መጽሐፍ ቅዱስ በማን ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስ በማን ተጻፈ? የሚለውን ርዕስ ከማየታቸውን በፊት መቼ ተጻፈ? የሚሉትን በቅድሚያ በጥቂቱ እንመልከት
⛳️የመጽሀፍ “ቅዱስ” ሁለቱም ክፍሎች ማለትም ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን የተጻፉበት ዘመን አንደማይታወቅ የክርስትያን የሐይማኖት ምሁራን ይናዘዛሉ፡፡ በዚህ አጀንዳ ዙሪያ የሚነገሩ ነገሮች በሙሉ ከመላምትነት የዘለሉ አይደለም፡፡ በዘመነኛ ምሁራን እንደሚታወቀው ግን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ13ኛው እስከ 1ኛ ክፍለ ዘመን ባሉት 1200 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ሰዎች መጻፋቸውን ይገምታሉ፤፤”📕(The History of Quranic text p230)
ይህም ማለት የመልእክቱ ባለቤት የሆነው ሙሴ ከሞቱ ከበርካታ ምእተ አመታት በኋላ ተወጥነው የተጠናቀቁ መጽሐፍ እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡
⛳️የአዲስ ኪዳን የተጻፉበትን ዘመን በተመለከተም እንዲሁ እርግጠኛ ነገር ማግኘት አይቻልም፡፡ በአብዛያዎቹ ምሁራን ዘንድ ተቀባይት ያገኘው ሃሳብ እንደሚያመለክተው “ወንጌል” እንደሆነ የሚታመነው የማርቆስ ወንጌል በ68 ዓመተ ልደት አከባቢ ማለትም እየሱስ ካረገ ከ35 ዓመታት በሃላ እንደተጻፈ ይገመታል፡፡ የመጨረሻ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ደግሞ ከ100-125 ዓ.ል ማለትም እየሱስ ካረጉ ከ70-90 ባሉት ዓመታ ውስጥ መጻፈተ ተገምቷል፡፡ የሉቃስ ወንጌል በ90 ዓ.ል ማለትም ከእየሱስ እርገት ከ60-80 ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደተጻፉ በምሁራን ተግምቷል፡፡ ከዚህም የምንረዳው ሳስቱም ወንጌሎች እየሱስ በሕይወት ሳለ አልተጻፉም ፡፡ እየሱስ ጋረገ ከበርካታ አስርት አመታ በኋላ የተጻፉ ናቸው፡፡ ሌሎች የአዲስ ኪዳን ክፍሎችም እስከ 150 ዓ.ል ባለው ጊዜ ውስጥ እንደተዋቀሩ ይገመታል፡፡ 📕(F.C Grant The Gosples: Their origine and Their Growth, Faber and faber,24 russel square, Lendone 1957, p20-21.)
⛳️ከዮሐንስ ወንጌል ውጭ ያሉት ቀሪ ወንጌሎች የይዘት ተመሳሳይነት ያላቸው (Synoptics) እንደሆኑና ዩሐንስ ከነርሱ በተለየ እንደሆነ በምሁራን ዘንድ ይታመናል ፡፡ የማርቆስ ወንጌል ለሉቃስና ለማቴዎስ ወንጌሎች በምንጭነት ሳያገለግል እንዳልቀራ ይገማታል፡፡ የዩሐንስ ወንጌል በይዘቱ ከ3ቱ ወንጌሎች ጋር እስከ ተቃርኖ የሚደርስ ልዩነት ያለው በመሆኑ ከማርቆስ ወንጌል እንዳልተቀዳ ምህራን ጽፈዋል፡፡
ኢንሳይክሎፒድያ አሜሪካ ላይ የሚከተለውን አባባል እናገኛለን፡- “If the synoptic are accepted as outhentic, the unourthenticity of john must follow.” “ተመሳሳይ የሆኑት (ሦስቱ) ወንጌሎች ትክክል ናቸው ማለት፤ የዮሐንስን ወንጌል ውድቅ ማድረግ ማለት ነው”
⛳️በዮሀንስ ወንጌልና በሌሎች ሶስት ወንጌላት መካካል በግልጽ የሚታይ ልዩነት በመኖሩ የወንጌሉ ታአማኒነት አጠያያቂ እንዲሆን ምክኒያት ሆኗል” ምንጭ 📄(ሜሪል ሲ.ቴኒ፤ የአዲስ ኪዳን ቅኝት፤ አሳታሚ የኢትዮጲያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የኮሚኒኬሽን ስነ ጹሁፍ መምሪያ፤ ገጽ 281)
⛳️የማቴዎስና የሉቃስ ወንጌል ምንጭ የማርቆስ ወንጌል ሳይሆን እንደማይቀር ምሁራን ገምተዋል ፡፡ ከማርቆስ በተጋዳኝ ሌላ ምንጭ ሳይተቀሙ እንዳልቀሩ ሊቃውንት ይገምታሉ ፡፡ ይህም ምንነቱ ያልታወቀ ምንጭ አጥኝዎች Q በሚለው ፊደል ወክለውታል ፡፡ ይህ Q የተባለ ምንጭ የባርናባስ ወንጌል ሊሆን ይችላል የሚል መላምት የሰነዘሩ ምሁራን አልጠፉም ፡፡ አንድ ሳይሆን ወጥነት የሌላቸው የተሌዩ ምንጮች ሊሆን እንዲሚችሉአጥኝዎች ገምተዋል ፡፡ ይህ Q የተባለ ምንጭ ምን ያህል ታማኝ እንደሆነ፤ እውነታዎችስ ምን ያህል እንዳካተተ፤ የዘነጋቸውና ያላሰፈራቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ያከላቸውና ያዛባቸው ነገሮች ስለመኖራቸው ፤ ከርሱ የቀዱ ጻሐፊዎች ምን ያህል በታማኝነት እንደቀዱ ፤ የቱን ትተው የቱን እንደወሰደ ወዘተ ምንም የሚታወቅ ነገር ባለመኖሩ ታሪካዊና ሐይማኖታዊ ፋይዳቸው እምብዛም ነው፡፡ 📕(Encyclopidia Britanica 1960 v137 p825) ይመለከቱ፡፡
⛳️አሁን ደግሞ እስቲ የጻሐፊዎች ማንነት እንመልከት #
፨ የብሉይ ኪዳን ሁሉም ጻሐፊዎች ማንነት በውል እንደማይታወቅ የክርስቲያን ምሁር ራሳቸው ይመሰክራሉ፡፡ ሙሴ ጽፏቸዋል ተብለው በዘልማድ ይገመቱ የነበሩ መልእክቶች እንኳ እርሱ እንዳልጻፋቸው ጥናቶች እያረጋገጡ መጥተዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ ይህ መጽሐፍ ማን እንደጻፈው አይታወቅም” የሚሉ ዓረፍተነገሮች ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ ተከታዩን የስነ መለኮት ሊቃውንት ምስክርነት ይመልከቱ፡-
ኦሪት “ከጥንት ጀምሮ አምስቱ የሙሴ መጽሐፍት በመባል ይታወቃል በ10ኛው ክ/ዘ ገዳማ ጀምሮ ግን አንዳንድ መምህራን ኋለኞች ነብያት ጸሐፊዎች በእስራኤልና በይሁዳ መንግስት ዘመን ከምርኮ በኋላ ባለው ዘመን ጹሑፎችንና የቀደሙ የባህል ህጎች ሰብስበው አቀነባበሩአቸው፡፡በእነሱም ዘመን ኦሪት መልክ ሊይዝ ይችላል የሚል ግምት አላቸው፡፡ይሁን እንጂ ጉዳዩ በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያነት ዘንድ አጨቃጫቂ ሆኖ ተገኝቷል” 📜(የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 189)
መጽሐፈ እያሱ “መጽሐፈ እያሱ የጻፈው ማን ነው? የሚለው ጥያቄ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን አከራክሯል፡፡ ሦስት የተለያዩ ሀሳቦች አሉ፡፡
1.ኛ መጽሐፈ እያሱ የተጻፈው በታሪክ ውስጥ የሚገኙ ድርጊቶች ከተጻፈው በታሪክ ውስጥ የሚገኙ ድርጊቶች ከተፈጸሙ ከ8 ዓመት በኋላ ነው፡፡የተጻፈውም ኦሪት ዘዳግምንና 2ኛ ነገስት ያሉትን ሌሎች የታሪክ መጽሐፍትን በጻፈው ሰው ስም ነው፡፡
2ኛ መጽሐፉን የጻፈው እያሱ ነው ፡፡ይህም ስለሞቱ ከሚነገረው በቀር መጽሐፉን በሙሉ የጻፈው በሚለው የአይሁድ አመለካከት አለ፡፡
3ኛ ከእያሱ ዘመን በኋላ ምናልባትም በሳሙኤል ጊዜ መጽሐፈ እያሱ ተጽፎ ወይም ተቀናብሮ ይሆናል፡፡
ስለዚህ መጽሐፈ ኢያሱ ፀሐፊው አይታወቅም፡፡ ነገር ግን የመጽፉ ስራ የተጠናቀቀው በዳዊት ጊዜ በ1000 ዓ.ዓለም ነው ማለቱ ይሻላል፡፡📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 342-343)፡፡
⛳️የመጽሐፈ መሳፍንት “ጸሐፊ ማን እንደሆነና እነዚህ የተለያዩ ተግባራት አሰባስቦ በአንድ ላይ ያቀናበራቸው ማን እንደሆነ የሚያመለክት ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም ፡፡ዓለማውያን ምሁራን መጽሐፍ የተጻፈበትን ጊዜ በማዘግየት በዚህ መልክ የጻፈው ኦሪት አዳግም የጻፈውንና ከኢያሱ እስከ 2ኛ ነገስት ያለውን የታሪክ ዘገባ ያቀናበረው ሰው ነው ይላል፡፡ ሆኖም ለዚህ ሁሉ አንዳች ማረጋገጫ የለም፡፡ አይሁድ የጻፈው ሳሙኤል ነው ብለው ያምናሉ፡፡
📜(ቲም ፌሎስ የብሉ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ ገጽ 370)፡፡
“መጽሐፉን ማን እንደጻፈው እና ምን ጊዜ እንደተጻፈ እርግጡ ባይታወቅም እንኳ የፃፈው ሳሙኤል ወይም በሳሙሴል ዘመን ከነበሩት ከነብያት ወግን አንዱ እንደሆነ ይታመናል፡፡” 📜(የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 34)