ሕይወት አዙሪት ናት፣ ረጅም እርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ||ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ!
ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ። በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ። የሕይወትን ትግል እየዳዳህ ትጀምራለህ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ።
ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል። ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ። የጀመርክበትን አትርሳ መጨረሻህ ነውና። የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና። ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ፣ ተምረህ እውቀት ብትጨምር፣ ነግደህ ሀብት ብታገኝ፣ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሰለጥን፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፣ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።
ልብ በል!
ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ እውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም። በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ። በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ።
ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል?
ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል?
ሕይወት መጨረሻዋና መጀመሪያዋ አንድ ነው። በዚህ የተነሳ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው። ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም። ልብ በል! የዓለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው። ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በጸጸተን ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!
▬▬▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!
◎ የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!
- https://t.me/Open_reading1