👀~~~~~~ዓይንናስ በሉኝ~~~~~~👁
✂️ሰዎች በተለምዶ አላህ የሠጣቸዉን ፀጋ መሠረት አድርገው አንዱ በሌላው መቀናናቱ የተለመደ ነው፡፡ በሃይ ስኩልም ሆነ በዩኒቨርስቲ ሰነፍ በተማሪ በጎበዙ ይቀናል ሌላው ቀርቶ በዒልም ቦታ ላይ ደረሳው በደረሳው ጧሊበል ዒልሙ በጡላበል ዒልሙ ሊቀና ሁሉ ይችላል፡፡ ደሃ ሰው ሀብታሙን ሰው ይመቀኛል፡፡ መልከጥፉዋ ሴት በቆንጆዋ ትናደዳለች ትቃጠላለች፣ በመሥሪያ ቤት የማይወደደው በሚወደደው ይቀናል፣ ከፍ ሲልም ይመቀኛል፡፡
.
🔖ምቀኝነት ከሚታይባቸው ቦታዎች መካከል የትምህርት ማዕከላት ይጥቀሳሉ፡፡ ከምቀኝነት ዉጤቶች መካከል ደግሞ ዐይን/ሒስድ እና ድግምት ዋንኞቹ ናቸው፡፡
📊ይህም ብዙ ግዜየ ሚከሰተው በዚያ ግለሰብ አንድን ነገር የሚያይ ሰው ይደነቃል፤ በአድናቆትም ሳያበቃ መጥፎ ነገር ያስባል፤ ምቀኝነትና ክፉ ነገር ይመጣበታል፡፡ ያ መጥፎ እይታ አደገኛ ቀስት ነው ሰዉን ይወጋል፣ ህመም ላይም ይጥላል፡፡ ለዚህም ነው አንድን አስደናቂ ስታዩ ሱብሓነላህ! ማሻአላህ ! በማለት በአላህ አፈጣጠር ተደነቁ፣ አላህንም አወድሱ የሚባለው፡፡
ስለዚህ አህባቦቼ! አማኝ ሁሌም ራሱን መፈተሽና መገምገም አለብት፡፡ ዙርያዉን ምሽጉን ማጠናከር አለበት፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ብርቱና የተጋ መሆን አለበት፡፡ ጠልፈው ሊጥሉት የከበቡት ጠላቶቹ በርካታ ናቸውና፡፡ ለጥቃት ላለመጋለጥ ሶላቱን በአግባቡ የሚሰግድ፣ ከወንጀል የሚርቅ፣ ሲያጠፋ ቶሎ የሚመለስ፣ በኃጢኣት የማይዘወትር፣ የአላህን ክልከላና ትዕዛዙን የመጠበቅ ሁኔታው ከፍ ያለ መሆን አለበት፡፡ ሴቶች በተለይ ተንኮሉ በነርሱ ላይ ይበዛልና መሳነፍ የለባቸዉም፡፡ ብርቱና የማይሸነፉ መሆን አለባቸው፡፡ በእምነታቸው የማይጠራጠሩ፣ ሒጃባቸዉን አስተካክለው የሚለብሱ፣ ንፅህናቸዉን የሚጠብቁና በተቻለ መጠን በዉዱእ የሚንቀሳቀሱ መሆን አለባቸው፡፡
በዚህ መልኩ ራሣችንን በመጠበቅ ቀዳዳዎች ካልደፈንን የሸይጣን መጫወቻ ነው የምንሆነው፡፡ በዐይነናስ፣ በመተትና በድግምት የተነሳ ብዙ ተማሪዎች ከመንገድ ቀርተዋል፤ ከዓላማቸውም ተሰናክለዋል፡፡
« አላህ በዐይንናስ እየተሰቃዮ ያሉ እህትና ወንድሞቻችንን ዓፊያቸውን ይመልስላቸው እኛንም ከስኬት የሚያሰናክሉንን የጁንም ሆነ የሰው ሸረኛ ያንሳልን‼
✍ ~~~አቡ ሱፍያን~~~
@AbuSufiyan_Albenan
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan