" ከከባዱ አደጋ አንዲትም ጭረት ሰውነታችንን ሳይነካን ነው የወጣነው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው !! " - ሳቢር ይርጉኡስታዝ ሀሺም ሽፋ እና ሳቢር ይርጉ አስከፊ ከሆነ የመኪና አደጋ አንድም ነገር ሳይሆኑ በህይወት ተረፉ።
ዛሬ ምሽት ከሱሉልታ አቅጣጫ አጣና ጭኖ ቁልቁለቱን ሲምዘገዘግ የነበረ ኤኔትሬ ከባድ መኪና ከነጭነቱ እነ ኡስታዝ ሲጓዙበት በነበረችው መኪና ላይ ከባዱ አደጋ አድርሷል።
ሳቢር ይርጉ ፤ " እንሆ የአላህን ኒዕማ አውጀናል። በአላህ ፈቃድ ሁለታችንም ከከባዱ አደጋ ምንም ሳንሆን ተርፈናል። ሁለታችንም አንዲትም ጭረት ሰውነታችን ላይ ሳይደርስ በሰላም ወጥተናል አልሀምዱሊላህ !! ወደ የቤታችንም ገብተናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" በህይወት ስንተርፍ ሞትን አንዘንጋው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው። አልሀምዱሊላህ ጀዛኩሙላሁ ኸይር ! " ሲሉ አክለዋል።
አደጋው የደረሰባቸው ዛሬ ምሽት ለጥቂት ቀናት የሊደርሺፕ ስልጠና ለመካፈል እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።
መኪናዋን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ ሲሆኑ ሁለቱም ከከባዱ አደጋ አንድም ጭረት ሰይነካቸው በህይወት ተርፈው ወደ ቤት ገብተዋል።
መረጃውን ያካፈሉን በ ' ድምጻችን ይሰማ ' የሰላማዊ እንቅስቃሴና ትግል ወቅት በእጅጉ የሚታወቁት ሳቢር ይርጉ ናቸው።
@yasin_nuru@yasin_nuru