TIKVAH-MAGAZINE:
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ጉባኤው ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡
በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም የሚገመገም ሲሆን የ2013ን በጀት ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ጠቁመዋል። እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ ቃለ ጉባኤ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የክልሉ የውሃና ፍሳሽ አዲስ ደንብ ማጽደቅም የጉባኤው አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራሮች ቦታ ሹመት ያጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡
#FBC
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
#HERQA
ፓራዳይም ዩኒቨርስቲ በሚል እራሱን ሰይሞና ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመከል እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ቢገልጽም በኤጀንሲው በኩል ምንም እውቅና እንዳልተሰጠውና ተማሪዎችና ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተገልጿል፡፡ ጉዳዩን በህግ አግባብ እንዲታይ እንደሚያደርግም ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ህክምና ተወገደ!
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን 6 የእንስሳት ሃኪሞች ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ህክምና አስወገዱ። ከጤና ባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ፍራኦል ዋቆ፤ “ላሚቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች” ሲሉ ከቀዶ ህክምናው በኋላ #ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ዶ/ር ፍራኦል “ከብቶች የሚግጡት ሳር ሲያጡ ወይም በሰውነታቸው ውስጥ የንጥረ ነገር እጥረት ሲያጋጥማቸው ፕላስቲክ ሊበሉ ይችላሉ” ያሉ ሲሆን ጨምረውም፤ ሰዎች ፕላስቲክ የሚያስወግዱበት መንገድ ለቁም እንስሳት ጤና ችግር እየሆነ ነው” ብለዋል።
50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ የተወገደላት ላም ባለቤት የሆኑት አቶ አሬሪ ጨሪ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደምም ፕላስቲክ የተመገበች ሌላ ላም ወደ ጤና ባለሙያዎቹ አምጥቶ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ ከሆዷ ወጥቶ ነበር።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
"ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም"- ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
- " ግልጽ መሆን ያለበት መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ ይህን ማስቆም በህገመንግስቱ የተሰጠው ኃላፊነት ነው ። የሰራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ፤ ግዴታም አለበት"
- የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያውያንን እኩል ሊያገለግል የሚችል ተቋም ሆኖ እየተገነባ መሆኑን አመልክተው፣ የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ ዕሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ሊቀረጽና ሊገነባ የማይገባው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
- ኢትዮጵያን እኔ ከሌለሁ ትፈርሳለች ወይም እኔ ካልተጠቀምኩ እናፍርሳት የሚለው አካል ሁል ጊዜ ቢናገርም፤ በእኔ በኩል ኢትዮጵያን የምትፈርሰው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ላይ የሚያምኑት ሕዝቦቿ እና መሪዎቿ ከሌሉና ከሌሉ ብቻ ነው ፡፡ ከዛ በላይ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው የመከላከያ ኃይላችን፣ የፀጥታ ኃይላችን፣ የደህንነት ኃይላችን ሲፈርስ፤ ወይም እሱ መስዋዕት ሆኖ ሲሸነፍ ብቻ ነው::"
Readmore https://telegra.ph/ENA-07-25
#ENA