#ማሳሰቢያ
ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ባሉበት
ጉዳዩ ፡-ለመውጫ ፈተና አገልግሎትየሚውል ክፍያን ይመለከታል
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም በመመሪያው ቁጥር 919/2014 ክፍል 24 መሠረት ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እና መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም (ክረምት፣ማታ፣የሳምንት መጨረሻ ፣ ርቀት እና ሌሎች) ትምህርታቸውን በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አገልግሎት ክፍያ እንደሚከፍሉ ተመላክቷል፡፡ በመሆኑም በየተቋሞቻችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ቁጥር መሠረት በማድረግ በአንድ ተማሪ 500(አምስት መቶ )ብር በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000553176097 የባንክ ደረሰኝ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በtibletmule@
gmail.com, zebibazemu @
gmail.com እና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማ ት በsemusisay2007 @
gmail.com ኢሚይል አድራሻ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
#ማስታወሻ
• የክፍያ ጊዜን በተመለከት ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋሙ ተፈታኝ ተማሪዎች ዝርዝር በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተቀባይነት ባገኝ በ5 (አምስት ) ቀናት ውስጥ ብቻ ሲሆን ለመንግስትከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከ ጥር 15 /2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
• ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ የማያስገቡ ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እንደማያስፈትኑ ይቆጠራል፡፡
በፊስቡክ -
https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር-
https://twitter.com/FDRE_ETAበዌብሳይት Www.
neta.gov.et ይከታተሉ