከ 10 ሰዓት ተኩል አንስቶ የሚቀርበው የአዕጋረ ፀሀይ መፅሀፍ ምረቃ ግጥምን በጃዝ ፣ ሙዚቃ ፣ ስዕል እና የመፅሀፏ ዳሰሳዎች የሚስተናገዱበት መድረክ ይሆናል ።

መሶብ ባንዶች በዓሉን ያደምቁታል ።

በሀገራችን ወግ እና ባህል መሰረት ቡናው ፣ ፋንዲሻው ፏ ብሎ የአዲስ ዓመት መምጣትን የሚያበስር ነገሪት ይጎስማል ።

የቻሌንጅ አሸናፊዎች ደጎስ ያለ ሽልማታቸውን ይቀበላሉ ።

ጥበባዊ ለዛ ያለው ድባብ ይኖራል ።

መግቢያው ፍቅር
እና
መውጫው ክብር የሆነበት የማይቀርበት ድግስ እነሆ ለእናንተ ተብላችኋል ቤተሰቦች፣ ተጋበዙልን!

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ [Ethiopian Readers Association!]
◎ {Book Lovers Union!}

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


"አንባቢ" ሲባል ቀርጸን ያቆምነው የሆነ ምስል አለ። የማይስቅ፣ የማይጫወት፣ ኮስታራ፤ በየንግግሩ አፍታ “እገሌ እንትን የሚለው መጽሐፉ ላይ እንትን አለ” እያለ በጥቅስ የሚያታክተን፤ ከእጁ መጽሐፍ የማይጠፋ ዓይነት ነገር። እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ለእኔ የ“woody allen”ን ገለጻ ከወሰድን ለ“PseudoIntellectual”ነት የቀረበ ነው። ለምንድነው የእኛ ሐገር ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ተቋም ሆነው ሳለ አዳዲስ ግኝቶች በመፍጠር ላይ የማናገኛቸው? ለምንድነው እንደበቀቀን እገሌ የተባለ ፈረንጅ ያወራውን መሸምደድ ዕውቀት የመሰለን? …ማንበብ ለእኔ ማንበብን ብቻ የሚወክል ሐሳብ አይደለም። አንብበህ ምን አመጣህ? ምን አዲስ ነገር አሰብህ? በምን መልኩስ ለወጠህ የሚለውንም ያጠይቃል። ሥነ ልቡና ሲባል Freudን ፤ ፊዚክስ ሲባል Einsteinን እያልን ስንት ዘመን ልንዘልቅ ነው? እነዚህ ሰዎች የሠሩት ሥራ ለእኛ የሚሰጠውን ጥቅም ማሳነሴ ሳይሆን (ኧረ ምን ቆርጦኝ!) እኛ ምን ሠራን? የሚለውንም ደፈር ብለን አብረን እንድናየው ነው።
.
ማንበብ አሳቢ ካላደረገ፤ አንባቢ የተባለው ሰውም የመፍትሔ ሐሳብ ጠቋሚ ካልሆነ ወይም በንባብ የቀሰመውን ልምድ ጠርቆ ውበት አልያም ዕውቀት የሚሆን ነገር "እንካችሁ!" ካላለን ምን ይፈይዳል? አንባቢ የመሆን መገለጫ በተዓብዮ የዕውቀት ምሬት ተሞልቶ "አይ ይሄ ማኅበረሰብ!" እያሉ መብሰክሰክ አይደለም። በምትሰድበው ሕዝብ ውስጥ የልጅ ልጅህን የሚገራ ስንትና ስንት ግለሰብ አለ? …እና "ማንበብ" ትንሽ አንብቦ በቅጡ ማሰብም ሊሆን ይችላል። ምን ይመስልሃል? ለምን "ተምረናል አውቀናል፣ በቅተናል!" ከምንል ከእኛ አያቶቻችን የተሻለ የሕይወት መረዳት ኖራቸው? ብለን አንጠይቅም?! መቼስ ነው “አቦ ይቺ ፀሐይ!” ብዬ ሳማርር “አክብራት! ቀድማህ የተፈጠረችው እሷ ናት!” እንዳሉኝ ሽማግሌ የምበስለው? የምን ጊዜም ኦቶባዮግራፊ የምንላቸው መጻሕፍቶች በደምብ የተኖሩ የግለሰብ ሕይወት ትርክቶች ናቸው። በሩቅ አላዋቂ እያልክ የምታናንቀው ሰው ሕይወት በመጽሐፍ መልክ ቢጻፍ ያንተ ክላሲክ ኦቶባዮግራፊ ሥራ ሆኖ ሊቀመጥ ይችላል። በማንበብ ብትበልጠው በመኖር ደግሞ የሚበልጥህ አለ። ረጋ በል!
.
4. ማንበብ ላይጠቅምህ ይችላል። አለማንበብም ሊጎዳህ ይችላል።
.
አብዛኛውን ጊዜ ደራሲያን የሚጽፉትን የማይኖሩ ናቸው። ስለተስፋ ጽፎ በጻፈው ጽሑፍ የተጽናና ማነው? ስለለጋስነት ጽፎ እጁ የሚሰስት ደራሲ ሊኖር ይችላል። አንዳንዴ እንዲህ ዓይነት የዋህነት አያለሁ። "እገልዬ!" የሚያስብል ፍቅር፣ "የት አባቱ!" የሚያስብል ጥላቻ ምናልባት የንባብ ባሕላችን ባለመዳበሩ ወይም የምናገኛቸው መጻሕፍት ውስን ስለሆኑ የገጠመን ይመስለኛል። አድናቆትና ትችታችን መሠረቱ የተምታታ ነው። ሥራውንና ሠራተኛውን ፤ ደራሲውንና ድርሰቱን ለይተን አልያዝንም። ለይተን አልተውንም። ግን በዚህ ሁሉ መሐል " ፍጹም አውቃለሁ!" ባዮች ነን። "እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው" የምትለዋ የአርስቶትል አባባል ብትለመድም ተራ ንግግር አለመሆኗ እያደር የገባኝ በየቀኑ ለአዳዲስ መጻሕፍትና ለአዳዲስ ደራሲያን ራሴን ክፍት እያደረግሁ በመጣሁ ቁጥር ነው። ማንበብ ውስጡ እየገባን በሄድን ቁጥር ሰፊ ባሕር ውስጥ እንደመጥለቅ ነው። ያልዳሰሰን ውኃ ገና በዚያ አለ። ያልነካን መገለጥ ገና በዚህ አለ። ያልኖርነው በረከት ገና ወዲያ አለ። እንወቅ። እናንብብ። ነገር ግን የማያነበውን ሰው ጥሰነው እንደሄድንና፤ እንደእኛ ማሰብ እንማይችል አድርገን የምንቆጥር ከሆነ ግን ሁሉንም ወዲያ ጥለን ወይ ቁርሀን፤ ወይ መጽሐፍ ቅዱስ እንግለጥ። ያልተቆረጠ ግብዝነት ውስጣችን አለ ወገን። እና እንደእኔ እይታ ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም። አለማንበብ ግን ሊያጎድል ይችላል። አንብቤያለሁ የመኮፈሻ መሣሪያ መሆን የለበትም። ያነበበ ሰው ትሁት ነው። ያነበበ ሰው ዝቅ ብሎ ለመማር አይጨንቀውም። ያነበበ ሰው ለመናቅም ለመከበርም ግድ አይሰጠውም። ያነበበ ሰው በፍቃድ ባሪያ እንደሆነ ንጉሥ ነው። እና የንባብ ባሕል በዘመቻ ሰው ላይ የምትጭነው ነገር ሳይሆን፤ ትውልድ ላይ መሠረት ባለው መልኩ የሚቀረጽ የኑሮ ስልትና እቅድ ነው።

እንደመውጫ(ባልተያያዘ ዜና)
.
4. ስብሐትና faulkner
Faulkner አንዴ ተጠየቀ “አንዳንድ ሰዎች ሁለቴም ሦስቴም አንብበውት ጽሑፍህን አይረዱትም። ምን ቢያደርጉ ትመክራለህ?” ሲመልስ ምን አለ? “ለአራተኛ ጊዜ እንዲያነቡት።”
ስብሐት አንዴ ተጠየቀ። “አንዳንድ ሰዎች ደጋግመን አንብበንም ስብሐት የሚጽፈው ነገር አይገባንም ይላሉ። ምን ቢያደርጉ ትመክራለህ?” ስብሐት ሲመልስ ምን አለ? “ለምን አትተወውም?! ምን አታገለህ?!”
-
እንዲህ የተንዘላዘለ ፅሑፍማ ያለመፈክር አይዘጋም።
.
እናንብብ! እናስነብብ! የሚያነብ ትውልድ እንፍጠር!
This weeks recommendation;- saul bellow - “seize the day”

ሄኖክ በቀለ ✍

20 last posts shown.