በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተገነባው ትምህርት ቤት
----------------------------------
በጎንደር ከተማ ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እርጅና ተጭኖት፣ እንክብካቤ ርቆት ከመማሪያ ክፍል ጎዳና ሊወጣ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡
ኑሮዋን በአዲስ አበባ ያደረገችውና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሃንዲሷ አክሱማይት አብረሃ ወደ አካባቢው ባቀናችበት ወቅት ትምህርት ቤቱ የነበረበትን ጉድለት ማየትና መስማት ብቻ ለእርሷ በቂ አልነበረም፤ የቻለችውን ለማድረግ ተነስታ ያሰበችውን አሳክታለች፡፡
ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር ትምህርት ቤት ነው፡፡
በክፍሎቹ ውስጥ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ማግኘት ከባድ ነበር። ተማሪዎች እንጨትና ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ነበር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት፡፡ ትምህርት ቤቱም ለመማር ማስተማር ሄደቱ ምቹ አልነበረም::
የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ገጽታ ረፍት የነሳት አክሱማዊት ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ትምህርት ቤቱን ማደስ የሚል ዘመቻ ጀመረች፡፡
ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም እና በ ሀገር ውስጥ እና ከ ሀገር ውጪ ያሉ ህብረተሰቦችን በማስተባበር 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ስምንት የመማሪያ ክፍሎችን ማስገንባት ችላለች፡፡
ከዚህ በመቀጠል በፋሲል ክፍለ ከተማ ቀበሌ13 የንባብ ማዕከል ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗንም አክሱማይት ተናግራለች።
ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ አመት 670 ተማሪዎችን ተቀብሎ በፈረቃ ለማስተማር ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
ዘመቻውን ያስተባበረችው አክሱማይት አብርሃ እና በዘመቻው ላይ የተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ፡፡ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲
@MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲
@MOEOFFICIALNEWS ⇲◉