ብቻህን አይደለም!
፨፨፨//////////፨፨፨
እውቀት ንግግር አይደለም፤ ይልቅ መረዳት ነው፤ ጥበብ ትንተና አይደለም ይልቅ ማስተዋል፣ መገንዘብ ነው፤ አዎንታዊነት እንከን ፈላጊነት አይደለም ይልቅ እውነታውን ለማወቅ፣ ሚስጥሩን ለመረዳት ዝግጁ መሆን ነው። በእግዚአብሔር አምላኩ እያመነ፣ በቤቱ እየተመላለሰ፣ ጠዋትና ማታ ስሙን እየጠራ ለሚማፀንና ለሚለምን ሰው "አንተ አምላክህን አታውቅም፤ በፈጣሪህም አታምንም፤ እርሱንም እየተቃወምክ ነው።" ብሎ መፈረጅ እራስን ፃድቅ አድሮጎ ሌላውን እንደ ሀጥዕ ከመቁጠር አይተናነስም። ስለሰዎች የምናውቀው ጥቂት ሆኖ የምንናገረው፣ የምንተነትነውና አብዝተን የምናወራው ግን ብዙ ነው። እውቀትን በማውራት ለሚለካ፣ ጥበብንም በመተንተን ለሚተረጉም ሰው ሁሉን በአግባብ በስረዓቱ አንብቦ፣ አውቆና ተረድቶ እንዲገነዘብ እድሉን ከመፍጠር በቀር ሌላ ሊደረግ የሚችል ነገር የለም። እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በመልክና በአምሳሉ ፈጠረ፣ የህይወት እስትንፋስንም እፍ አለበት፣ በእርሱ መንፈስም ሞላው። ምድራዊው የሰው ልጅም የሰማያዊውን አባት መንነፈስ ተሞላ። ተዓምራቱም ያሉት የአምላኩን መንፈስ በአግባቡ መጠቀምና አለመጠቀም መሃል ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ብቻህን አይደለም! ትችላለህ ስትባል የሚያስችልህ አምላክ አለህ፤ ታደርገዋለህ ስትባል የሚያስደርግህ ፈጣሪ አለህ፤ ትወጣዋለህ ስትባል በደካማው የሰውነት ባህሪህ፣ በተሰባሪው ማንነትህ፣ ቶሎ በሚያዝነው ስብዕናህ አይደለም፤ ይልቅ ባንተ ላይ ሙሉ ስልጣን ባለው፣ በፈጠረህ፣ በሚያኖርህና ምድር ላይ በሚያመላልስህ ህያው አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍፁም መንፈስ ነው። እውቀትን ጥበብ ያላደረጉ በእውቀታቸው ይስታሉ፤ ግንዛቤን ከውስጣቸው ያላስገቡ ባነሰ አስተውሎታቸው ለትቺትና ተቃውሞ ይፋጠናሉ። ስለማታውቀው በማውራት ትኩረት ትስብ ይሆናል፣ ብዙ አዳማጭም ታገኝ ይሆናል፣ ነገር ግን የእውነታውን ምንነት ከቶ መደበቅ አይቻልህም። አስተዋይ ልቦና፣ የሚያመዛዝን ህሊናን ከአምላኩ የታደለ ሰው በሰውነቱ ቅንጣት ትምክህት አይሰማውም፤ በማንነቱ ፍፁም እንደሆነ አያስብም። ይልቅ ፍፁም የእግዚአብሔር መንፈስ ውስጡ እንዳለ ያውቃል፤ ትምክህቱ የሚጠፋው ሳይሆን ህያው ነፍስን ያደለው አምላኩ እንደሆነ በሚገባ ይገነዘባል።
አዎ! አምላክህ ባንተ እንዲመሰገን፣ ፈጣሪህ ባንተ እንዲከብር አብረሀው መስራትህን፣ ከፊትህም እርሱን ማስቀደምህን እንዳትረሳ። ንቁ ትውልድ ብቻውን የሚሮጥ ሳይሆን ከእግዚአብሔር አምላኩ ጀርባ የሚሮጥ፣ በተግባሩ ሁሉ ፈጣሪውን የሚያስቀድም ነው። ላንተ እንዲሰራ ሳይሆን ባንተ ላይ እንዲሰራ የፈቀድክ እለት የህይወት ተዓምራትህን መመልከት ትጀምራለህ። ከሃይማኖት መምህራኖችህ ተማር፤ እምነትህን ከማውራት በተሻለ በህይወትህ እንዲገለጥ አድርግ። ፃድቅ መስሎ የሚከስህ ሁሉ ፃድቅ አይደለም፤ ሀጥዕ መስሎ የሚከሰስ፣ የሚፈረጅ፣ የሚተች ሁሉ ደግሞ ሀጥዕ አይደለም። ፈራጅ እግዚአብሔር እያለ በፍፁም በባልንጀራህ ላይ የፍርድ እጅህን አታንሳ። ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ የሰጠሀውን ስፍራ ያውቃል፤ አዎንታዊነትህን ይረዳል፤ መልካምነትህን ይቆጥራልና በእርሱ መታመንህን እንዳታቆም። አምላኩን ይዞ ያፈረ የለምና በአንድ ሰሞን ተቃውሞ ልብህ አይረበሽ፤ ከመንገድህም አትገታ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikreaimro 😊 💪