ዓምደ ሃይማኖት


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️✟

         


“የአእላፋት ዝማሬ በመንፈስ ቅዱስ የተሰናዳ የሰላም መዝሙር ነው" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ



መዝሙሮቹን ለማግኘት 👇👇

https://t.me/janyared_2


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!! 

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ  ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ  #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize  #ANTEXETHIOPIA  #ANTEXTEXTILE  #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
+ በዓታ ለማርያም +

ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡   
በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግቷል፡፡  

በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፪  ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
ሐዋርያዉ ታዴዎስ ፣ ሠለስቱ መዕት ፣ ቅድስት አትናስያ ፣ አቡነ እንድርያኖስ ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ ፣ አባ ጉባ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪

የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤና በዓለ ንግሥ
በጓንጓ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወቅድስት አርሴማ ገዳም

ታኅሣሥ ስድስት ቀን የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል ደምቆ ይከባራል።

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቅድስትቤተክርስቲያን ተመለሰ

+ 70 ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ +

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ማዕተብ በኩል 70 ወጣቶች ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በልጅነት ጥምቀትና በቄደር ጥምቀት ተመለሱ::

ጃን ማዕተብ ሥራ ከጀመረ ጊዜ አንሥቶ በአንድ ለአንድ (የገፅ ለገፅ) የትምህርት መንገድ የተማሩት እነዚህ ንዑሰ ክርስቲያን ከእስልምና ከፕሮቴስታንት ከካቶሊክ እና እምነት የለሽነት የተመለሱ መሆናቸውን የጃን ማዕተብ የንዑሰ ክርስቲያን ክትትል አስተባባሪ ዶ/ር ቤተልሔም ገልጻለች::

"በወላጆቻቸው ፣ በትዳር አጋሮቻቸውና በወዳጆቻቸው ጥቆማ ወደ እኛ የሚመጡትን ወጣቶች በመጀመሪያ ያሉበትን የግንዛቤ ደረጃ የመመዘኛ ቃለ መጠይቅ ካደረግንላቸው በኋላ በየርእሰ ጉዳዩ በጠነቀቁ (specialize ባደረጉ) መምህራን አንድ ለአንድ እንዲማሩ በማድረግ መምህረ ንስሓ በማገናኘት እስከጥምቀት ድረስ የማብቃትና የመከታተል ሥራዎችን ስንሠራ ቆይተናል" ያሉት የጃን ማዕተብ ሰብሳቢ ዲ/ን እርሱባለው ኩምሳ "ከተጠመቁት መካከል በሚገባ ተምረው በንዑሰ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ከእኛ ጋር ማገልገል የጀመሩም አሉ" በማለት ገልጸዋል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር የተቀላቀሉት ወጣቶች መካከል በሔዱባቸው ቦታዎች እስከ ሰባኪነት የደረሱና አንዳንዶቹም "የተሐድሶ" ሥልጠና ሠጪዎች የነበሩም እንዳሉበትና ለወራት በአንድ ለአንድ ትምህርትና ሱባኤ ጉባኤ በመማር ላይ እንደሚገኙ ተገልጾአል:: ከእነዚህም መካከል አስቀድሞ በዘማሪነት ሲያገለግል የነበረውና ወደ ተሐድሶ ተወስዶ የነበረው ዘማሪ ሐዋዝም ላለፉት ስምንት ወራት በጃን ማዕተብ ሲማር ቆይቶ በይፋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቄደር ጥምቀት ተመልሶ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይፋዊ የይቅርታ ደብዳቤውን አቅርቦአል::

ጃን ማዕተብ በብዙ ድካም የሠራውን የፕሮጀክት ምክረ ሃሳብ በመተግበርም በቀጣይ ጉዳይ ተኮር የሆኑ የዕቅበተ እምነት ጉባኤያትና ዐውደ ጥናቶችን በማዘጋጀት ሒደት ላይ መሆኑን የገለጸው ዲ/ን እርሱባለው "ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት" ላይ ማተኮርና የንዑሰ ክርስቲያን የመግቢያ ትምህርት ዶክመንት የማዘጋጀት ሥራዎችም እየተሠሩ መሆኑን ገልጾአል::

በጃን ማዕተብ የተሰናዳው "ወደ ኦርቶዶክስ (ወደ ቀናችው ሃይማኖት) መመለስ" የተሰኘ ዕቅበተ እምነታዊ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ማታ በጃንደረባው ሚድያ ቻናል ይለቀቃል::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#በፍጹም_ልብህ_ብታምን_ተፈቅዶአል

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ጾመ ነብያት ነገ እሑድ ኅዳር 15 ይገባል ።

ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ::

(ዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ኅዳር 12

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ!!


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
+ ምጽዋት +

ምጽዋትን ለተቸገረ ወገኑ የሚሰጥ ሰው ለእግዚአብሔር መስጠቱ ነው ።

፦ ምጽዋት ለእምላክ የሚሰጥ ብድር ነው ።
፦ ምጽዋትን የሚመጸውት ለችግረኛ የሚራራ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል በስጦታውም መጠን እግዚአብሔር ይከፍለዋል( ምሳ19፥17 ሲራ 29፥1)


ምጽዋት ብልህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስቀምጡት አደራ ነው ። ገንዘብ /ንብረትን/ በታመነ ሰው ዘንድ ማስቀመጥ /አደራ ማስጠበቅ / የተለመደ ነው። በፈለጉት ጊዜ የሚገኝ ስለሆነ ።

"ያላችሁን ሽጡ ሽጣችሁ ምጽዋት ስጡ የማያረጅ ከረጢት ለእናንተ አድርጉ የማያልቅ ድልብም በሰማይ ሌባ ከማይደርስበት ነቀዝ ፣ ብል ከማያበላሹበት ገንዘባችሁ ካለበት ልባችሁ በዚያ ይኖራል ። ሉቃ 12-32 ማቴ 6-19-21 እንዲል ማለት ነው ።

ምጽዋት ሰው ለሰው ያለው በጎ ፈቃድ የሚገለጥበት ክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር ዘርፍ ነው ። በዚህ ዓለም ጥረት ከራሳቸው ተርፈው ለሌሎች ማካፈል ችግረኞችን መርዳት የሚቻላቸውን ብቻ ሳይሆን በመጠነኛ ኑሮ የሚተዳደሩ ደጋግ ሰዎች ያለንን ተመግበው ለሀብታችን ለዕውቀታችንና ጉልበታችን ሳስተን የምንኖር ከሆነ መንግሥተ ሰማያትን በምን እንወርሳለን ? ብለው ከሚበሉት ከሚጠጡት ከፍለው ይረዳሉ ይመጸውታሉ ። በኑሮአቸው በዝቅተኛነት የመስጠት ፈቃዳቸውን የልግስና ብልፅግናቸውን አያግደውም ። ከአቅማቸው የሚያልፍ እንኳ ቢሆን ጨክነው ያደርጉታል ። ፪ኛ ቆሮ ፰-፪ ።( ኪዳነ ጽድቅ ገጽ 96-97 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ"

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
(የአህያን ስም በአሳማ በአይጥ በውሻ ወዘተ እየቀየሩ ዐረፍተ ነገር ይሥሩ:: ሃሳቡ ያው ነው) ግዝረትም የማይበሉ ምግቦችም ከ613 የአይሁድ ሕግጋት (The 613 Mitzvot) ውስጥ ናቸው::

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ቄራ (የበሬ)

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" ኤፌሶን 4:29

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ የማይነገር መቃተት +


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ። 8፥26

የማይነገር መቃተት ምንድ ነው ? ከተባለ ፦ መቃተት አስጨናቂ በሆነ ነገር መድከም ማለት ።

የመቃተት ትርጉም መልፍት ፣ መድከም ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ይለፍል ፣ ይደክማል ማለት ነው ወይ ተብሎ ከተጠየቀ፦ መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል እንደሚረዳን ወይም እንደሚያግዘን ይገባን ዘንድ (ይረዳን ዘንድ ) ለሰው ልጆች በሚነገረው አነጋገር ስለ ተነገረ ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደክምም ተብሎ ይመለሳል ። የማነገር መቃተት የሚለው መንፈስ ቅዱስ ይደክማል ተብሎ ስለማይነገር  ነው ። መንፈስ ቅዱስ ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ጭንቅላቴ ዞረ አይልምና ። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ይህን የመሰሉ አነጋገሮች ይገኛሉ ።

በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ አረፈ (ዘፍ 2፥2 ) እግዚአብሔር ሥራ ሰርቶ ድካም አይሰማውም ። ዕረፍትም አያስፈልገውም ። ለሰው ልጆች በሚገባቸው አነጋገር ለመግለጽ ነው እንጂ ። አንድም የሰንበትን ዕረፍ ለሰው ልጆች ለመሥራት ነው ። "ጌታችን ያረፈበት ቀን ሰንበተ (ዕረፍት) ተብሎአልና ። እስራኤል በኃጢአት ላይ ኃጢአት ሲጨምሩ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት "ሸክም ሆነብኛል ልታገሣቸውም  ደክሜያለሁ " ብሎአል (ኢሳ.1፥14 ) ። እግዚአብሔር እንደ ሰው በትግዕሥቱ አይደክምም ። ወይም እንደ ሰው ትዕግሥቴን ጨርሻለሁ አይልም። "ልታገሣቸው ደክሜያለሁ " ማለቱ ፦ ብዙ ቢተገሣቸውም ከኃጢአታቸው የማይመለሱ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው እንጂ ። ( የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ከሮሜ እስከ ገላትያ ትርጓሜ/ማብራርያ መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ -106)

#ዓምደ_ሃይማኖት


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር
***
በብዙ መልካም የሆነ ሰውን አንድ ክፉ ነገር ብናይበት ብዙ መልካም ነገሩን ሳይሆን ክፉ ነገሩን አይተን ጉድለት ይሰማናል። አእምሯችን ነጭ ወተት ላይ አንዳረፈ ዝንብ ክፉውን ትኩረት ሰጥቶ ያያል፤ ልባችንም መውደድ ይከብደዋል። ይህ ግን የሥጋ እውቀትና ግብር ነው።
እግዚአብሔር እንደዚህ ቢሆን ኖሮ መወደድ እና መዳን አይገኝም ነበር። በእርሱ ዓይን ብዙ ክፋታችን የተገለጠ ነውና። ነገር ግን እርሱ መልካም ስለሆነ በኃጢአት እየኖርን ጠላቶቹ እያለን ወደደን፤ ያውም እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር። ለዚህ ቸርነትና ፍቅር አንክሮ ይገባል! (ሮሜ. 5፥10)
ይህ አምላካዊ ቸርነት በእኛ ዘንድ ለእምነት፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ምንጭ ነው። እምነት ማለት ሳይገባን ክፉዎች ሆነን የወደደን እና ቀድሶ እና አክብሮ መልካም ልጆቹ ያደርገን ዘንድ ወደ እርሱ የጠራን አምላክ መኖሩን ተረድቶ በእርሱ ታምኖ መኖር ነው። ከዚህም ምሥጋና እና ደስታ ይወጣል። (ዮሐ. 14፥1)
ፍቅር ደግሞ በሥራ እግዚአብሔርን መምሰል ነው፤ እሱ ያለ ጥቅም እና ማዳላት ሁሉን ይወዳልና፤ ጠላቶች ሆነን ሳይቀር ወዶናልና። በእኛ ውስጥ ያለውን ክፋት አይቶ ሳይተወን መልካም አድርጎ መፍጠሩን አስቦ ሊያድነን መጥቷልና።
ተስፋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ርስትን እየጠበቁ መከራን መታገስ እና የክርስቶስን መምጣት መጠበቅ ነው። እኛን ያድን ዘንድ አንድያ ልጁን ለመከራ አሳልፎ የሰጠ መልካሙ እረኛችን እና አባታችን የማይሰጠን ምን ነገር አለ? የሚጠቅመንን እና ቃል የገባልንን ሁሉ ይሰጠናል። (ሮሜ. 8፥32)
ፍቅር ግን ከሁሉም ይበልጣል አለ ሐዋርያው። እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ሕግን ሁሉ ፈጽሟልና። (1ኛ ቆሮ. 13፥13)

( በረከት አዝመራው )


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ ተለቀቀ +

🩸 አዲስ ድንቅ ዝማሬ 🩸

በ5ቱ ዘማርያን🔊

👇👇 👇👇
OPEN   OPEN OPEN 
OPEN   OPEN OPEN 
OPEN   OPEN OPEN


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
+ የእመቤታችን ምስጋና ትርጓሜ +

የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሴ ቅዱስ ያደረባትን የኤልሳቤጥን ምስክርነት ከሰማች በኋላ "ነብሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኅኒቴ ሐሤት ታደርጋለች" በማለት ክብር የባሕርይ ገንዘቡ የኾነ በማሕፀኗ በፈቃዱ ያድር ዘንድ ለወደደ ለአምላኳ ያላትን ክብር ገልጻለች ነብዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ በመንፈስ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በምዕ ፳፩-፲ ላይ ፦ "አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና የጽድቅንም መጎናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች " በማለት ትንቢት እንደተናገረ ቅድስት ድንግል ማርያምም የንጽሕናን የቅድሰት ጸጋና ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም ያበቃትን ርሱን ደስታን በተመላ በዚኽ ቃል አመሰግናለች።


ሐሴት" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሳ ዘጠኝ ጋዜ በላይ ሲጠቀስ ክቡር ዳዊት በመዝ ፷፯-፫ ላይ " ጻድቃንም ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፈት ሐሤት ያድርጉ በደስታም ደስ ይበላቸው" ሲል ነቢዩ ዕንባቆምም በምዕ ፫፥፲፰ ላይ "እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኅኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለኁ " በማለት ፈጣሪውን እንዳመሰገናት "ደስተኛዩቱ ደስ ይበልሽ " የተባለች የባሕርይ አምላክን በማሕፀኗ የተሸከመች ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇን "መንፈሴም በአምላኬ በመድኅኒቴ ሐሤት ታደርጋለች " በማለት በደስታ ኾና አመሰገነችበት ። ( "ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን" በመጋቢ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ገጽ 205-206)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

20 last posts shown.