በቁሙ ለሚቃዠው የሙነወር ልጅ ሸይኽ ዶ/ር ሑሴን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ በማለት ፅፈዋል:-
“የተምይዑ ዋሻ የሙነወር ልጅ ንግግር መጣረስ ለምንድነው የበዛው??
በእርግጥም ብዙ የንግግሩን ግጭቶች፣ የርስበርሱን መጣረስና አላዋቂነቱን እንዲሁም በበርካታ ንግግሮቹ ላይ በሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸለይ "በአሻዒራዎች ላይ አወድሷል" በማለት መቅጠፉን፣ በሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ አደም "ከዩሱፍ አልቀርዷዊ አንስተዋል" ብሎ መቅጠፉን፣ ይባስ ብሎ ነቢዩ ﷺ ከኸዋሪጆች ከማስጠንቀቃቸውም ጋር "ኸዋሪጆችን አወድሰዋል" በማለት መቅጠፉን አውስተናል።
የሙነወር ልጅ ከጠንካራው የሰለፎች ጎዳና ወደ ጥመት ለመዘንበሉ ሰበብ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ፣ በሱንና ዑለማዎች ላይ አለመማሩ ነው፣ ከሱና መሻይኾች አንደበት እውቀትን አለመያዙ ነው።
የሰለፊያን አስተዳደግም አላደገም፣ እውቀት የያዘው ያለ አስተማሪዓሊም ከመፅሃፍና ከመፅሃፎች ሆድ በራሱ ግንዛቤ ነው።
ስለዚህ አንተ ሰለፊይ ወንድሜ ሆይ! አላህ ይጠብቅህና የሙነወር ልጅ ለቢድዐህና ለጥመት ባለቤቶች በመከላከሉ አትደነቅ (እንግዳ ነገር አይሁንብህ)፣ ነገ ተነስቶ ከሰልማን አል-ዐውዳ፣ ከሰፈረል ሀዋሪ፣ ከሰይድ ቁጥብ፣ ከቀርዷዊና ከዐብደላህ አል-ሀረሪ ቢከላከል አትደናገጥ አትገረም። ምክንያቱም የሙነወር ልጅ ማለት በራሱ በደመነፍስ የሚጓዝ እንጂ በዑለማዎች እጅ በሱንና ተኮትክቶ ያደገ አይደለምና፣ ለዚያም ነው ሸይኽ አልባኒ (ረሂመሁላህ) በብዙ ሙሃዶራዎቹ የሚያዘውትርባት የነበረችው ጥሪው (التصفية والتربية) የምትል የነበረው።
ይህ ማለት በትክክለኛው እስልምና ውስጥ ሰርጎ ከገባበት ነገር ማጥራትና ነቢዩ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው በነበሩበት መንገድ ተኮትክቶ ማደግና ኮትክቶ ማሳደግ ማለት ነው።
ነቢዩ ﷺ ሶሃቦችን ሐቅን በመከተልና ሐቅን ከሁሉ ነገር በማስበለጥ ነው ኮትክተው ያሳደጓቸው፣ ለዚያም ነው ተኮትክተው ያደጉ ቀደምቶች እንዲህ ያሉት:- “ወዮልህ መቀያየርን ተጠንቀቅ! የአላህ ዲን አንድ ነው።” መቀያየርና የንግግር መጣረስ ደግሞ የሱንና ዑለማዎች የተከሉትን ሱንና አጥብቆ ያልያዘ ሰው መለያ ነው። የሙነወር ልጅ፣ ሳዳት ከማል፣ ሙሀመድ ሴራጅና… ሌሎችም የሚገለባበጡና የሚቀያየሩ የሆኑት ሙመይዓዎችን ይመስል።
ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተን እስክንገናኝ ድረስ ልባችን በዲንህ ላይ አፅናልን!!” [ሸይኽ ሑሴን ኖቬምበር 7/2024]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa