⛳️መብት
⛳️ለሰው ልጅ ጥሩ ወይም መጥፎ የመምረጥ ሙሉ መብት ከከባድ ሀለፊነት ጋር ማጎናፀፍ የኢስላም ልዩ ባህርይ ነው፡፡
አላህ ለሰው ልጅ በሠጠው በዚህ ልዩ መብት የሰውን ልጅ አክብሮታል ይሁን እንጅ መብቱ ተጠያቂነትንም ጭምር ያዘለ በመሆኑ በፍረዱ ቀን ለምን ዓላማ እና ተግባር እንደተጠቀመበት ይጠይቀዋል፡፡
ይህ ለሰው ልጅ የተሠጠው የመምረጥ ነፃነት አላህ በፍጡራኑ ላይ የሚከሰተውን እያንዳንዱን ነገር ያውቃል ከሚለው ሀሳብ ጋር በምንም መልኩ አይቃረንም።
⛳️እዚህ ላይ «አላህ ነገ ሀጢያት እንደምንሰራ የሚያውቅ እስከሆነ ሀጢያቱን ከመስራት የመታቀብ ምንም እድል የለኝም፡፡
ምክኔያቱም የአላህ እውቀት እንከን የለሽ እና ተግባራዊ ከመሆን የሚመልሰው ኃይል የለም ተብሏልና” የሚል ሀሳብ ሊነሳ ይችላል፡፡
ማንም ሰው ምን እንደሚወስን አላህ አስቀደሞ ያውቃል ማለት ሰውየው የሚወስነውን ውሳኔ ሁሉ እንድፈፅም ያስገድደዋል ማለት አይደለም፡፡
አንድ ሰው ጥሩ አልያም መጥፎ ውሳኔ ሊወስን ይችላል፡፡
ሆኖም ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ወይም የመተው ሙሉ መብት የግለሰቡ ነው፡፡
የሰው ልጅ የፍላጎቱን የመምረጥ አላህ በፍጡራኑ ላይ የለውን የልዕለ-ኃያልነት ሥልጣንም የሚጋፉ አይደለም፡፡
እንድሁም ያለ አላህ ፍቃድ በፍጡራኑ ላይ ማንኛውም ነገር አይከሰትም የሚለውን ሀሳብም አይቃረንም፡፡
አንድ ሰው የመምረጥ ነፃነት የሚባለው ነገር ሊሆን የማይችል እንደሆነ አድርጎ ሊያስብ ይችላል፡፡
አንድ ነገር ልብ ልንል ይገባል ፤አላህ ለእያንዳንዳችን የፍላጎት አቅጣጫ የመተለምና ትልማችንን የመተግበር ችሎታ የሠጠን በመሆኑ አላህ የምርጫችንን የምንሠራ አድርጎ ፈጥሮናል፡፡
አንድ ሰው የምርጫውን ሲሠራ አላህ የሰውየውን ፍላጎት እንድፈፅም የሚያስፈልጉትን ነገሮች እና ሁኔታዎች በመለኮታዊ ችሎታው ያሟላለታል፡፡
⛳️የሰው ልጅ የፍላጎቱን የመምረጥ ነፃነት የኔ ገኘው በአላህ ፍላጎት ነው፡፡አላህ ሰዎች በሚያሳልፉት ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን የመምረጥ ነፃነት ተጠቅመው ይህንን ውሳኔ ለመወሰን እንድችሉ ብቃቱን ሰጥቷቸዋል፡፡
ለምሳሌ:-አንድ ሰው ጥሩ ነገር ለመስረት
ያስባል፡፡ሆኖም ለመስራት አስቦት የነበረውን ጥሩ ነገር ሳይተገብረው ይቀራል፡፡ያ ሰውዬ በተግባር ባያውለውም ጥሩ ነገር ለመስራት አስቦ ስለነበር ብቻ ከአላህ ምንዳ ያገኛል፡፡ ቢተገብረው ደግሞ አላህ ለበጎ ሃሳቡም ለበጎ ተግባሩም ምንዳ ይከፈለዋል፡፡
አላህ በአንድ በኩል ጥሩ ነገር ለመስራት ስለታሰበ ብቻ ምንዳ ሊከፈል በሌላ በኩል ግን መጥፎ ተግባር ለመፈፀም ታስቦ ሳይተገበር ቢቀር አይቀጣም፡፡
⛳️•በኃይማኖት ማስገደድ የለም
~~~
አንድ ሰው ሙስሊም ሊሆን የሚችለው በፍላጎቱ ሙስሊም መሆንን ሲመርጥ ብቻ ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረው ዓላማ በገዛ ፍላጎቱ አላህን ይገዛ ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም የእምነት ድርጊት ዋጋ ሊኖረው የሚችለው የሰው ልጅ የመምረጥ ነጻነቱ ተጠቅሞ በመቀበል ሊፈፅለው ብቻ ነው፡፡
አንድ ሰው ማንኛውንም እምነት ተገዶ እንዲቀበል ቢደረግ እምነቱ የይስሙላና ፍሬ ቢስ ይሆናል።
ደጉ አላህ «በኃይማኖት ማስገደድ የለም፤ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፣ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው፣ ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በርግጥ ጨበጠ፣ አላህ ሰሚ አዋቂ ነው፡፡ »📕ቁርዓን (2:256)
ብሏል፡፡
⛳️Ali Dawah
https://t.me/AliDawah2