አቁሜስ?
፨፨///፨፨
" ህልሜ እስኪሳካ፣ ሃሳቤ እውን እስኪሆን፣ ምኞቴ እስኪፈፀም፤ በሁለት እግሬ እስክቆም፤ አንገቴን ቀና እስከማደርግ፣ በኩራት መራመድ እስከምችል መቼም አላቆምም፤ ከጥረቴ አልገታም፤ ወደኋላም አልመለስም። "
ይህ ለእራስህ የምትገባው ፅኑ ቃል ነው። በምንም በማንም የማይናወጥ፣ የማይሸበር፣ የማይረበሽ ብርቱ ቃል ነው። ለቃልህ ታመን፤ አድርገህ ታይ፤ ሆነሀው ተገኝ። አቁም፤ አያዋጣም፤ አያዛልቅህም ስለተባልክ ብቻ እጅ አትሰጥም። እንዴት እንደ ጀመርከው፣ ለምን እንደጀመርከው አንተ ታውቃለህ። እውቀትህ ያለማቆምህ ምክንያት ነው። የጅማሬህን መጨረሻ ሳታይ የትም አትሔድም፤ መቼም እንዴትም አታቆምም።
አዎ! ጀግናዬ..! " አቁሜስ? ተስፋ ቆርጬስ? በእራሴ አዝኜስ? ስብራቴን አፍጥኜስ? ተብረክርኬስ? " ብለህ እራስህን ጠይቅ። ምን ይመጣል? ምን ይፈጠራል? እዛ የማትወደው ህይወት ውስጥ እንደገና ልትዘፈቅ? ያንን የማረረህን ልማድ ልትደጋግም? በተሳለቁብህ ፊት አንገትህን ልትደፋ? በቀለዱብህ ሰዎች ዳግም መቀለጃና መሳለቂያ ልትሆን? ማቋረጥህን ለማውራት ልትዘጋጅ? አለመቻልህን በአንደበትህ ልትናገር? አታደርገውም። ማቆም ትችላለህ፤ ተስፋ መቁረጥ፣ ወደኋላ መመለስ፣ ነገህን ማጨለምም ትችላለህ። ነገር ግን ከዛስ ቀጣዩ የህይወትህ ገፅ ምን ይመስላል? በአይነ ህሊናህ ሳለው፤ በጥልቀት ተመልከተው። ይህ ነው የምትለው፣ በኩራት የምትናገርለት፣ ውሃ የሚቋጥር፣ መኖርህን የሚያጎላ፣ ህይወትህን የሚያቃና አንዳች ነገር፣ አንዳች ታሪክ ሳይኖርህ ቀረህ ማለት ነው።
አዎ! ከማቆም ጀርባ ያሉትን፣ ተስፋ ከመቁረጥ፣ ፊትለፊትን ካለመመልከት፣ ራዕይን ካለመሰነቅ፣ ህልምን ካለመኖር ኋላ ያሉትን ትርጉም አልባ ሁነቶች አጢን፣ በጥልቀትም መርምራቸው። ህልምህን መኖር ቀላል ስላልሆነ ተስፋ ለመቁረጥ ትንደረደራለህ፣ በእራስ መቆም፣ በዓላማ መፅናት፣ ለእራስ መታመን፣ ትልቁን የመኖር ትርጉም ማግኘት ከባድ መሆኑ ግልፅ ነው፤ ነገር ግን ክበደቱ ግልፅ ስለሆነ ብቻ ለብርታት ያዘጋጅሃል፤ ከወዲሁ ያጠነክርሃል።እራስህን አታሳፍርም፤ በእራስህ ፊት፣ በሰዎች ፊት በእየአደባባዩ አንገት አታስደፋውም። ደረትህን ነፍተህ መሔድ የምትችለው ለማያውቅህ ሁሉ ማንነትህን ስታሳይ ብቻ ነው። መቻልህን አሳይ፤ ማድረግህን አስመስክር፤ አቅምህን ግለጥ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikreaimro 😊 💪