ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ አምሰት
12 የሺርክ አደጋዎች
12.1 ስራዎችን ሁሉ ያበላሻል
መቼም የምርጥም ምርጥ አለው። አላህ የአደምን ልጅ አልቆታል። ከአደም ልጆች ውስጥ ደግሞ መልክተኞቹና ነብያቱን አስበልጧል።ነብያቱና መልክተኞቹ ከሰዎች ጥቅምን ሳይፈልጉ ከአዛኙ አላህ የሚወርድላቸውን መለኮታዊ ራእይ ለፍጡራኑ ለማድረስ በድብቅም በግልፅም፣በቀንም በማታም ደፋ ቀና ያሉና የለፉ ናቸው።የአላህን መልእክት ለማድረስ ሲሉ ስንት ከባድ አደጋ በህይወታቸው፣በንብረታቸው፣በቤተሰቦቻቸው ላይ የደረሰባቸውና ስንት መስዋእት የከፈሉ፣ስንትና ስንት ገደል የፈፀሙ ናቸው።
ግን ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ሺርክ የሚባለው ነገር ቢፈፅሙ ስራቸው ሁሉ እንደሚታበስ ጌታችን እንዲህ ሲል ነግሮናል፦
ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهْدِى بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ ۚ وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡(አል -አንዓም :88)
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከአንቀፁ በፊት ልብ እንበል አላህ የነዚህን ነብያት ገድል ተናግሮላቸዋል።አላህ እዚህ ጋር ቢያጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር ብሎ የጠቀሳቸው 18 ነብያት የሚከተሉት ናቸው ፦
አላህ ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዛቸው ነብዩላህ ኢብራሒም- አል ኸሊል ፣ነብዩላህ ኢስሐቅ ፣ነብዩላህ ያዕቁብ፣ነብዩላህ ኑሕ፣ነብዩላህ ዳውድ፣ነብዩላህ ሱለይማን፣ነብዩላህ አዩብ፣ነብዩላህ ዩሱፍ፣ አላህ ያናገራቸው ነብዩላህ ሙሳ፣ነብዩላህ ሃሩን፣ነብዩላህ ዘከሪያ፣ከሳቸው በፊት ሞክሼ የሌላቸው ነብዩላህ የሕያ፣ በአላህ ፍቃድ ለምጣምን ያዳኑት ፣የሞተን የቀሰቀሱት የመርየም ልጅ ነብዩላህ ዒሳ፣ነብዩላህ ኢልያስ፣ካዐባን ከአባታቸው ኢብራሒም ጋር የገነቡት፣ከአባታቸው ጋር ለአላህ ትዕዛዝ እጃቸውን በመስጠት ሊታረዱ የነበሩት ነብዩላህ ኢስማኤል፣ነብዩላህ የሰዕ፣ ነብዩላህ ዩኑስ፣ነብዩላህ ሉጥ ናቸው።እሺ እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እንወስዳለን ?
ምንም አይነት ምድራዊ ጥቅምን ሳያልሙ “አላህን ብቻ በብቸኝነት አምልኩ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ማንንም ይሁን ምንንም ራቁ ”፣ ወገኖቼ ሆይ ! አላህን በብቸኝነት አምልኩ። ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም” እያሉ ለተውሒድ የተዋደቁ የአላህ ምርጥ ባሮች እንዲህ ከተባሉ እኛስ ምን እንባል ? ሌላ ምሳሌ አላህ ሊጨምርልን ነው ።የአላህ ውድ፣የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ፣የታላቁ ምልጃ ባለቤት፣ለአለማት እዝነት የተላኩ፣የአደም ልጆች ሁሉ ምርጥ፣ታላቁ የተውሒድ አስተማሪ ፣የኢብራሒም መንገድ ተከታይ ፣ነብዩ ሙሐመድ አበል ቃሲም ﷺ አላህ እንዲህ አላቸው፦
وَلَقَدْ أُوحِىَ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡
ይሄ እኛን ለማስተማሪያ እንጂ እሳቸው ከሺርክ የፀዱ ናቸው።እንዲያውም እኛን በአላህ ፍቃድ ከሽርክ ጨለማ አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ( በማስተማር) ሊመሩ የመጡ ናቸው።ግን ሱብሃነላህ ሺርክን ምን ያህል ከባድ እንደሆነና ስራን ሁሉ ድምጥማጡን እንደሚያጠፋ ከእንደዚህ አይነት ምሳሌዎች በላይ ምን ይምጣ ? !!!
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 30-32)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide