ኦርቶዶክስ መዝሙር ❖


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


💠 እንኳን ደና መጡ 💠
.
ጥያቄዎች ➱ @Orthodox_question
መዝሙር ➱ @Orthodox_mezemur
መፅሐፍ ➱ @Orthodox_book
መፅሀፍ ➱ @EOTC_books
ግጥም ➱ @Orthodox_poem
ፊልም ➱ @Orthodox_film
ግሩፕ ➱ @Orthodox25
ብራና ➱ @EOTC_library
.
💠 @EOTC_library_bot 💠
.
ለአስተያየቶ ➱ @Orthodox2_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


​​🌼 አበባዮሽ 🌼
#እሰይ_ደስ_ደስ_ይበለን

ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ። የዝማሬ ዳዊት ቻናል ለመላው ኢትዮጲያዊ መልካም አዲስ ዓመትን ይመኛል።

@Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




#ቀዋምያን

ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት 
ኡራኤል ወሩፋኤል/2/ 
ይትፌነዉ ለሣህል/2/
እምኀበ ልኡል/2/ 

#ትርጉም፦
ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት 
ኡራኤልና ሩፋኤል/2/ 
ከልኡል ዘንድ ለይቅርታ/2/
ይላካሉ ከልኡል/2/

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




💠👉 ጳጉሜ ለምን እንጠመቃለን?
🎤 ቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




Forward from: Vamos fixed game
✝ ​​እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሠን ✝
አሜን ፫




ገድሉ​​ ተአምራቱ

ገድሉ​​ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
አዝ
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አዝ
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው ተክልዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot




አምላከ ተክለሃይማኖት ማረን

አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት
አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃድቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት
አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት
አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot




ኢትዮጵያዊው ጻድቅ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/

አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና

ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot




ተክለሃይማኖት ፀሐይ

ተክለሃይማኖት ፀሐይ የአምላክ አገልጋይ /2/
ፀሐይ የአምላክ አገልጋይ/2/

የኢትዮጲያን ምድር /የባረካት/2
አስተማሪዋ /የሆንክላት/2
ይህንን አውቃ /ትዘምራለች/2
ተክለሃይማኖት /ትጠራሃለች/2
አዝ ......
አልጫው ጣፍጧል /በጸሎትህ/2
ብርሃን በርቷል /ለልጆችህ/2
በቃልኪዳንህ ፍጥረት /ጸደቀ/2
ተአምራትህም /በዓለም ታወቀ/2
አዝ .......
ምስክርህን /አምላክ ያከብራል/2
የነኩህንም እርሱ /ይጣላል/2
ፍርፋሪህን /ልቤ ናፈቀች/2
ያንተን በረከት /ስለወደደች/2
አዝ .....
በእግዚአርያ በፀጋዘአብ ተማጽኛለሁ
ልቤን ለእጅህ /ሰጥቼሃለሁ/2
ከአንተ ጋር ልኑር /ለዘላለም/2
የሚለያየን /ማንም የለም/2

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot




ተክለሃይማኖት ባህታዊ

ተክለሃይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሀል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሀል
አዝ
ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውኃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሀል
አዝ
ተሰባበሩ ጣኦታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot




አባ አባ ተክለሃይማኖት

አባ አባ ተክለሃይማኖት አቡዬ /2/
በለኒ በለኒ ወልድየ /2/
አዝ
አባ አባ - - - እንኳን ሰው ምድሪቱን
አባ አባ - - - ጦም አያሳድርም
አባ አባ - - - አምላከ ተክልዬ
አባ አባ - - - ብዬ አፍሬ አላውቅም
አባ አባ - - - ምድራዊ መልዓክ ነህ
አባ አባ - - - የእቲሳ አምበሳ
አባ አባ - - - ለደብረ ሊባኖስ
አባ አባ - - - አንተ ነህ ሞገሷ
አዝ
አባ አባ - - - ስማኒ ብያለው
አባ አባ - - - ሳለ በሰማይ
አባ አባ - - - ከኪሩቤል ተርታ
አባ አባ - - - ሆነህ ስትታይ
አባ አባ - - - ስምህም ሲጠራ
አባ አባ - - - ገድልህ ሲነገር
አባ አባ - - - እፁብ ድንቅ ያሰኛል
አባ አባ - - - የተሰጠህ ክብር
አዝ
አባ አባ - - - አባቴ እልሃለው
አባ አባ - - - ልጄ ሆይ በለኝ
አባ አባ - - - የአባትና የልጅ
አባ አባ - - - ፍቅርህ ይጽናልኝ
አባ አባ - - - ንፍሮ ውሃ ጠጥቼ
አባ አባ - - - ታምር አይቻለሁ
አባ አባ - - - እባብና ጊንጡን
አባ አባ - - - ተረማምጃለሁ
አዝ
አባ አባ - - - እለት በለት ሄጄ
አባ አባ - - - ደጅ ስጠናው
አባ አባ - - - ይሰማል ተክልዬ
አባ አባ - - - ዛሬም ህያው ነው
አባ አባ - - - እንቆቅልሽ ፈቶ
አባ አባ - - - ደስ አሰኝቶኛል
አባ አባ - - - የተክለሃይማኖት
አባ አባ - - - ቡራኬው ደርሶኛል

#ሼር
@Orthodox_mezemur

@metshaf
@EOTC_library_bot



20 last posts shown.

686

subscribers
Channel statistics