ስብሃት በዚህ ድርሰት ውስጥ ኢ-ርቱዕ ሙግቱን ለአንባቢ
ካቀበለ ለማሳየት እሞክራለሁ፤ የዚህ ጽሑፍ ዓቢዩ ጉዳይም በዚህ በቀጣዩ ክፍል የተተነተነው ነው፡፡
ሰይጣን መነፅሩ - በ‹ስምንተኛው ጋጋታ›
***
ሰይጣንን በአካል በልቦለድ ውስጥ መቅረፅ በ“ዘመናዊ”
ስነጽሑፋችን አልተለመደም፡፡ በተለይ በ“መደበኛው
ልቦለድ” (mainstream fiction) ሰይጣንን ገፀባሕርይ
አድርጐ መሳል እንግዳነት አለው፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ደፋር
ተንታኞች የዓለም ሥነ-ጽሑፍ በተለይም ረጅም ልቦለድ
ያለሰይጣን/ያለእርኩስ መንፈስ የኖረበት ዘመን የለም
እስከማለት ይደርሳሉ፡፡ በዓለም ሥነ-ጽሑፍ ታላላቅ ተብለው
ከሚጠቀሱት ደራሲዎች መሃል እንደነ ዳንቴ አሊጌሪ፣ ጆን
ሚልተን፣ ክርስቶፈር ማርሎ፣ እነ ዎልፍጋንግ ገተ፣ እነ ሚኻይል
ሌርሞንቶቭ፣ ሚኻይል ቡልጋኮቭ እና አሌክሳንደር ፑሽኪን፣ እነ
ሔንሪክ ኢብሰን፣ ማርክ ትዌይን፣ ጆርጅ በርናንድ ሾ፣ … እና
ሌሎች ቢያንስ ስማቸው እንግዳ የማይሆንብን እና
ተተርጉመውም ያነበብናቸው ደራሲዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ባለፉት
ሁለት ሦስት ዐሥርት ዓመታት በተረታዊ አጻጻፉ ከዓለም ብዙ
የመጻሕፍት ቅጂ ሻጭ ደራሲዎች አንዱ የሆነው ፓውሎ
ኮዬልሆም ሰይጣንን በቀጥታ በገፀ ባሕርይነት ካመጡት
ደራሲዎች ዝርዝር ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡
ስብሃት በ‹ሰባተኛው መልአክ› ባካተታቸው ሁለት “ፋንታሲ”
ሥራዎቹ ውስጥ - ለዚህ ጽሑፍ በተመረጠው በ“ስምንተኛው
ጋጋታ” እና በ“አጋፋሪ እንደሻው” - ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ
አድርጐ ቀርጿል፡፡ ባለታሪክ፣ ባለሚና አድርጐ በድርሰቶቹ ውስጥ
ተርኮታል፡፡ ይኽ ጽሑፍ በሰይጣን አሳሳል ወይም በእንግዳነቱ
ሳይሆን፤ ይኽ መንፈሳዊ ገፀ ባሕርይ ወደ ድርሰቱ በገባበት
ሰበብ እና በተላለፈበት ጭብጥ ላይ ነው ያተኮረው፡፡
መርማሪነት፣ የሰው ልጅ ባሕርይ ነው፡፡ መጠየቁ የማኅበራዊም
የግላዊም ዕድገቱ መሠረት ነው፡፡ መጠየቁ የመሻሻሉ
የመበልፀጉ መነሻ ነው፡፡ ካልጠየቀ በቃኝ ባይ ይሆናል፤
ካልጠየቀ ለውጥ አይሻም፤ ካልተለወጠ ዕድገትና ውድቀት
የሚባሉ ሂደቶችን አያልፍም፡፡ ተፈጥሯችን ግን እንዲያ ሆኖ
ለመኖር አይፈቅድልንም፡፡ እናም- እንደሰውነታችን-
እንጠይቃለን፡፡ ስለምንጠይቅም ዛሬ፣ ትላንት እና ከትናንት
ወዲያችን አንድ አይደሉም፡፡ እጓለ ገብረ ዮሐንስ የሰው ልጅ
አካባቢውን አሜን ብሎ ተቀብሎ በኖረበት ዘመኑ፣ “የተፈጥሮ
ችሎታውን ባለማወቅ … በዙሪያው የሚገኙት የሥነፍጥረት
ጉልበቶች መጫወቻ ነበር፣” ይላሉ (የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣
ገፅ 97)፡፡
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር፣ በ“ስምንተኛው ጋጋታ”፣ ጠያቂነት
እንደነውር የሚያስወቅስበት እንደ ሃጥያት የሚያስወግዝበት
እንደ ወንጀል የሚያስቀጣበትን፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አኗኗር
ነቅፏል፡፡ በተለይ ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ አድርጐ በተረከባቸው
ገጾች ስብሃት ይኼን ሥርዓት ሲቃወም መርማሪነትን ሲያበረታታ
እናገኘዋለን፡፡ ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ አድርጐ ማምጣቱም
ሁልጊዜም ከአንድ አቅጣጫ የሚፈስ “እውነት” ተቀባይ
መሆናችን የዋህነት መሆኑን ለማመልከት ይመስላል፡፡
በታሪኩ ውስጥ ሰይጣን በሦስት የተለያዩ ሁኔታዎች
ያጋጥመናል፡፡ በያዙት ጭብጥ ተቀራራቢነት በተለይ ሁለቱን፣
ማለትም ሰይጣን ከኢየሱስ ጋር በሲኦል የተወዳጀበትንና ከዋና
ገፀ ባሕርይው ከአቶ አልአዛር ጋር ያደረገውን የስልክ የሐሳብ
ልውውጥ በማንሳት፤ ስብሃት መርማሪነትን በተረታዊ ድርሰቱ
አማካይነት አበረታቷል ያስባለኝን ለማስረዳት እሞክራለሁ፡፡
የሃይማኖት መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት ሰይጣን ከእግዜር
በታች ከሰው በላይ ሆኖ ምድርን በክፋቱ የሚገዛት፣ የዚህች
ዓለም ገዢ ነው፡፡ ሰይጣን፣ ሳጥናኤል በትርጉሙም፣ “ሰግዶ
አሰጋጅ” ተብሎ አስቀድሞ የተሰጠውን የመላዕክት አለቅነት
በገዛ እጁ ያጣ፣ በአምላኩ ላይ አምጾ ክብሩን የተነጠቀ
መንፈሳዊ ፍጡር ነው፡፡ የፈጣሪውን ዙፋን በመመኘቱና
ፈጣሪውን በማስቆጣቱ ወደ ምድር ተጥሏል፡፡ አዳምና ሄዋንን
አስቶ ከእግዜር መንገድ አስወጥቶ ፀጋቸውን አስገፍፏል፡፡
ለሞትም መምጣት ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ የኢዮብንም
ትግስት ተፈታትኗል፤ የኢየሱስንም ያርባ ቀን ጾም፣ የ3 ዓመት
ከ3 ወር ተልዕኮ ለማክሸፍ ሞክሯል፡፡ እናም ሰይጣን
የእግዚአብሔር ተቃራኒ የሰው ልጆችም ጠላት እንደሆነ
የሃይማኖት አባቶችና መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡
የስብሃት ድርሰት ግን ሰይጣንና ኢየሱስን ያወዳጃል፡፡
ሃይማኖታዊውን እውነት የምናይበት ሌላ መነጽር ያጠልቅልናል፡፡
ወይም እውነቱን ለማየት ከቆምንበት አቅጣጫ በተቃራኒው
አቁሞ ያየነውን በሌላ ዐይን ያሳየናል፡-
“ኢየሱስ ፍቅር ነውና አዳምን ወዶት ሊያድነው የሞትን ወንዝ
እንደተሻገረ ሁሉ፣ ሰይጣንንም ወዶት በስደት አገሩ በሲኦል
ሊጠይቀው የዘላለምን ወንዝ ተሻገረ፡፡
ሰይጣንም በግዞት አገር ሊጐበኘው የመጣውን እንግዳ እደጀ
ሰላም ድረስ ወጥቶ ተቀበለው፣ ይወርድ ዘንድ አህያውን
ባለሻኛውን ያዘለት፣ ይገባ ዘንድ በሩን ከፈተለት…” (127-8)
በዚህ ክፍል ሰይጣን እንግዳው ኢየሱስን ጠላና ቆሎ አቅርቦ
ከጨዋታ ጋር አስማምቶ ያስተናግደዋል፡፡ ኢየሱስ ሲኦል ድረስ
የወረደው የሰይጣንን ወዳጅነት ፈልጐ አይደለም፡፡ ሰይጣንን
“አታሎ” ነፍሳት ሊሰርቀው እንጂ፡፡
ሰይጣንና ኢየሱስ በሰዎች ነፍሳት ላይ የየራሳቸው ፍላጐቶች
አሏቸው፡፡ ሁለቱም እነዚያን ነፍሳት ይፈልጓቸዋል፡፡ የስብሃት
ኢየሱስም ከሰይጣን የተወዳጀ የመሰለው በሰይጣን ግዛት
(ሲኦል) ከታሸጉት ነፍሳት ወደራሱ ግዛት በዘዴ ለመውሰድ ብሎ
መሆኑን እናያለን፡፡
“ሳቀ ኢየሱስ ከት ብሎ ሳቀ፣ ሲኦል ግድግዳው ተሰነጠቀ፣
ነብሳት ነቁ በስንጥቁ፣ በሺ በእልፍ እየወጡ አመለጡ፡፡ ሰይጣን
ይህን አልጠረጠረ፣ 'ንገረኝ አብሬህ ልሳቅ፣' አለ፡፡” (129)
የስብሃት ኢየሱስ፣ “ወንድሜ ሳጥናኤል ሆይ፣” እያለ ሰይጣንን
እያባበለ የሰይጣን ንብረት (ዜጐች) የሆኑትን ነፍሳት ዘርፎታል፡፡
ስብሃት ግን እዚህ ጋር ቆም ብለን፤ የኖረውን ትረካ ገልበጥ
አድርገን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ማታለል የሰይጣን ተግባር
ሆኖ ሳለ፣ በዚህ ትረካ ውስጥ ግን አታሎ መዝረፍ የኢየሱስ
ሆኗል፡፡ በርግጥ ሰይጣን ሲያታልል ሞትን ለሰው ልጆች አመጣ፤
ኢየሱስ ሲያታልል ነፍሳት ዘላለማዊ የደስታ ኑሮ እንዲኖሩ
ያደርጋል፡፡
ኢየሱስና ሰይጣን በተወዳጁበት በዚሁ ክፍል የተነሳን ሌላ
ሁኔታም እናንሳ፡-
“ውድ ወንድሜ ሳጥናኤል ሆይ፣ እስቲ የምድርን ነገር አንሳና
ስለ ሰው ልጆች አጫውተኝ፡፡ መሬት ስጋ አብቅላ አድጐ
ሲያብብ፣ ያበበው ጠውልጐ ሲረግፍ፣ በሌላ አበባ ሲተካ
የሚነግር ወሬ ጨዋታ አምጣ፡፡ እገሌ እንዲህ ሆነ እንዲህ
ደረሰበት የሚል ጨዋታ፡፡ ተረት ብጤ ጨዋታ...” (129)
ኢየሱስ ለሰይጣን የ“እንደምን ላስተናግድህ” ጥያቄ ስለምድር
የሚያወራ ተረት ብጤ ጨዋታ እንዲያጫውተው ጠይቆታል፡፡
ሰይጣን ደግሞ እንደ እንግዳ ተቀባይነቱ የእንግዳውን ጥያቄ
ተቀብሎ የእንግዳውን ሐሳብ ለመሙላት ካዲሳባ ተረት ይዞ
መጥቷል፡፡
...ከዚያማ ሰይጣን ተረቱን ጀመራታ.. የመኖር የመሞት ጨዋታ፣
ኩኩሉ አይነጋም ጨዋታ፣ አየሁሽ ለየሁሽ ጨዋታ፣ እንቁልልጭ
ሙልልጭ ጨዋታ፣ እንቆቅልሽ ቆቅ ታንቆልሽ ጨዋታ፡፡
አቶ አልአዛር... ቤታቸው በራፍ ሊደርሱ ጥቂት እርምጃ
ሲቀራቸው እንቅፋት መታቸውና ወደቁ፡፡ ተነሱ፣ ሰውነታቸውን
ደባበሱ፣ ልብሳቸውን አራገፉና ወደ ቤታቸው በር ራመድ
ራመድ...
ኧ..? ቤታቸው ከስፍራው የለም፡፡ ኧ..? (130)
አቶ አልአዛር የድርሰቱ ዋና ባለታሪክ ናቸው፡፡ አቶ አልአዛር አንድ
ጊዜ የውሽማቸውን ቤት በሌላ ጊዜ የራሳቸውን ቤት ከስፍራው
አጥተዋል፡፡
ካቀበለ ለማሳየት እሞክራለሁ፤ የዚህ ጽሑፍ ዓቢዩ ጉዳይም በዚህ በቀጣዩ ክፍል የተተነተነው ነው፡፡
ሰይጣን መነፅሩ - በ‹ስምንተኛው ጋጋታ›
***
ሰይጣንን በአካል በልቦለድ ውስጥ መቅረፅ በ“ዘመናዊ”
ስነጽሑፋችን አልተለመደም፡፡ በተለይ በ“መደበኛው
ልቦለድ” (mainstream fiction) ሰይጣንን ገፀባሕርይ
አድርጐ መሳል እንግዳነት አለው፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ደፋር
ተንታኞች የዓለም ሥነ-ጽሑፍ በተለይም ረጅም ልቦለድ
ያለሰይጣን/ያለእርኩስ መንፈስ የኖረበት ዘመን የለም
እስከማለት ይደርሳሉ፡፡ በዓለም ሥነ-ጽሑፍ ታላላቅ ተብለው
ከሚጠቀሱት ደራሲዎች መሃል እንደነ ዳንቴ አሊጌሪ፣ ጆን
ሚልተን፣ ክርስቶፈር ማርሎ፣ እነ ዎልፍጋንግ ገተ፣ እነ ሚኻይል
ሌርሞንቶቭ፣ ሚኻይል ቡልጋኮቭ እና አሌክሳንደር ፑሽኪን፣ እነ
ሔንሪክ ኢብሰን፣ ማርክ ትዌይን፣ ጆርጅ በርናንድ ሾ፣ … እና
ሌሎች ቢያንስ ስማቸው እንግዳ የማይሆንብን እና
ተተርጉመውም ያነበብናቸው ደራሲዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ባለፉት
ሁለት ሦስት ዐሥርት ዓመታት በተረታዊ አጻጻፉ ከዓለም ብዙ
የመጻሕፍት ቅጂ ሻጭ ደራሲዎች አንዱ የሆነው ፓውሎ
ኮዬልሆም ሰይጣንን በቀጥታ በገፀ ባሕርይነት ካመጡት
ደራሲዎች ዝርዝር ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡
ስብሃት በ‹ሰባተኛው መልአክ› ባካተታቸው ሁለት “ፋንታሲ”
ሥራዎቹ ውስጥ - ለዚህ ጽሑፍ በተመረጠው በ“ስምንተኛው
ጋጋታ” እና በ“አጋፋሪ እንደሻው” - ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ
አድርጐ ቀርጿል፡፡ ባለታሪክ፣ ባለሚና አድርጐ በድርሰቶቹ ውስጥ
ተርኮታል፡፡ ይኽ ጽሑፍ በሰይጣን አሳሳል ወይም በእንግዳነቱ
ሳይሆን፤ ይኽ መንፈሳዊ ገፀ ባሕርይ ወደ ድርሰቱ በገባበት
ሰበብ እና በተላለፈበት ጭብጥ ላይ ነው ያተኮረው፡፡
መርማሪነት፣ የሰው ልጅ ባሕርይ ነው፡፡ መጠየቁ የማኅበራዊም
የግላዊም ዕድገቱ መሠረት ነው፡፡ መጠየቁ የመሻሻሉ
የመበልፀጉ መነሻ ነው፡፡ ካልጠየቀ በቃኝ ባይ ይሆናል፤
ካልጠየቀ ለውጥ አይሻም፤ ካልተለወጠ ዕድገትና ውድቀት
የሚባሉ ሂደቶችን አያልፍም፡፡ ተፈጥሯችን ግን እንዲያ ሆኖ
ለመኖር አይፈቅድልንም፡፡ እናም- እንደሰውነታችን-
እንጠይቃለን፡፡ ስለምንጠይቅም ዛሬ፣ ትላንት እና ከትናንት
ወዲያችን አንድ አይደሉም፡፡ እጓለ ገብረ ዮሐንስ የሰው ልጅ
አካባቢውን አሜን ብሎ ተቀብሎ በኖረበት ዘመኑ፣ “የተፈጥሮ
ችሎታውን ባለማወቅ … በዙሪያው የሚገኙት የሥነፍጥረት
ጉልበቶች መጫወቻ ነበር፣” ይላሉ (የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣
ገፅ 97)፡፡
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር፣ በ“ስምንተኛው ጋጋታ”፣ ጠያቂነት
እንደነውር የሚያስወቅስበት እንደ ሃጥያት የሚያስወግዝበት
እንደ ወንጀል የሚያስቀጣበትን፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አኗኗር
ነቅፏል፡፡ በተለይ ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ አድርጐ በተረከባቸው
ገጾች ስብሃት ይኼን ሥርዓት ሲቃወም መርማሪነትን ሲያበረታታ
እናገኘዋለን፡፡ ሰይጣንን ገፀ ባሕርይ አድርጐ ማምጣቱም
ሁልጊዜም ከአንድ አቅጣጫ የሚፈስ “እውነት” ተቀባይ
መሆናችን የዋህነት መሆኑን ለማመልከት ይመስላል፡፡
በታሪኩ ውስጥ ሰይጣን በሦስት የተለያዩ ሁኔታዎች
ያጋጥመናል፡፡ በያዙት ጭብጥ ተቀራራቢነት በተለይ ሁለቱን፣
ማለትም ሰይጣን ከኢየሱስ ጋር በሲኦል የተወዳጀበትንና ከዋና
ገፀ ባሕርይው ከአቶ አልአዛር ጋር ያደረገውን የስልክ የሐሳብ
ልውውጥ በማንሳት፤ ስብሃት መርማሪነትን በተረታዊ ድርሰቱ
አማካይነት አበረታቷል ያስባለኝን ለማስረዳት እሞክራለሁ፡፡
የሃይማኖት መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት ሰይጣን ከእግዜር
በታች ከሰው በላይ ሆኖ ምድርን በክፋቱ የሚገዛት፣ የዚህች
ዓለም ገዢ ነው፡፡ ሰይጣን፣ ሳጥናኤል በትርጉሙም፣ “ሰግዶ
አሰጋጅ” ተብሎ አስቀድሞ የተሰጠውን የመላዕክት አለቅነት
በገዛ እጁ ያጣ፣ በአምላኩ ላይ አምጾ ክብሩን የተነጠቀ
መንፈሳዊ ፍጡር ነው፡፡ የፈጣሪውን ዙፋን በመመኘቱና
ፈጣሪውን በማስቆጣቱ ወደ ምድር ተጥሏል፡፡ አዳምና ሄዋንን
አስቶ ከእግዜር መንገድ አስወጥቶ ፀጋቸውን አስገፍፏል፡፡
ለሞትም መምጣት ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ የኢዮብንም
ትግስት ተፈታትኗል፤ የኢየሱስንም ያርባ ቀን ጾም፣ የ3 ዓመት
ከ3 ወር ተልዕኮ ለማክሸፍ ሞክሯል፡፡ እናም ሰይጣን
የእግዚአብሔር ተቃራኒ የሰው ልጆችም ጠላት እንደሆነ
የሃይማኖት አባቶችና መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡
የስብሃት ድርሰት ግን ሰይጣንና ኢየሱስን ያወዳጃል፡፡
ሃይማኖታዊውን እውነት የምናይበት ሌላ መነጽር ያጠልቅልናል፡፡
ወይም እውነቱን ለማየት ከቆምንበት አቅጣጫ በተቃራኒው
አቁሞ ያየነውን በሌላ ዐይን ያሳየናል፡-
“ኢየሱስ ፍቅር ነውና አዳምን ወዶት ሊያድነው የሞትን ወንዝ
እንደተሻገረ ሁሉ፣ ሰይጣንንም ወዶት በስደት አገሩ በሲኦል
ሊጠይቀው የዘላለምን ወንዝ ተሻገረ፡፡
ሰይጣንም በግዞት አገር ሊጐበኘው የመጣውን እንግዳ እደጀ
ሰላም ድረስ ወጥቶ ተቀበለው፣ ይወርድ ዘንድ አህያውን
ባለሻኛውን ያዘለት፣ ይገባ ዘንድ በሩን ከፈተለት…” (127-8)
በዚህ ክፍል ሰይጣን እንግዳው ኢየሱስን ጠላና ቆሎ አቅርቦ
ከጨዋታ ጋር አስማምቶ ያስተናግደዋል፡፡ ኢየሱስ ሲኦል ድረስ
የወረደው የሰይጣንን ወዳጅነት ፈልጐ አይደለም፡፡ ሰይጣንን
“አታሎ” ነፍሳት ሊሰርቀው እንጂ፡፡
ሰይጣንና ኢየሱስ በሰዎች ነፍሳት ላይ የየራሳቸው ፍላጐቶች
አሏቸው፡፡ ሁለቱም እነዚያን ነፍሳት ይፈልጓቸዋል፡፡ የስብሃት
ኢየሱስም ከሰይጣን የተወዳጀ የመሰለው በሰይጣን ግዛት
(ሲኦል) ከታሸጉት ነፍሳት ወደራሱ ግዛት በዘዴ ለመውሰድ ብሎ
መሆኑን እናያለን፡፡
“ሳቀ ኢየሱስ ከት ብሎ ሳቀ፣ ሲኦል ግድግዳው ተሰነጠቀ፣
ነብሳት ነቁ በስንጥቁ፣ በሺ በእልፍ እየወጡ አመለጡ፡፡ ሰይጣን
ይህን አልጠረጠረ፣ 'ንገረኝ አብሬህ ልሳቅ፣' አለ፡፡” (129)
የስብሃት ኢየሱስ፣ “ወንድሜ ሳጥናኤል ሆይ፣” እያለ ሰይጣንን
እያባበለ የሰይጣን ንብረት (ዜጐች) የሆኑትን ነፍሳት ዘርፎታል፡፡
ስብሃት ግን እዚህ ጋር ቆም ብለን፤ የኖረውን ትረካ ገልበጥ
አድርገን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ማታለል የሰይጣን ተግባር
ሆኖ ሳለ፣ በዚህ ትረካ ውስጥ ግን አታሎ መዝረፍ የኢየሱስ
ሆኗል፡፡ በርግጥ ሰይጣን ሲያታልል ሞትን ለሰው ልጆች አመጣ፤
ኢየሱስ ሲያታልል ነፍሳት ዘላለማዊ የደስታ ኑሮ እንዲኖሩ
ያደርጋል፡፡
ኢየሱስና ሰይጣን በተወዳጁበት በዚሁ ክፍል የተነሳን ሌላ
ሁኔታም እናንሳ፡-
“ውድ ወንድሜ ሳጥናኤል ሆይ፣ እስቲ የምድርን ነገር አንሳና
ስለ ሰው ልጆች አጫውተኝ፡፡ መሬት ስጋ አብቅላ አድጐ
ሲያብብ፣ ያበበው ጠውልጐ ሲረግፍ፣ በሌላ አበባ ሲተካ
የሚነግር ወሬ ጨዋታ አምጣ፡፡ እገሌ እንዲህ ሆነ እንዲህ
ደረሰበት የሚል ጨዋታ፡፡ ተረት ብጤ ጨዋታ...” (129)
ኢየሱስ ለሰይጣን የ“እንደምን ላስተናግድህ” ጥያቄ ስለምድር
የሚያወራ ተረት ብጤ ጨዋታ እንዲያጫውተው ጠይቆታል፡፡
ሰይጣን ደግሞ እንደ እንግዳ ተቀባይነቱ የእንግዳውን ጥያቄ
ተቀብሎ የእንግዳውን ሐሳብ ለመሙላት ካዲሳባ ተረት ይዞ
መጥቷል፡፡
...ከዚያማ ሰይጣን ተረቱን ጀመራታ.. የመኖር የመሞት ጨዋታ፣
ኩኩሉ አይነጋም ጨዋታ፣ አየሁሽ ለየሁሽ ጨዋታ፣ እንቁልልጭ
ሙልልጭ ጨዋታ፣ እንቆቅልሽ ቆቅ ታንቆልሽ ጨዋታ፡፡
አቶ አልአዛር... ቤታቸው በራፍ ሊደርሱ ጥቂት እርምጃ
ሲቀራቸው እንቅፋት መታቸውና ወደቁ፡፡ ተነሱ፣ ሰውነታቸውን
ደባበሱ፣ ልብሳቸውን አራገፉና ወደ ቤታቸው በር ራመድ
ራመድ...
ኧ..? ቤታቸው ከስፍራው የለም፡፡ ኧ..? (130)
አቶ አልአዛር የድርሰቱ ዋና ባለታሪክ ናቸው፡፡ አቶ አልአዛር አንድ
ጊዜ የውሽማቸውን ቤት በሌላ ጊዜ የራሳቸውን ቤት ከስፍራው
አጥተዋል፡፡