ፈገግ ለማለት ያህል ...
°
°
"እውነትም ዝምታህ ጠቅሞሀል!"
ኢማሙ አቡ ሐኒፋን (አላህ ይዘንላቸውና) በተደጋጋሚ ጥያቄ ከሚጠይቋቸው ሰዎች ዘንድ የሚቀማመጥ አንድ ሰው ነበር።ሰው ሁሉ ሲጠይቅ ይህ ሰው ግን ያዳምጣል እንጂ አይጠይቅም። አያወራምም።የዚህን ሰው ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ያስተዋሉት አቡ ሐኒፋም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦
አቡ ሐኒፋ "ሰው ሁሉ ጥያቄ ሲጠይቅና ሲያወራ አንተ ግን አትናገርም።ጥያቄ የለህም ነው? ወይስ ምን ሆነህ ነው?" አሉት።
ሰውየው "ጥያቄስ አለኝ ያ ኢማም!" አላቸው።
አቡ ሐኒፋም "እንግዲያውስ ጠይቅ እንጂ!" አሉት።
ሰውየውም "መች ነው ፆመኛ የሚያፈጥረው?" ብሎ ጠየቀ።
አቡ ሐኒፋም "ፀሐይ ስትገባ ፆመኛ ያፈጥራል።" አሉት።
በዚህን ጊዜ ሰውየው "ፀሐይዋ ዙሁር ላይ ብትገባስ?" ብሎ ጠየቃቸው።
አቡ ሐኒፋም ፈገግ ብለው "እውነትም ዝምታህ ጠቅሞሃል!" አሉት
@ashrefnassermenzuma