Forward from: AASTU STUDENTS UNION OFFICIAL
GDSC AASTU እና Ahamenes Space Science and Technology Club በጋራ በመሆን 10 ለሚደርሱ ት/ቤቶች የልምድና የዕውቀት ማጋራት አደረጉ።ታኅሣሥ 14 2016 ዓ.ም በነበረው ዝግጅታቸው፣ ሁለቱ የግቢያችን ክበባት ከ10 ትምህርት ቤቶች በተወጣጡ ወደ 200 ገደማ የሚጠጉ ተማሪዎችን ስለ ክበባቸው ምን ዓይነት ሥራዎችን እንደሚሰሩ ወደፊት ለሚሰሩት ሥራ ተማሪዎች በምን መልኩ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገለጻም ተደርጎላቸዋል።
ከዚህ በመቀጠልም በአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ሬጂስትራል እና አልሙናይ በግቢው ውስጥ ስለሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች፣ በተለይም ደግሞ ስለ Software Engineering እና Space Science ያላቸውን ጠቀሜታ በማብራራት በተቀሩትም የትምህርት ዘርፎች በኢንደስትሪው ዘርፍ እንዴት ምርታማ እና አትራፊ ሊሆኑ የሚችሉበትን ከተጨባጭ የትግበራ መንገዶች ጋር ገለጻ አድርገዋል።
በስተመጨረሻም ከተሳታፊ ተማሪዎች ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዛ ላይ ማብራሪያዎችን በመስጠት በጎግል እውቅና ያለው የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ለተማሪዎቹ በመስጠት መርኃ ግብሩ ተደምድሟል።
እነዚህን መሰል ዝግጅቶችም ወደፊት እንደሚቀጥሉ የክበባቱ ተጠሪዎች የገለጹ ሲሆን፣ የግቢያችን ተማሪዎችም በሚኖራቸው የትርፍ ሰዓት ትርፋማ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ክበባቶች ላይ በመሳተፍ ብዙ እውቀትና ልምድ ከትምህርታቸው በተጨማሪ እንዲያካብቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው የተማሪዎች ሕብረት ሕዝብ ግንኙነት ነው