🔷 አሁንም ወደ አላህ እንመለስ
የቅርቢቱ ዐለም ስቃይና መከራ ሰዎችን ነፍሳቸው ጉሮሯቸው እስከ ምትደርስ ያስጨንቃቸዋል በፍርሃት እንዲርዱ ያደርጋቸዋል ። ይህ መከራና ስቃይ በተደጋጋሚ ለማስታወስ እንደተሞከርነው ከአላህ የሆነ ፈተና ነው ። ምክንያቱ ደግሞ የኛ ሀጢያት ውጤት ነው ። አማኞች እንዲህ አይነት ፈተና ሲገጥማቸው በፅናትና በትእግስት እንዲሁም በተውበትና በኢስቲግፋር ሊያልፉት ይገባል ። ተስፋ ሊቆርጡ ወደ አላህ ከመጠጋት ሊገታቸው አይገባም ። ለአማኞች መሸሻም ሆነ መጠጊያ ከሱ ሌላ የላቸውምና ። ለዚህ እንዲረዳቸው የቂያማ ቀን ያለውን ጭንቅና መከራ ማስታወስ ይጠቅማል ። የዚህች ዓለም ፈተና የመጨረሻው በሞት ይጠናቀቃል ። የአኼራው ፈተና ሞት ቢፈልጉትም የማያገኙበት ነው ። ሁሉንም የሚያካትተው የቂያማ ፈተና ከባድ ነው ። ልጅ ወላጁን የሚረሳበት ፣ ወላጅ ልጁን የማይጠቅምበት ፣ ነፍሰ ጡር በድንጋጤ ፅንሷ የሚጨናገፍበት ፣ አጥቢ እናት የምታጠባውን ህፃን የምትረሳበት ፣ ተራሮች ወደብናኝነት የሚቀየሩበት ፣ ባህሮች የሚነዱበት ፣ ሰማዮች እንደ ወቀት የሚጠቀለሉበት ፣ ምድር የተሰራባትን የምትናገርበት ፣ ህፃናት ሽበት የሚያበቅሉበት ፣ ሁሉም በድንጋጤ የሚሰክርበት ቀን መኖሩን ማሰብ የዛሬውን ጭንቀት ያቀለዋል ። ይሁን እነጂ ይህ ፈተና አላህ እኛን ሊያስተምርበት ያመጣው ነው ።
የሰላም ዋጋ ስንት ይሆን ?
ትላንት ድርጅት ፣ ቤትንብረት ፣ መኪና ፣ ያማረ ጊቢ የነበራቸው ዛሬ ይህን ሁሉ ጥለው ነፍስ ማዳን ያልቻሉትን ስናይ ስንሰማ በዚህ ኒዕማ ላይ ያለን ምን እየተሰማን ይሆን ?
እነዚህ ወገኖቻችን ሞኝ ስለሆኑ ይሆን የዚህ መከራ ባለቤት የሆኑት ?
መልሱ አይደለም ነው ። ነገ እኛም ምን እንደ ሚገጥመን አናውቅም ስለዚህ ከልባችን ወደ አላህ እንመለስ ። ሌላው አሁን ደሴና ኮምቦልቻ ባለው ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ እየተሰደዱ ያሉ ወንድሞቻችን አሉ ባዶ እጃቸውን ህፃናትንና ሴቶችን ይዘው ከቄያቸው የወጡ እነዚህ ወንድሞቻችን ከጎናቸው ልንሆን ይገባል ። አንድ ወንድማችን ቤተሰቦቹ መጥተው በሱ ላይ ሲደረቡ እያየን ወይም ጋደኛ ጋር መጥተው የሰው እጅ ሲያዩ ከንፈር መጠን ዝም ማለት የለብንም ። ተቀናጅተን ቤት ተከራይተን አስቤዛ አሟልተን አለን ልንላቸው ይገባል ። ይህን ነው ኢስላም ያስተማረን ። የመዲና አንሷሮች እስከ ቂያማ አንሷር ( ረዳት ) በሚለው የማእረግ ስም እንዲጠሩ ያደረጋቸው የመካ ሙሀጂሮችን ( ስደተኞችን ) ተቀብለው ያላቸውን አካፍለው የመረጡትን እንዲወስዱ በማድረጋቸው ነው ። ፈለጋቸውን መከተል ነብዩን የመውደድ ምልክት ነው ። በኪታብ የቀራነውን ወይም በድምፅ የሰማነውን የምንተገብርበት ጊዜ አሁን ነው ። ለዚ ተግባር ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ ።
https://t.me/bahruteka