ከቋሚ ኮሚቴዎች የተውጣጣ ቡድን አቶ #ክርስቲያን ታደለን እና #ጫላ ዋታን (ዶ/ር) በማረሚያ ቤት አነጋገሩ
ከሕግና ፍትሕ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲሁም ከአማካሪ ኮሚቴ አባል የተውጣጣ ቡድን አቶ ክርስቲያን ታደለን እና ጫላ ዋታን (ዶ/ር) በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተግኝቶ አነጋገረ፡፡
አቶ ክርስቲያን ታደለ በማረሚያ ቤቱ ጠበቃቸውን በተናጠል ከሚያገኙት ይልቅ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት አካላት በጋር በመሆኑ ጠበቃቸውን አብረው ማናገር ሲፈልጉ ተጨማሪ ሰዓት ቢፈቀድ የሚል ጥያቄ ለቡድኑ ማንሳታቸውን ከህ/ተ/ም/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጫላ ዋታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት፤ የምግብ መጠን እና ጥራት ጋር ያለውን ችግር ማረሚያ ቤቱ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ በማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎች የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት እና አገልግሎት አሰጣጥ፤ ታራሚዎችን በቤተሰብ የመጎብኘት ሁኔታ ምን እንደሚመስል እንዲሁም የሰብአዊ አያያዝ እና የዲሞክራሲ መብቶቻቸው ጋር በተያያዘ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡
በሰኔ ወር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በማረሚያ ቤት የሚገኙ የምክር ቤት አባላቱን አያያዝ መመልከቱን ይታወሳል።