MINISTRY OF EDUCATION


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተገነባው ትምህርት ቤት
----------------------------------
በጎንደር ከተማ ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እርጅና ተጭኖት፣ እንክብካቤ ርቆት ከመማሪያ ክፍል ጎዳና ሊወጣ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡

ኑሮዋን በአዲስ አበባ ያደረገችውና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሃንዲሷ አክሱማይት አብረሃ ወደ አካባቢው ባቀናችበት ወቅት ትምህርት ቤቱ የነበረበትን ጉድለት ማየትና መስማት ብቻ ለእርሷ በቂ አልነበረም፤ የቻለችውን ለማድረግ ተነስታ ያሰበችውን አሳክታለች፡፡

ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር ትምህርት ቤት ነው፡፡

በክፍሎቹ ውስጥ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ማግኘት ከባድ ነበር። ተማሪዎች እንጨትና ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ነበር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት፡፡ ትምህርት ቤቱም ለመማር ማስተማር ሄደቱ ምቹ አልነበረም::

የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ገጽታ ረፍት የነሳት አክሱማዊት ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ትምህርት ቤቱን ማደስ የሚል ዘመቻ ጀመረች፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም እና በ ሀገር ውስጥ እና ከ ሀገር ውጪ ያሉ ህብረተሰቦችን በማስተባበር 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ስምንት የመማሪያ ክፍሎችን ማስገንባት ችላለች፡፡

ከዚህ በመቀጠል በፋሲል ክፍለ ከተማ ቀበሌ13 የንባብ ማዕከል ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗንም አክሱማይት ተናግራለች።

ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ አመት 670 ተማሪዎችን ተቀብሎ በፈረቃ ለማስተማር ወደ ተግባር ገብቷል፡፡

ዘመቻውን ያስተባበረችው አክሱማይት አብርሃ እና በዘመቻው ላይ የተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ፡፡ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉


የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት በቴክኖሎጂ የተደገፋ እንደሚሆን ተገለፀ።
----------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች ከተወጣጡ የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ባለሙያዎች ጋር እየተወያየ ነው።

በውይይቱም የ 2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የ 2013ዓ.ም እቅድ ይቀርባል።።

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ዳይሬክተር ወ/ሮ ካሳነሽ አለሙ የትምህርት ዘርፉን ጥራት የሚለካበት አንዱ መንገድ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት በመሆኑ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል።

በውይይት መድረኩ የተመዛኞችን የምዘና ውጤትና ትንተናን ጨምሮ ከምዝገባ እስከ ሰርቲፊክሽን ድረስ ያለውን ሂደት የሚያሳይ በቴክኖሎጅ የተደገፈ ዳታ ቤዝ ትውውቅ ይደረጋል፡፡

በመድረኩም የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ የ2012 በጀት ዓመት ሪፖርት ይቀርባል።

በቀጣይም የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘና የጥናት ሰነድ ላይና ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተመርቀው በሚወጡ መምህራን የሙያ ብቃትና ሌሎች የትኩረት አቅጣጫዎች ዘሪያ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉




የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በ አዳማ ከተማ ገዳ ሮበሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመለከቱ።

በትምህርት ቤቱ በግንባታ ላይ ያሉ እና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ት/ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በትምህርት ቤቱ 3 አዳዲስ ክፍሎች የተገነቡ ሲሆን 4 ከዚቀደም አገልግሎት የማይሰጡ ክፍሎች ታድሰው ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ መደረጋቸውን የአዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቢሹ ተናግረዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉




የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በ አዳማ ከተማ ገዳ ሮበሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመለከቱ።

በትምህርት ቤቱ በግንባታ ላይ ያሉ እና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ት/ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በትምህርት ቤቱ 3 አዳዲስ ክፍሎች የተገነቡ ሲሆን 4 ከዚቀደም አገልግሎት የማይሰጡ ክፍሎች ታድሰው ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ መደረጋቸውን የአዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቢሹ ተናግረዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉


የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በ አዳማ ከተማ ገዳ ኪሎሌ ቅድመ መደበኛ እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

4 ክፍሎች በባለሀብቶች እንዲሁም 2 ክፍሎች በ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተገነቡ ሲሆን 4 ክፍሎች ላይ የማሻሻል ስራ ተሰርቶ ዝግጁ ሆነዋል ሌላ 6 ተጨማሪ ክፍሎችም በግንባታ ላይ ይገኛሉ።

በቅጣይም ለመማር ማስተማሩ ሂደት ዝግጁ እንደሚሆኑ የ አዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቢሹ ተናግረዋል።

ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉


የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በ አዳማ ከተማ ገዳ ሮበሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመለከቱ።

በትምህርት ቤቱ በግንባታ ላይ ያሉ እና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ት/ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በትምህርት ቤቱ 3 አዳዲስ ክፍሎች የተገነቡ ሲሆን 4 ከዚቀደም አገልግሎት የማይሰጡ ክፍሎች ታድሰው ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ መደረጋቸውን አዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቢሹ ተናግረዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉








የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በ አዳማ ከተማ ገዳ ምቻሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

በትምህርት ቤቱ 3 አዳዲስ እና 3 የማሻሻል ስራ የተሰራባቸው ክፍሎችን ተመልክተዋል።

በትምህርትቤቱም የውሃ ቧንቧዎች እና የማንበቢያ ፖርኮች ተገንብተው ተጠናቀዋል

ትምህርት ቤቶቹም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መገንባታቸውን የአዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቡሹ ተናግረዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉




የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።
--------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ከእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግ ጋር በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ በበየነ መረብ መክረዋል።

የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና በስደተኝነት የሚኖሩ ህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የተማሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የመላክ ልምድ አላቸው ብለን እናምናለን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) የጎልማሶች ትምህርት በአዲስ ስልት ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩን አብራርተዋል።

መደበኛ ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በሚገባ እንዲረዱት 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ላይ ልዩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት እንደሚሰጥ ገለፀው የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግም መንግስታቸው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትምህርት መስክ የምትሰራቸው ስራዎችን ይደግፋል ብለዋል።

የእንግሊዝ መንግስት የትምህርት ዘርፉን ከሚደግፉ ሀገራት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ለዚህ ድጋፉ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉


ባለሃብቶችና ድርጅቶች የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር ጠየቀ።
------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።

በአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙትን ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውረው የተመለከቱት የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ባለሃብቶችና ድርጅቶች የትምህርት ዘርፉን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ በሰበታ ከተማ ያስገነባውን ዲማ ማኛ ትምህርት ቤት በመረቁበት ወቅት በሀገር ውስጥ የተሰማሩ ድርጅቶች በትምህርት ቤት ግንባታና በውሃ አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ በህዝቡ አስተዋፅኦ፣ በባለሃብቶች እንዲሁም በመንግስት ድጋፍ ከ 50ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ገልፀዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉


የትምህርት ሚኒስትሩ ምስጋና እና መልዕክት
-------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ እየሰራ ላለው ስራ እንዲሁም በሰበታ ዲማ ማኛ ትምህርት ቤት ለሰራው ስራ አመስግነው አሁንም ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቀርበዋል።

ሚኒስትሩ በህዝቡ አስተዋፆ ፣ በባለሃብቶች ድጋፍ እንዲሁም በመንግስት ድጋፍ ከ 50ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ገልፀዋል።

"በሀገር ውስጥ የተሰማራቹ ኩባንያዎች በሀገራችን ውስጥ የትምህረት ዘርፋ ችግር ውስጥ ስለሆነ ባላቹበት የትምህርት ሴክተሩን እንድታግዙ፣ ትምሀርት ቤቶችን እንድትገነቡ ፣ በ ውሃ አቅርቦት እንድትደግፉን ጥሪ አቀርባለው" ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ሚኒስቴር

ኩባንያዎች ለሀገራችን የልማት አጋር መሆናቹን እንድታስመሰክሩ ሲሉም ተናግረዋል።
ሼር ═══◉❖◉════
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉
◉⇲ @MOEOFFICIALNEWS ⇲◉




የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ ከ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ ሃላፊ ዊሊያም ዴሪ የትምህርት ቤቱን ቁልፍ ተረክበዋል።





20 last posts shown.

309

subscribers
Channel statistics