Federal TVET Agency


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Technical and Vocational education and training Agency

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር #የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ #ኮሌጆች






በደቡብ ብሐር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት #የመንግስት_የቴክኒክና_ሙያ ትምህርትና ሥልጠና #ኮሌጆችና የሚገኙበት ዞንና ወረዳ


#የተራዘመ_የመመዝገቢያ_ጊዜ_ስለማሳወቅ
በኢትዮጵያ ከቴክኒካል ዩንቨርሲቲ ከሲ ወደ ቢ ደረጃ በ2013 ዓ/ም የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በዋናው ግቢ እና ሳተላይት ካምፓስ የምትገቡ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ አሰላጣኞች የመግቢያ ጊዜ #መጋቢት 2 እና 3 የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን የመግቢያ ፈተና ውጤት ለክልሎች እና ኮሌጆች ባለመድረሱ የመግቢያው ቀን ወደ #መጋቢት 16 እና 17/ 2013 ዓ/ም የተዛወረ መሆኑን አውቃችሁ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልታችሁ እንንድትመዘገቡ እንገልፃለን፡፡
በ2012 ዓ/ም በትምህርት ላይ የነበራችሁ ውጤት ባለመሙላቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጣችሁ መመዝገቢያ ጊዜ መጋቢት በ18 እና 19/2013 ዓ/ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡//@FTA












#ኢንስቲትዩቱ_ወደ_ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲነት_ተሸጋገረ
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት #የኢትዮጵያ_ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲ በሚል ስያሜ ወደ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲነት መሸጋገሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ያስታወቀው ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ስልጠና አጠናቃቂዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደገለጹት ሚንስቴር መስሪያቤቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ #ለአገር_ግንባታ ያለውን ፋይዳ በመረዳት በዘርፉ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
እንደ ሚንስትሩ ገለፃ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ስራዎች ሀገር በቀል እውቀትን መሰረት በማድረግ ዜጎች የሙያ ባለቤት ሆነው በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ብቁ ሰራተኞች የሚሆኑበትን አማራጭ ለማስፋት፣ ቴክኖሎጂን በመቅዳትና በመፍጠር ሂደት የሚሳተፉ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተፈላጊ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ነው፡፡
ከለውጥ ስራዎቹ ጋር ተያይዞም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ለዘርፉ አሰልጣኞችን፣ አመራሮችንና ቴክኖሎጂስቶችን የማቅረብ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ #አቅም የመፍጠር ስራ እንደተጀመረ ነው ሚንስትሩ የገለጹት፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና ባላቸው ጸጋ እንዲለዩ በቀረበው የትምህርትና ሥልጠና #ፍኖተ_ካርታ ጥናት መሰረት ኢንስቲትዩቱ በቴክኒካል ዩኒቨርሲቲነት እንዲደራጅ የተወሰ ሲሆን ከዚህ ቀደም ይሰራቸው የነበራቸውን መልካም ስራዎች አስፍቶና ተጨመማሪ ተልዕኮ ይዞ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ችግሮችን የሚፈቱ ባለሙያዎችን በጥራት፣ በአይነትና በብዛት እንዲሁም በደረጃም ጭምር አሻሽሎ እንዲያፈራ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት ኢንስቲትዩቱ #የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚል ስያሜ ይዞ ወደ ስራ ይገባል ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል የትምህርትና ሥልጠና ስራው ዘመኑ በደረሰበት #የዲጂታል ቴክኖሎጂ እየታገዘ የዘመነ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የቦርድ አባላትም የዩኒቨርሲቲውን #የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ከግንዛቤ ያስገባ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ተጨማሪ የቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚያስፈልግና የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ቀጣይ ለሚከፈቱት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል እንዲሆን እንደሚሰራ ዶ/ር ሳሙኤል ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉን እንዲደግፍና ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱና ሌሎች አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው ላደረጉት ድጋፍና ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩቱ ሲሰራቸው የነበሩትን ዋና ዋና ተግባራት አጠናክሮ ይሄዳል ያሉት አቶ ተሻለ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የአቅም ግንባታ ማዕከል መሆኑ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ያለውን የአሰልጣኞች እጥረት ለመቅረፍ ታሳቢ በማድረግ በ2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተደራሽነቱን ለማስፋት በስድስት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ውስጥ 15 የሳተላይት ማዕከል በመክፈት ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በእስካሁኑ ሂደትም ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡












#የሰልጣኞች_ዕውቀትና_ክህሎት_የስራ_ገበያውን_የሚመጥን_እንዲሆን_የአሰልጣኞችንና_የተቋም_አመራሮችን_ብቃት_ማሳደግ_ያስፈልጋል፡፡
ዶ/ር #ሳሙኤል_ኡርቃቶ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር
#የኢትዮጵያ_ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲ_በተለያዩ_ሙያዎች_በመጀመሪያና_በሁለተኛ_ዲግሪ_ያሰለጠናቸውን_1920_ሰልጣኞች_አስመረቀ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በምረቃ ስነስርቱ ላይ እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ልማት በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
በሀገራችን ካሉ መልካም አጋጣሚዎች አኳያ ግን ዘርፉ አሁንም ድረስ ብቁና በቂ ስልጠና አጠናቃቂዎችን ለስራ ገበያው ማቅረብ አልቻለም፡፡
ለተግባር ትምህርትና ሥልጠና የዳበሩና ጥራት ያላቸው የስልጠና ተቋማት ሳይለሙ መቆየታቸውና የተገነቡ ተቋማትም በንድፈ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ስልጠና መስጠታቸው ለስልጠናው ውጤታማነት ማነስ እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በመሆኑም የሰልጣኞች ዕውቀትና ክህሎት የስራ ገበያውን የሚመጥን እንዲሆን የአሰልጣኞችንና የተቋም አመራሮችን ብቃት ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱም በዚህ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩትን በቴክኒካል ዩኒቨርስቲነት እንዲደራጅ አድርጓል ብለዋል፡፡
ተመራቂዎች ኢንስቲትዩቱ በቴክኒካል ዩኒቨርስቲነት እንዲደራጅ በተወሰነበት ወቅት መመረቃችሁ ድርብ ደስታን የሚሰጥ ነው ያሉት ሚንስትሩ፣ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አቅርበዋል፡፡
ዛሬ እናንተ ዋጋ ከፍላችሁ የምትሰሩት ትውልድን የመቅረጽ ስራ ነገ ለልጆቻችሁ ደስታና እፎይታ ነወ፡፡ በመሆኑም ጥልን ሳይሆን ፍቅርንና አንድነትን አስተምሩ፣ ልማትንና ስራን ለሰልጣኞቻችሁ አሳዩ፣ ለአገራችን እድገት የእናንተ አስተዋጽኦ የማይተካ በመሆኑ ሙያችሁን አክብራችሁ በቅንነትና በትጋት ለኢትዩጵያ እድገት ስሩ ሲሉም ሚንስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ #ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በአሁን ሰዓት በሰባት ፋኩሊቲዎችና በ23 የቅድመ ምረቃ እንዲሁም በ10 የድህረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
እየተሰጡ የሚገኙት ፕሮግራሞችም ኢትዮጵያ የቅድሚያ ቅድሚያ በሰጠቻቸው የሙያ መስኮች ላይ ያተኮሩ እና ኢንዱስትሪንውና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሁን ከተመረቁት 1920 ስልጠና አጠናቃቂዎች በተጨማሪ 1000 ስልጠና አጠናቃቂዎች በሁሉም የሳተላይት ካምፓሶች በቀጣይ ሳምንት ይመረቃሉ ብለዋል፡፡


#ኢንስቲትዩቱ ከ2500 በላይ ሰልጣኞቹን ነገ ያስመርቃል፡፡ በዕለቱ ወደ #ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲነት_ማደጉን_ይፋ_ያደርጋል፡፡
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ2500 በላይ ሰልጣኞቹን ነገ ያስመርቃል፡፡
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን በዕለቱ ኢንስቲትዩቱ ወደ ዩኒቨርሲቲነት ማደጉ ይፋ እንደሚደረግ የወጣው መርሃ-ግብር ያመለክታል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና በልህቀት ለመለየት ባደረገው ጥናት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት በቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ምድብ ተካቶ ከኢንስቲትዩትነት ወደ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲነት እንዲያድግ መወሰኑ ይታወሳል፡፡





20 last posts shown.

7 368

subscribers
Channel statistics