#ኢንስቲትዩቱ_ወደ_ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲነት_ተሸጋገረ
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት #የኢትዮጵያ_ቴክኒካል_ዩኒቨርሲቲ በሚል ስያሜ ወደ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲነት መሸጋገሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ያስታወቀው ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ስልጠና አጠናቃቂዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደገለጹት ሚንስቴር መስሪያቤቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ #ለአገር_ግንባታ ያለውን ፋይዳ በመረዳት በዘርፉ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
እንደ ሚንስትሩ ገለፃ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ስራዎች ሀገር በቀል እውቀትን መሰረት በማድረግ ዜጎች የሙያ ባለቤት ሆነው በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ብቁ ሰራተኞች የሚሆኑበትን አማራጭ ለማስፋት፣ ቴክኖሎጂን በመቅዳትና በመፍጠር ሂደት የሚሳተፉ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተፈላጊ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ነው፡፡
ከለውጥ ስራዎቹ ጋር ተያይዞም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ለዘርፉ አሰልጣኞችን፣ አመራሮችንና ቴክኖሎጂስቶችን የማቅረብ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ #አቅም የመፍጠር ስራ እንደተጀመረ ነው ሚንስትሩ የገለጹት፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና ባላቸው ጸጋ እንዲለዩ በቀረበው የትምህርትና ሥልጠና #ፍኖተ_ካርታ ጥናት መሰረት ኢንስቲትዩቱ በቴክኒካል ዩኒቨርሲቲነት እንዲደራጅ የተወሰ ሲሆን ከዚህ ቀደም ይሰራቸው የነበራቸውን መልካም ስራዎች አስፍቶና ተጨመማሪ ተልዕኮ ይዞ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ችግሮችን የሚፈቱ ባለሙያዎችን በጥራት፣ በአይነትና በብዛት እንዲሁም በደረጃም ጭምር አሻሽሎ እንዲያፈራ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት ኢንስቲትዩቱ #የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚል ስያሜ ይዞ ወደ ስራ ይገባል ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል የትምህርትና ሥልጠና ስራው ዘመኑ በደረሰበት #የዲጂታል ቴክኖሎጂ እየታገዘ የዘመነ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የቦርድ አባላትም የዩኒቨርሲቲውን #የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ከግንዛቤ ያስገባ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ተጨማሪ የቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚያስፈልግና የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ቀጣይ ለሚከፈቱት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል እንዲሆን እንደሚሰራ ዶ/ር ሳሙኤል ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉን እንዲደግፍና ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱና ሌሎች አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው ላደረጉት ድጋፍና ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩቱ ሲሰራቸው የነበሩትን ዋና ዋና ተግባራት አጠናክሮ ይሄዳል ያሉት አቶ ተሻለ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የአቅም ግንባታ ማዕከል መሆኑ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ያለውን የአሰልጣኞች እጥረት ለመቅረፍ ታሳቢ በማድረግ በ2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተደራሽነቱን ለማስፋት በስድስት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ውስጥ 15 የሳተላይት ማዕከል በመክፈት ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በእስካሁኑ ሂደትም ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡