በሞስኮ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል አዛዥ ተገደሉ‼️
በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ አንድ አፓርትመንት ሕንፃ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፤ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸው ተገልጿል፡፡
ኢጎር እና ረዳታቸው የተገደሉት ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የመኖሪያ አፓርትመንታቸው ውጭ በደረሰ ፍንዳታ ነው ተብሏል።
ጄነራሉ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ መሆኑን በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው ታስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር፤ በኮስትሮማ ከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኬሚካል መከላከያ ትምህርት ቤት ወታደራዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 ጀምሮ የጦር ኃይሉን እንዲመሩ ተሹመዋል።
ጄኔራሉ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ጨምሮ ከአደገኛ ፈንጂዎች ጋር በተዛመደ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ በተለያዩ ሚናዎች አገልግለዋል። በትላንትናው ዕለት የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ዩክሬን ውስጥ የተከለከለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲል ጄኔራል ኢጎርን ከሶ ነበር፡፡የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት በኪሪሎቭ መሪነት ሩሲያ 5 ሺሕ ያህል የኬሚካላዊ መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ሲል ተናግሯል።
ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር "በዩክሬን በሩሲያ ጦርነት ላይ አውዳሚ ኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተጠቅመዋል" በሚል በብሪታኒያ፣ ካናዳ እንዲሁም በሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ቆይቷል።