የ #አንካራ ስምምነትን ተከትሎ የ #ሶማሊያ ልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ #አዲስ_አበባ ይገባል
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጉብኝቱ በአንካራው ስምምነት መሰረት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የልዑካን ቡድኑ በጋራ ጥቅም እና ትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለመፍጠር የለውጥ ዕድሎችን በማሰስ ላይ እንደሚያተኩር ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የሶማሊያ መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሉዓላዊነት እና በግዛት አንድነት መርሆዎች ላይ የጸና ግንኙነት ለመፍጠር ባለው ራዕይ ቁርጠኛ መሆኑ ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በባሕር በር ሳቢያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ታህሳስ 2/ 2017ዓ/ም በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በአንካራ ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል።