Forward from: أبو الناموس الأثري ""ከጦሳ ማዶ ደሴ ""
👌 አጭር ጥቆማ 👌
🔺=====👌=====🔺
ከሚያስቁኝ ፖስቶች የትዳር ፖስት
----------------🔺---------🔺----------------
👇🔺 ምክሩን ባልቃወምም ሳነባቸው ሳቄን ከሚያመጡት ፖስቶች ውስጥ የትዳር ፖስት አንዱ ነው ። ብዙው የተጋነነና ማስመሰል የበዛበት ፖስት ነው ። ሁሉም ሳይሆኑ አብዛሐኛዎቹ ወንድምና እህቶች ይህችን ፖስት ካበዙ ለማጨት መንገድ ላይ እንደሆኑ ማሳያ ነው ። አዎ ወይም ያሰበችው ያሰባት አለች ወይም ተጫጭተው ጨርሰዋል ወይም አድስ ተጋብተዋል ። ስለዚህ የትዳር ፖስት ራስን መልአክ ማስመሰያ ሜካፕ ነው ። አዎ ከታዘብኩት እውነታ ሲያጩ ወይም እጮኛ ሲፈልጉ የትዳር ፖስት ያበዛሉ ። የትዳር ፖስት አንዱ ራስን የማሳያ ዘዴ ሲሆን ቀይ ጥምጣም ከሽቱጋ ጀለብያ ከነጥምጣሙ አብሮት ከተለጠፈማ ጭራሽ እዚህ ነኝ ብሎ ለፈላጊው ጅ ፒ ኤስ ሎኬሽን መክፈት ነው ። አቡ እንትና ይሰማል .❓
ነግሬካለሁ እነዚህ የተለጠፉ ጨርቆች የነገር ከፈን ሊሆኑ ስለሚችሉ ዘው አትበል አስብ አስተውል ... ድኗን ፀባይዋን በደንብ ከታማኝ ከሚያዝንልህ ትዳርህን ከሚወድልህ ከማይመቀኛት ሰው አጣራ ።
-----
👌🔺 ትዳርን በደላላ ግፊት ብቻ ከያዝከው እንደ ጨረቃ ቤት ድንገት ይፈርስልካል ። ደላላ ቤት ሲሸጥልህ ይሔ አካባቢ ለዋና ከተማነት ታጭቷል እያለ እንደሚያባብልህ እሷንም የነብዩን ልጅ ፋጡማን አድርጎ ይስልልካልና ተጠንቀቅ ።
------
👌 አዎ የfb የትዳር መካሪዎች አቡ እንትና ድንገት ተነስቶ ሚስቶቻችንን እንውደዳቸው እናክብራቸው እንዘንላቸው እያለ ደሊሉን ሲያዘንበው ባህሪው የነብዩን ባህሪ ሊመስል አንድ ዙር እስከሚቀረው ይመክራል ። ነገር ግን እህት ዓለም ይሔ የልጁ ፅሁፍ እንጂ እሱ አይደለም ። በወሬ አትሸንገይ አጣሪ በደንብ ጠይቂ ብዙው ጨካኝ ፅሁፍን እንደ ወጥመድ ላይ ሽንኩርት ይጠቀማልና ።
-------
🔺👌እሷም ኡሙ ፉላና በፅሁፍ ስትመክር ባለቤትሽን ወደ ስራ ሲሔድ ኮቱን አልብሽው ሲመለስ በር ላይ ተቀበይው ሳም አድርጊው እያለች ትመክራለች ። ባጭሩ ኸድጃን ልትመስል አንድ ዙር እስከሚቀራት ምክሩን ስታዘንዘውና ስትደረድረው መቼ አንብባው ነው ትላለህ ..❓
ገንፎው አቡ ፉላን ይሔንን ባዬ ጊዜ በቃ ይህችን ካገባ እንደ ፅሁፏ ካንከባከበችው ቤቱም ቤተ መንግስት እሱም ንጉስ የሚሆን ይመስለዋል ። ወንድም አጣራ በፁሁፍ ዘው ብለህ ገብተህ ኮትህን ሳይሆን ቆዳህን እንዳታወልቅልህ መሳሟ ቀርቶ እንዳትነክስህ ከበር በነገር እንዳትቀበልህ ። ጠንቀቅ በልና ማናት ብለህ ሸሪዓ እንዳዘዘህ አጣራ በfb ከመጣች ግን በfb ትሔዳለች ።
------
በትዳር ንፍቅና ይቁም
🔺👌https://t.me/AbuNamuse/5720
--------