ከብዛት ጥራት!
፨፨፨//////፨፨፨
ከብዛት ጥራት አጭርና ግልፅ መርህ። በዙሪያችሁ መቶ ሰዎች አያስፈልጓችሁም፤ በአንዴ ብዙ ስራ መስራት አይጠበቅባችሁም፤ ሁሉም ቦታ ለመገኘት መሯሯጥ አይኖርባችሁም፤ የምታውቁትን ሰው ሁሉ ለማስደሰት መጨነቅ አይኖርባችሁም። ቀላሉን መርህ አስታውሱ፦ "ከብዛት ጥራት" አለቀ። ኮተት አታብዙ፣ ህይወታችሁን ጥራት ባላቸው ሰዎች፣ ተግባሮችና ውጤቶች ሙሉ። ጥራት ያለው፣ ትርጉም የሚሰጥ፣ የተገደበና የተመጠነ ስራን ስሩ። አስር ቦታ ተበጣጥሳችሁ ከአስሩ አንዱንም ሳታገኙ እንዳትቀሩ ተጠንቀቁ። በሁሉ አማረሽ እሳቤ ሁሉን አጥታችሁ እንዳትቀሩ። ተሰብሰቡ፣ ጥቂቱን ወሳኝ ነገር ምረጡ፣ ዙሪያችሁን በተወሰነ ጠቃሚ ነገር ሙሉት። አስከዛሬ የተማራችሁትን ወይም የምታውቁትን ሁሉ በአንዴ ለማድረግ ብትሞክሩ ምንያህል ጭንቀት ውስጥ ትገቡ ነበር? ለአስሩም ጓደኞቻችሁ ጥሩ ለመሆን ስትሞክሩ ለራሳችሁ ምንአይነት ሰው ትሆኑ ነበር? እዚም እዛም፣ የሚመጥናችሁም የማይመጥናችሁም ቦታ እየተገኛችሁ ቢሆን የጊዜ አጠቃቀማችሁ ብሎም የህይወት ጥራታችሁ ምን ይመስል ነበር?
አዎ! ከብዛት ጥራት! ከምርጥም እጅግ በጣም ምርጥ፣ ከጥሩ እጅግ በጣም ጥሩ። በአማካኝ ነገሮች መከበብ አቁሙ፤ ዞሮ ዞሮ እዛው ከሆነ አካሔድ ውስጥ ውጡ። የትኛውም የሰው ልጅ ሊከተለው ከሚገባው የህይወት መርህ ውስጥ አንዱ "ከብዛት ጥራት" የሚለው መርህ ነው። አቅሙ አለኝ ወይም ጊዜ አለኝ ተብሎ ሁሉም ነገር አይነካካም፣ ሁሉም ነገር አይሞከርም። የያዙትን አንድ ነገር አድምቶ መስራት፣ የፈለጉትን አንድ ነገር እስከመጨረሻው መከተል፣ ለሚያውቋቸው ጥቂት ሰዎች ህይወት ቀያሪ ተግባርን መፈፀም። አዋቂ የሚባሉ ሰዎች ምናልባትም ብዙ ነገር ያውቁ ይሆናል የሚኖሩት ግን የመረጡትንና በህይወታቸው ለውጥ እንደሚያመጣ የሚያምኑትን የተወሰነ እውቀት ነው። ከሚታወቀው ጥቂቱ እንኳን ፍሬ ያፈራ ዘንድ ተመረጦ ሊከወን ይገባዋል። ልኬት የህይወት ጠዓም መሰረት ነው። እዚም እዛም ማለት አቁማችሁ የያዛችሁት ላይ ብቻ አተኩሩ።
አዎ! ጀግናዬ..! ራስህን ቆጥብ። ችሎታው አለኝ ብለህ ያገኘሀው ዛፍ ላይ አትንጠልጠል፣ ያየሀውን ነገር ሁሉ አትሞክር። ሁሉንም ነገር ለማየት በጣርክ ቁጥር የምርም ያንተ የሆነውንና ላንተ ህይወት የሚመጥነውን ነገር ታጣዋለህ። ጓደኞችህን መጥን፣ ስራህን መጥን፣ ውሎህን መጥን። ሰብሰብ በል፣ ጥራት ያለው ህይወት ለመኖር አማራጮችህን ገድባቸው። ከመደበኛው ትንሽ ከፍ ያለ ህይወት ከተለመደው የተለየና ጠለቅ ያለ እውቀትና ተግባርን ይፈልጋል። ከባዱ ነገር ብዙ ነገር መሞከር ሳይሆን አንድ የያዙትን ነገር እስከመጨረሻው ታግሎ ማሸነፍ መቻል ነው፤ የእውነትም ትልቅ ጥረትን የሚፈልገው ነገር ከብዙ ሰዎች ጋር ከአንገት በላይ መተዋወቅ ሳይሆን ከጥቂቶች ጋር ልብለልብ መተዋወቅ ብሎም መግባባት ነው። ህይወትህን በፈተና የተሞላች አታድርጋት። መርሁን ተግብረው። ብዙ ከማሳደድ ጥቂቱን ጥራት ያለውንና የሚጠቅምህን ነገር ብቻ በመያዝ አሳድግው።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪